በሻሸመኔ በተማሪዎች ላይ መንግስት እየፈፀመ ያለው አረመኔያዊ ተግባር

በሻሸመኔ በተማሪዎች ላይ መንግስት እየፈፀመ ያለው አረመኔያዊ ተግባር ቤተሰቦችን ጭንቀት ላይ ጣለ

አባይ ሚዲያ ዜና
ናትናኤል ኃይለማርያም

ሻሸመኔ በሚገኘዉ ሉሲ ትምህርት ቤት ዉስጥ ያሉ ተማሪዎች በወያኔዉ የአፈና ቡድን ተይዘዉ ሰቆቃ እየተፈፀመባቸዉ መሆኑን ከስፍራዉ የተገኘዉ መረጃ ያስረዳል። ተማሪዎቹ የታፈኑበት ዋና ምክንያት ተደርጎ የተወሰደዉ የሕዉሐት ገዥዉ መደብ ያወጣዉን የኮማንድ ፖስት አዋጅ በመቃወም ያለ ፈቃድ ስብሰባ ማድረጋቸዉ ሲሆን ከዚሁ ጋርም ተያይዞ ተማሪዎቹ ጥቁር ካኒቴራ በመልበስ እና ኮከብ የሌለዉን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በመያዛቸዉ እንደሆነ ታዉቋል።

ዚህ ፀረ ሕዉሐት ስብሰባቸዉ የለበሱት ካኔቴራ ገዥዉን ሕዉሐትን የሚያወግዝ መልዕክት እንዳለዉ ታዉቋል። የተለመደዉ የሕዉሐት የሃሰት ክስም ለነዚሁ ተማሪዎች የተሰጠ ሲሆን ተማሪዎቹን በራሪ ወረቀቶችን በመበተን ተማሪዉን በመቀሰቀሳቸዉ እና በሕቡዕ ለሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ተልዕኮ አስፈፃሚዎች ናቸዉ በማለት መወንጀሉ የደረሰን ሪፖርት ያሳያል።

(abbay Meadia) -በሻሸመኔ የሉሲ ተማሪዎች ላይ የሕዉሐት የደህንነት ክፍል እየወሰደ ያለዉ ኢሰብዓዊ ድርጊት ወላጆችን በእጅጉ ያሳሰባቸዉ እንደሆነ እና ለማን አቤት እንደሚሉ ስለጨነቃቸዉ የልጆቻቸዉን ጉዳይ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ ባሉበት ቦታ ለሚመለከተዉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም ሆነ ጉዳዩ ለሚመለከታቸዉ መስሪያ ቤቶች አቤት እንዲሉላቸዉ መማጸናቸዉ ክስፍራዉ ተዘግቧል።

ከዚህ ከሚደርስባቸዉ ሰቆቃ በተጨማሪ ተማሪዎቹ ለጤና እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ቦታ ላይ መታሰራቸዉ በጤናቸዉ ላይ ከፍተኛ ችግር ሊገጥማቸዉ እንድሚችል መታወቁ ቤተሰቦቻቸዉ ለከፍተኛ የስነ ልቦና ቀዉስ እንደተጋለጡ ለመረዳት ተችሏል።</p>
<p>የሕዉሐት ደህንነት ገና ታዳጊ የሆኑትን ሕፃናት በዘር እየለየ ጥቃት እያደረሰም መሆኑ ሲታወቅ የዚህ ጥቃት ሰለባ የሆኑት አብዛኞቹ የኦሮሞ፤ የአማራና የጉራጌ ተወላጅ ልጆች እንደሆኑም ታዉቋል። ሕዉሐት እድሜና ፆታ ሳይለይ በዜጎች ላይ እየወሰደ ያለዉ ሰቆቃ ያለበት አጣብቂኝ ከምንጊዜዉም በበለጠ ማጠፊያ እንዳጠረዉ ያሳያል ሲሉ አንዳንዶች ለዝግጅት ክፍላችን አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሕዉሐት ባለስልጣናት በታሰሩት ተማሪዎች ቤተሰብ ላይ የተለያየ የሙስና ወንጀል እየፈፀሙባቸዉ መሆኑም ታዉቋል።