በቡራዩና አካባቢው በተከሰቱ ግጭቶች የሰዎች ሕይወት ማለፉ ታወቀ

በቡራዩና አካባቢው በተከሰቱ ግጭቶች የሰዎች ሕይወት ማለፉ ታወቀ

በቡራዩና አካባቢው በተከሰቱ ግጭቶች የሰዎች ሕይወት ማለፉ ታወቀ

(ethiopianreporter)–በቡራዩና አካባቢው ባሉ ከተሞች በደረሰ ብሔርን መሠረት ያደረገ ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፣ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ዜጎችመፈናቀላቸዉ ታወቀ፡፡

ከሐሙስ መስከረም 3 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በተፈጸመዉ ጥቃት በዋናነት የጋሞ ፣ የወላይታ፣ የጉራጌና የስልጤ ብሔር ተወላጆች ጥቃት እንደደረሰባቸዉሪፖርተር ያነጋገራቸው ተጎጂዋች ገልጸዋል፡፡

ጥቃቱም በዋናነት በቡድን ይንቀሳቀሱ በነበሩ ወጣቶች መፈፀሙን ተጎጂዋች ለሪፖርተር ተናግረዎል፡፡

በጥቃቱም እስካሁን በርካታ የተገደሉ ዜጎች አስከሬን መነሳቱንና አሀዙም ከዚህ በላይ ሊያሻቃብ እንደሚችል ከተጎጂዎች አንዱና የተጎጂዋቹ አስተባባሪ የሆኑግለሰብ ለሪፖርተር ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ሴቶች መደፈራቸውንና ንብረቶች መውደማቸውን ከተለያዩ ምንጮች ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ጥቃቱን ተከትሎ በርካቶች ከቡራዩ ተፈናቅለውወደ አዲስ አበባ እንደመጡና በተለያዩ ስፍራዎች ተጠልለው እንደሚገኙ ምንጮች ለሪፖርተር አስታውቀዋል፡፡

በዋናነትም በአስኮ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን፣ በአካባቢው ባለ ቃሌ በሚባል ትምህርት ቤትና ቀይ መስቀል በሠራቸዉ ጊዜያዊ መጠለያ ድንኳኖች ተጠልለዉይገኛሉ፡፡

በተጨማሪም ወደ 200 የሚሆኑ ሴቶች፣ ሕፃናት፣ አዛውንቶችና እመጫቶች ከሰላም ሠፈርና ሙገር አካባቢዋች ተፈናቅለዉ ታጠቅ ሠፈር አካባቢዎች ተጠልለውእንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል፡፡

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንዳስታወቁት ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት በጋራ ሰላም ለማስመለስ እየሠሩ ነው፡፡ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ውይይት መደረጉንም ተናግረዋል፡፡ ኃላፊው የሞቱ ሰዎች ምን ያህል እንደሆነ በውል እንደማይታወቅም ገልጸዋል፡፡

ከዚህም ጋር በተያያዘ መፈናቀሉ አሁንም እንዳልቆመና ተጨማሪ ቁጥር ያላቸዉ ተፈናቃዮች በመከላከያ ሠራዊት አባላት ታጅበዉ ወደ አዲስ አበባ እየተጓዙመሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ከውይይት በኋላ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀዬያቸው ለመመለስ አስቀድመው የተስማሙ ቢሆንም፣ ሐሳባቸውን ቀይረው ከአካባቢው እየወጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማና ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በመጠለያቸው በመገኘት ተፈናቃዮቹን ጎብኝተዋል፡፡