በሼህ አላሙዲን ላይ የመጀመሪያው ዙር ምርመራ በአሜሪካኖችና ሳኡዲ ደህንነቶች ተጀምሯል

  Ethiopia : በሼህ አላሙዲን ላይ የመጀመሪያው ዙር ምርመራ በአሜሪካኖችና ሳኡዲ ደህንነቶች ተጀምሯል። በማንኪያ ሰጥቶ በአካፋ የሚቀበለው ሰው ሼህ መሐመድ አላሙዲን ከዘረፋ ጎን ለጎን የአሜሪካ የስለላ ድርጅትና የሳዑዲ ንጉሳውያን ቤተሰቦች የስልጣን ሽኩቻ የአሜሪካ ሪፑብሊካኖችና ዲሞክራቶች ግብግብ ተጠቂ መሆናቸው ታውቋል። በሙስና የታሰሩት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከሕወሓት ኤፈርት ቀጥሎ በሞኖፖል የያዙት ሼህ አላሙዲን የፖለቲካ ጥያቄ መጠየቃቸውን ወንድማቸው ሸህ ሀሰን ባሁሴን አሊ አልሙዲ የሜድሮክ ግሩፕ በሳኡዲ አረቢያ ሃላፊ ወንድሙን ሼህ አላሙዲንን ካነጋገረ በኋላ ገልጿል።

ሼሁ የሳኡዲ መርማሪዎች መንግስት የመቀየር ሴራ ተሳትፎና በሙስና ቡኩል ያለውን ጥያቄዎች ሲያዋክቧቸው አሜሪካኖቹ በፖለቲካና በሽብርተኝነት ዙሪያ ጥያቄዎችን እንደጠየቋቸው ለወንድማቸው ሸህ ሀሰን ባሁሴን አሊ አልሙዲ ነግረውታል። ሼህ አላሙዲን ለታናሽ ወንድማቸው የነገሩት እኔን እና ጠላል ቢን ወሊድ በሄላሪ ኪልተን ምርጫ ላይ አንተ እጅቹ አለበት ወይ ድጋፍ አድርገሀል ወይ የሚል ጥያቄ ነው የጠየቁኝ ብለውታል። እንዲሁም በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ያላቸውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ በተመለከተ ምርመራ ተደርጎባቸዋል። ሸሁ ለወንድማቸው ሙስና ያሉት የሕዝቡን አመለካከት ለመቀየር እንጂ በራሳቸው የፖለቲካ ሽኩቻ ተጠቂ ሆኛለሁ ሲሉ በሳዑዲ መንግስት ላይ አማረው ተናግረዋል ሲል ታናሽ ወንድማቸው ሲናገር ተደምጧል።

ሌላው የሼሁ የባንክ አካውንት በከፊል ዛሬ ተከፍተዋል ለማስረጃ ያህል ነፍት የሚባለው የቤንዚል ማደያቸው በቀን ከሁለት ሚሊዮን ሪያል በላይ በሁሉም የሳኡዲ ግዛቶች ለባንክ ገቢ ሲያደርጉ የነበሩት ለሰባ ሁለት ሰአት በመዘገጀታቸው በሀገሪቱ በአሁኑ ሰአት የስራ እንቅስቃሴ በወደቀበት ጊዜ የሼሁ በነፍት የሚገኛው ገቢ በትናንሽ ከተሞች ላይ ተፅኖ በመፍጠሩ የብዙ ድርጅቶች ባለቤት ከዓርባ በላይ የሚሆኑ ካምፖኒዎች ሂሳብ መዝጋት ድሮም በደንብ ያልታሰበ ሰለነበር ዛሬ ተከፍቱዋል ከነዛም ውስጥ ነፍት እና ኤቢቪ የሚባሉት በሳኡዲ የሚገኙ ድርጅቶቹ ገንዘባቸውን ሲያንቀሳቅሱ መዋላቸው ለምንሊክ ሳልሳዊ ከሰራተኞች የተገኘ መረጃ ጠቁሟል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የታሰሩት ሰዎች ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በማፍሰስ የራሳቸውን ደህንነቶች ማሰማራታቸው ሲታወቅ ከነዚህ ውስጥ የሼህ አላሙዲን ሰዎች ኢትዮጵያውያንን በገንዘብ በመደለል ለስለላ እና ለቅስቀሳ ማሰማራታቸው ምንጮቹ ይናገራሉ። እንዲሁም ጎን ለጎን የሳዑዲ ደህንነት ቢሮ ኢትዮጵያውያን በገንዘብ ገዝቶ በሼህ አላሙዲን ድርጅቶች እና የቅርብ ሰዎችና ሰራተኞች ላይ ማሰማራቱን ምንጮቹ ይናገራሉ።

ከግብጽ ሚዲያዎች የሚሰማው ዘገባ ደግሞ የሚገርም ሆኗል። የግብጽ አረቢኛና እንግሊዘና ሚዲያዎች አላሙዲን በመቶ ሺህ ሚሊዮኖች ለዓባይ ግድብ ስለሚረዳ መታሰሩ ለግብጽ ጉሮሮ መከፈት ምልክት አድርገው በመዘገብ ላይ ናቸው። በሸሁ መታሰር ደስታቸውን እየገለፁ ነው።ይህ ማለት በአባይ ግድብ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሲረድ እንደነበር መረጃው እንዳላቸው የሚሊየነሩ መታሰር በአባይ ግድብ ላይ አሉታዊ ተፅኖ ያመጣል ብለው ያስባሉ።

MinilikSalsawi