በአለም መድረክ ከአሁኑ እውቅና የተነፈገው የምርጫው ጫወታ እና የሚኖረው ውጤት!!

በአለም መድረክ ከአሁኑ እውቅና የተነፈገው የምርጫው ጫወታ እና የሚኖረው ውጤት!!

ከታች ምስሉ ላይ የሚታዩት በተለያዩ ጎራ ተሰልፈው በጋራ ለአንድ አላማ የሚሰሩ ቁልፍ የወቅቱ ባለስልጣኖች እና ታዋቂ ሰዎች ናቸው:: ሶስቱም ምርጫውን ብልጽግና ፓርቲ እንዲያሸንፍ እና አዲስ አበባን ኢዜማ እንዲወስድ በጋራ እያመቻቹ ይገኛሉ፡፡ በቀጣይ ምርጫ ብልጽግና በትንሹ 80% አጊኝቶ በሐገር ደረጃ እንዲያሸንፍ እና ገዢ ፓርቲ እንዲሆን በምርጫ ቦርድ ተመቻችቶለታል፡፡ የብልጽግና አካል የሆነው አዴፓ ንዑስ ፓርቲ በምርጫው ብልጽግና እንዲያሸንፍ ከሚመኘው በላይ የኢዜማው ብርሐኑ ነጋና የምርጫ ቦርድ ሐላፊዋ ብርቱኳን ሚደቅሳ ብልጽግና ፓርቲ እንዲያሸንፍ ከልብ ይመኛሉ፡፡
 
በአንጻሩ አዴፓ መሐል ላይ ቆሞ ግራ በመጋባት ላይ ያለ የብልጽግና አጋር ፓርቲ ነው፡፡ በስተመጨረሻ በብልጽግና አካሄድ በጣም የሚጎዳው እና ብዙ ዋጋ የሚከፍለው ኦዴፓ ቢሆንም፤ አሁን ላይ ብልጽግና ወዴት እየሄደ እንደሆነ ምንም ስላልገባው ወጥሮ ምርጫውን እየደገፈው ይገኛል፡፡ የሆኖ ሆኖ ብልጽግና ካሸነፈ ቦሓላ አሁን ያሉት የክልልም ሆነ የፌደራል ባለስልጣኖች በሙሉ በአዲስ አመለካከት ባላቸው እና የዜግነት አስተሳሰብ በሚያራምዱ አባላት እንዲተኩ በአብይ አህመድ ስለሚደረግ ከምርጫ ቦሃላ ማንም ቢንጫጫ እራሱን ከጥቅም ውጪ አድርጎ ከመጉዳት ውጪ የሚያመጣው አንዲት ነገር የለም፡፡
 
በአለም መድረክ እውቀና ከአሁኑ የተነፈገው ሐገራዊ ምርጫ ውጤቱ ሲጠናቀቅ፤ በማግስቱ በአዲስ መልክ የሚመጡት ሚኒስትሮችም ሆነ የክልል ፕሬዝዳንቶች በአብይ አህመድ በጣም የሚደገፈውን የብርሐኑ ነጋን የዜግነት ፖለቲካ እንዲያሳልጡ የማድረግ ስራ ይሰራል፡፡ ጎን ለጎን ደግሞ የቡድን እና የብሄር ብሄረሰቦችን መብት የሚያስከብረውን የብሄር ብሄረሰቦች ህገመንግስት እና ብሔርን መሰረት ያደረገው የፌደራል ስርዓቱ እንዲጠፋ የሚደረግ እና በምትኩ በዜግነት ስም ልሙጥ ኢትዮጵያን የመገንባቱ ስራው በሁሉም አቅጣጫ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ይህንን በህግ እና በፖሊሲ ደረጃ የሚያስተሳስር ህገመንግስት እና ለአስተዳደር በሚያመች መልኩ የምድር አቀማመጥን መሰረት ያደረገ የፌደራል ስርዓት የሚዘረጋ ይሆናል፡፡
 
አሁን ላይ በብልጽግና ውስጥ የሚገኙ በብሄር ላይ ተንጠላጥለው ስልጣን ያገኙ በሙሉ እንዲሳንፈፉ እየተደረገ በስተመጨረሻ ከአይን የሚጠፉበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ በአሁኑ ወቅት በፌስቡክ ላይ እና በየመድረኩ አትያዙን ልቀቁን በማለት የሚደነፉ ሹመኞች ሁሉ ስልጣናቸው በእርግጠኝነት እስከ ምርጫ ብቻ የሚቀጥል ነው፡፡ ስለዚህ ምርጫው እንደተጠናቀቀ ነባር ባለስልጣኖች በሶስት አመት ውስጥ በነበራቸው የመታዘዝ እና የአቋም ሁኔታቸው እየታየ እና እየተገመገመ ሂሳብ በአንባገነኑ መሪ ያወራርዳሉ፡፡ እንደሚታወቀው አምባገነን መሪ ለብዙ ግዜ ሰዎችን በስልጣን ላይ ማቆየት ስለማይፈልግ የሚተርፍ የአሁን ሹመኛ ይኖራል የሚል እምነት የለም፡፡
 
ማሳሰቢያ፡ ከላይ ያለው ጹሁፍ ትግራይ ክልልን አይመለከትም፡፡ ትግራይ በቅርቡ እራሷን ከወረሯት ነጻ በማውጣት በህገመንግስቱ አንቀጽ 39 መሰረት ህዝባዊ ውሳኔ በክልሉ ህዝብ (referendum) በማድረግ እና ውጤቱን ለተባበሩት መንግስታት (UN) አቅርባ በማጸደቅ ነፃ ሐገር ትሆናለች!! አብይ አህመድም ብዙም ላለመጨቃጨቅ ባላየ የሚያልፈው ጉዳይ ይሆናል፡፡