በአማራ ክልል ሰሜን አቸፈር ወረዳ አቶ ደርቤ አየለ የተባሉ ግለሰብ ቤታቸውን ሊፈትሹ ከመጡ የኯማንድ ፖስት አባላት ጋር ባለመስማማታቸው በተፈጠረ

በአማራ ክልል ሰሜን አቸፈር ወረዳ አቶ ደርቤ አየለ የተባሉ ግለሰብ ቤታቸውን ሊፈትሹ ከመጡ የኯማንድ ፖስት አባላት ጋር ባለመስማማታቸው በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ስድስት የኮማንድ ፖስቱ አባላት ሲገደሉ ስድስት ደግሞ ቆስለዋል

#AmhraStrikes– six members of the command post were killed & 6 wounded during a gun fire exchange with Derbe Ayele when the they insisted in searching his house.
Derbe took his own life & received a hero’s burial in #Amhara region North Achefer woreda. #StateOfEmergency

#HERO : የመቶ አለቃ ደርቤ አየለ የቀብር ስነ ስርዓት በድምቀት ተከናወነ ፡፡ #RIP

#Ethiopia : የህወሓት ት ወታደሮችና ባንዳዎች የካቲት 25 ቀን 2010 ዓ/ም ለሊት ላይ ሲሆን በሰሜን አቸፈር ድርቤቴ ከተማ ነዋሪ የሆኑትን የመቶ አለቃ ደርቤ አየለን ከመኖሪያ ቤታቸው ለማፈን 55 ሆነው የሔድትን የህወሓት ኃይሎች 13 ቱን በመግደል ከ30 በላይ በማቁሰል ከፍተኛ ጀብድ በመስራት ራሳቸውን ሰውተዋል ፡፡ የመቶአለቃ ደርቤ አየለ የ72 ዓመት እድሜ ባለፀጋ የነበሩ ሲሆን ቀደም ሲል በሕዝብ ላይ የሚፈፀሙ በደሎችን በመቃወም በድር ሲታገሉ ከቆዩ በኃላ በቀድሞው መንግስት ማለትም በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባል በመሆን ከፍተኛ ጀብድ ሰርተዋል በቀድሞው መከላከያ ሰራዊት ለ11 ዓመት ያገለገሉ ሲሆን በመጀመሪያ የ6ተኛ ክፍለ ጦር 14ተኛ ሻለቃ አባል በመሆን አኩሪ ታሪክ ሲሰሩ ቀይተው በመጨረሻም ወደ ኤርትራ አስመራ በመቀየር የ31ኛ ክፍለ ጦር አባል በመሆን ቡዙ ጀብዶችን ሰርተዋል በዚህ በሰሩት ጀብድ እንዳሁኑ ሳይሆን ማዕረግ እጅግ ውድ በሆነበት ወቅት ከምክትል የአስር አለቃ እስከ መቶለቃ ማዕረግ ደርሰዋል ፡ ከደርግ ውድቀት በኃላ ወደ ትውልድ ቦታቸው በመመለስ በግብርና እና በንግድ ስራ በመሰማራት ኑራቸውን የሚመሩ የነበረ ሲሆን እሳቸውም የአገሪቱ ሁኔታ እጅግ እያሳዘናቸውና በዘር በመከፋፍል ታሪክን ህወሓት ሲያበላሸው እጅግ ይቆጩና ያዝኑ ነበር ፡፡ በዚህም ምክንያት ህወሓቶችና የእሱ ጉዳይ ፈፃሚ የሆኑ ብአዴኖች እየተከታተሉ ያስቸግራቸው ነበር ፡ የኒህ ሰው ተሰሚነትና በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነታቸው ያሳሰበው ወያኔ የካቲት 25 ቀን 2010 ዓ/ም ከ55 በላይ የሚሆኑ ወታደሮቹን እና ፀረ ሽምቅ አባሎቹን አስከትሎ ወደ መኖሪያ ቤታቸው የሔደ ሲሆን ፖሊስ አዛዡ የመኖሪያ ቤታቸውን በርግዶ ሲገባ በፍጥነት ተኩሰው ግንባሩን በመመታት ሲገድሉት ተከታትለው የመጡትን 9 የመከላከያ አባላትን ተኩሰው ገድለዋል ከዚያም ከ30 ደቂቃ በላይ ከተታኩሱ በኃላ ጥይት ሲጨርሱ በያዛቸው ቦንቦች ከ30 በላይ የህወሓት ኃይሎችን ከባድ የማቁሰል አደጋ አድርሰዋል እነዚህ የቆሰሉ የህወሓት የፀጥታ ኃይሎች እጅና እግራቸው ተቆርጠው በባህርዳር ፈለገ ሔይወት ሆስፒታል ተኝተው ይገኛሉ ፡ በመጨረሻም በስልት እጃቸውን ከሰጡ በኃላ “እጅ ስጥ አለኝ እጅ ተይዞ ሊወሰድ ፡ አያውቅም እንዴ ክንዴ እንደሚያነድ ” በማለት ህወሓቶች የማረኩና በቁጥጥር ስር የዋሉ መስላቸው በደስታ ስሜት ወደ ተሽከርካሪ እንዳወጣቸው እኒህ ጀግና በኪሳቸው ደብቀው በያዛት የእጅ ቦንብ ከበው የያዛቸውን 4 የህወሓት ወታደሮቹን ጨምሮ እሳቸውን አጥፍተው በመስራት በጠላት ሳይሆን በራሳቸው እጅ ራሳቸውን አጥፍተዋል ፡፡ በመሆኑም የኒህ ጀግና የቀብር ስነስርዓት የካቲት 26 ቀን 2010 ዓ/ም ከቀኑ 7:00 ሳዓት ሲሆን ዘመድ ወዳጆቻቸውና ጀግና አክባሪ የሆነው ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ በተገኘበት የቀብር ስነስርዓታቸው ተፈፅማል የ መቶ አለቃ ደርቤ አየለ ባልትዳር የነበሩ ሲሆን የ8 ወንዶችና የ2 ሴት በድምሩ የ10 ልጆል አባት ነበሩ ፡፡ ከኒህ ጀግና ሁላችንምጠቡዙ ትምርት በመውሰድ ትጥቄን አልፈታም ለዘረኛና ለባንዳ እጄን አልሰጥም በማለት የሰሩትን አኩሪ ተጋድሎ በመቀበል የሞቱለትን አላማ ከግብ ለማድረስ እድንረባረብ ጥሪ እያቀረብን ፡ የኒህን ጀግና ገድል እና ታሪክ በቀጣይ የምናቀርብ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡ ድል ለሕዝብ !!!