በቅማንት ሕዝብ ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ግፎች

በቅማንት ሕዝብ ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ግፎች

ከሚያዚያ 05/2013 ዓ ም ጀምሮ በቅማንት ሕዝብ ላይ እየፈጸሙበት ያሉ ግፎች ተቆጥረው አያልቁም። የሚከትውሉትን ብቻ አቅርበናቸዋል።
1.መከላከያው የአማራ ልዩ ሀይል፣ የአማራ ፋኖና ሚሊሻን ህገወጥነት መቆጣጠር አለመቻሉ ብቻ ሳይሆን ሽፋን እየሰጠ መሆኑ፡፡
 
2.አይከል ከተማ ውስጥ ያለው ልዩ ሀይልና የኤርትራ ወታደር በየቀኑ ንፁሃን ቅማንቶች ላይ ግድያ ሲፈፀም እያየ መከላከያው “ትንኮሳ የፈፀመው ቅማንት ነው” በሚል የተሳሳተ መረጃ እየሰጠ ይገኛል፡፡
 
3.አይከል ሆስፒታል መድኀኒት፣ የርዳታ ቁሳቁስ እንዳይገባ ከመከልከል ባሻገር የሠራተኞችን ደመዎዝ በመከልከል ሠራተኛው ጥቅሜ አልተከበረም በሚል አመፅ በማንሳት ሆስፒታሉ እንዲዘጋ አጠንክረው እየሠሩ ናቸው።
 
4. የሀገር ሽማግሌዎች ህዝብን ወክለው ለመከላከያ የሚያቀርቡት ሐሳብ ተቀባይነት አጥቷል።
 
5.#ኮለኔል_ሽጉጤ በአማራ ክልል መንግሥት በኩል ኮብራና የግል ጠበቂዎች፣ የጦር መሳሪያና ሙሉ ሎጀስቲክ ተሰጥቶት አንድ የገዳይ ቡድን/Murder Squad/ ይዞ በተመረጡ ግለሰቦች ላይ ጥቃት ለመፈፀም እየሠራ ነው።
 
6.ት/ቤት፣ ባንክ፣ ጤና ጣቢያ፣ የመንግስት ተቋማት፣ ውሃ፣ ስልክ፣ መብራት የመሳሰሉ ማህበራዊ ግልጋሎቶች አይከል ውስጥ ዝግ ናቸው።
 
7.አይከል ቀበሌ 01 እና 02 በአስፓልት መንገድ በኩል አደጎ መገናኘት አልተቻለም፣ ምክንያቱም የኤርትራ ወታደር ከልዩ ኃይሉ ጋር ሆኖ እሜቴ አይከል ሚባል ቦታ ላይ ኬላ ጥሎ ሰውና ተሽከርካሪን አልሞ እየመታ ስለሆነ ነው።
 
8.በመንግስት ታጣቂ ቡድን የታፈኑ ወገኖች እስካሁን አልተለቀቁም። ህልውናቸውም አደጋ ላይ ነው።
 
9.ለተፈናቀሉ፣ ለቆሰሉ፣ ለሞቱ ሰዎች በመንግሥት በኩል ምንም ዓይነት የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ አልተደረገም።
 
10.ሚዲያ እንዳንጠቀም ተከልክለናል።
 
11.ከግንቦት 16/2013 ጀምሮ ጎንደር ከተማና ዙሪያው ላይ በቅማንት ሕዝብ የክልሉ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና የጎበዝ አለቃ ዘረፋ፣ ጭፍጨፋ፣ ግድያና አፈና እየተፈፀመ ነው።
 
12. ጫንቅ አካባቢ በ18/09/13 በርካታ የቅማንት ቤቶች ተቃጥለዋል።
 
13.የኤርትራ ወታደሮች ወደ ጎንደር የገቡት DART ወደ ትግራይ የገባ ጊዜ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ሆኖም ከዛ ጊዜ ጀምሮ ወደ ቅማንት ቀጠና በመግባት ትግራይ ላይ የፈፀሙትን ግፍ በቅማንት ላይ እየፈፀሙ ነው።
 
14. በተወሰን የቅማንት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላትን ላይ ርምጃ ለመውሰድ መከላከያው ፎቶግራፍ በእጁ ይዞ የመለየት ሥራ እየሠራ ነው፡፡
 
15. መደበኛ ታካሚም ይሁን ቁስለኛ ጎንደር ሆስፒታል ውስጥ መታከም አልቻለም፣ ቅማንት የሆኑ የጎንደር ሆስፒታል ሰራተኞች በመንግሥት ቀጥተኛ ትዕዛዝ እየተሳደዱ መሥራት አልቻሉም፡፡
 
16. ከሚያዚያ 10 ጀምሮ ቁስቋም ወደ 25 ሞተር እና 3 ሰዎችን አሥረዋል። በ14/09/13 ቁስቋም ላይ የታጠቀ የመንግሥት ታጣቂ የገበሬዎችን እንስሳት የገቢያ መንገድ ላይ ጠብቀው ዘርፈዋል። ለገቢያ የወጡ ሰዎችን ከተሽከርካሪ እያስወረዱ ሞባይል፣ ገንዘብ ፣ ንብረት ዘርፈዋል። ቆይተው ተጨማሪ ሁለት ሞተሮችንም ዘረፉ።በአጠቃላት የጎንደር ከተማ የቁስቋም ነዋሪ የቅማንቶ ሙሉ በሙሉ አካባቢውን ለቀው ተሰደዋል።
 
አሁን ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ዝርዝር ጉዳዮችን ስናይ፡-
☞ቁስቋም ከ100በ በላይ ቤት ተቃጥሏል።
☞ቤታቸው ውስጥ የነበሩ ህፃናት፣ሴቶች ፣አረጋውያኖች ተቃጥለዋል።
☞ጎንደሮች ጊዮርጊስ፣ ጫንቅ፣ ቁስቋም፣ ቀበሌ 15፣ ቃሃ ዙሪያ፣ ወለቃና ፈጭፋጪት ተመሳሳይ ድርጊት ተፈፅሟል።
☞ መከላከያ የቅማንት ህዝብን መኖሪያ ሠፈሮች በከባድ መሳሪያ እየደበደበ ያስለቅቃል፣ ዘራፊው ቡድን ተከትሎ ይዘርፋል፣ ፋኖ፣ ልዩ ኃይል፣ የኤርትራ ወታደር ይገድላል፣ ቤት ያቃጥላል፡፡
 
☞ እስካሁን ያልተነሳ አስክሬን በየቦታው ወድቆ ይገኛል።
በአጠቃላይ በቅማንት ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ከትግራዩ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ጋር ልዩነት የለውም፡፡ ያልፈፀሙት በድሮን፣ በሄሌኮፍተርና በሚግ ድብደባውንና ነጭ ፎስፎረስ መተኮስን ብቻ ነው። እነዚህንም ለመፈፀም በዝግጅት ሂደት ላይ ናቸው፡፡