በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች የነበሩ የህወሓት አመራሮች እና የደህንነት አባላት ከተማውን ለቀው እየወጡ ነው ፡፡

በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች የነበሩ የህወሓት አመራሮች እና የደህንነት አባላት ከተማውን ለቀው እየወጡ ነው ፡፡

Ethiopia : ዛሬ ታህሳስ 11 ቀን 2010 ዓ/ም በደረሰን መረጃ በአማራ ክልል በባህርዳር ከተማ የህወሓት የድርጅቱ አስተባባሪ እና የትግራይ ልማት ማህበር ሊቀመንበር በመሆን ከፍተኛ የደህንነት ስራ እና ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች የሚሰጠውን ተልዕኮ በክልሉ ሲፈፅም እና ሲያስፈፅም የነበረው ፀጋዬ በየነ የተባለው ከ 10 ቀን በፊት ወደ አዲስ አበባ ሄዶ ከቆየ በኃላ ዳግመኛ ወደ ባህርዳር ሳይመለስ ወደ አሜሪካን አገር ኮብልሏል ፡፡ የባህርዳር ህዝብ ከአሁን ቀደም ስርዓቱን በመቃወም አደባባይ በወጡበት ወቅት ይህ የህወሓት አመራር ራሱ እና ልጆችን ጭምር በማሰለፍ ከፍተኛ በደል ፈፅማል ፡ በተለይ ሳሙኤል (ሳሚ) ፀጋዬ የተባለው ባህርዳር አባይ ማዶ ከሚገኘው ሳሚ ጃንቦ ሀውስ የህወሓት ነብሰ ገዳይ የሆኑ የአጋዚ አባሎች ስናይፐር እንደያዙ ከድርጅቱ በማስገባት እና ቦታ በመስጠት በርካቶች ንፁሀን እዲገደሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል በዚህ ድርጊቱ አርበኞች እና የከተማው ወጣቶች ክትትል ሲያደርጉበት ወደ አዲስ አበባ በመሔድ ከደህንነት ቢሮ በመሆን በቪዲዮ የተቀረፁ እና በደህንነት ካሚራ የተነሱ የነፃነት ጠያቂ ወጣቶችን ምንነት በመለየት እና በማስያዝ ስራ ሲሰራ ከቆየ በኃላ በቅርብ ቀን ወደ አሜሪካ እንደተላከ ሳይመለስ መቅረቱ መረጃ ያመለክታል ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም በክልሉ የሚኖሩ የህወሓት የደህንነት አባላት በጨለማ እና አሳቻ ሰዓት በመጠበቅ ከክልሉ እየወጡ ይገኛሉ ። ከአሁን ቀደምም በሰሜን ጎንደር ዋና ተዋናይ የነበረው አምባዬ አማረ በአርበኞች በቦንብ የግድያ ሙከራ ሲፈፀምበት ከቦታው ለቆ ወደ አሜሪካ እደሄደ የሚታወስ ነው ፡፡

በመሆኑም በቅርብ ቀን እነዚህ የደህንነት አባላት በድብቅ በህዝብ ደም ዘርፈው የሰሩትን ድርጅት እና የመኖሪያ ቤት እየሸጡ እንደሆነ መረጃዎች እየመጡ ሲሆን የነዚህን በህግ የሚፈለጉ በንፁሐን ደም እጃቸው የተነከሩ ሰዎችን ንብረት መግዛት ማለት በንፁሀን ደም እንደመነገድ ስለሚቆጠር በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በዚህ ግዥ የምትሳተፋ ሰዎች ከአድራጎታቹሁ እንድትቆጠቡ ለማሳሰብ እንወዳለን ፡፡

 

Via : Natnael Mokonnen


Ethiopia : በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የትግራይ ልማት ማህበር የሰጠው መግለጫ ጉድ ነው ዘንድሮ ስንቱ የኦሮሞና የአማራ ልጅ ሲጨፈጨፍ ዝም ብለው ስለ ሱማሌ ጭፍጨፈ ሊያውም ወያነ ለአቀነንባበረው ግድያ የሀዘን መግለጫ ያወጣሉ ይህ የትግራይ ልማት ማህበር በኦሮሞና በአማራ ክልሎች መሬት ዘርፎ ፈብሪካዎችን እየከፈተና እየገነባ ያለ ማህበር ነው:: የዚህ መሀበር ንበረቶች ይታሰብበት በገዛ ሀገራችንን ሶስተኛ ዜጋ ሆነን ሶስቴ አንሞትም !


Ethiopia : ሃሃሃሃ እነ ወዲ በትግራይ መሀበር ስም መግለጫ ያወጡና በሶሻል ሚዲያና በጋዜጠኞች እንዲሁም በአክቲቪስቶችና በህዝቡ ውግዘት ሲገጥማቸው የመሀበሩ አቋም አደለም የመሀበሩ አባል በግሉ ያወጣው ነው ይሉሀል ጉጀሌ ሁላ ! አደለም መግለጫ ህዝብ ስትገሉና ስታስሩ ስታባሉ ተመካክራቹሁ እንደሆነ ብታምኑም ባታምኑም ይህ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃ


 

1 Comment

  1. the executive committee of the UTNA should have to officially denounce the the contents of the letter of condolence if they want us understand them.
    Otherwise it will be understood as it was written by the consent of the association without attributing it to individual.

Comments are closed.