በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስና ሚሊሺያዎች አማካኝነት የሚደርሱ ጥቃቶች አሁንም አልተቋረጡም

በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስና ሚሊሺያዎች አማካኝነት የሚደርሱ ጥቃቶች አሁንም አልተቋረጡም

አራት ሰው ሞቷል – በየቀኑ ሰዎች እየተገደሉ ነው :
– “በየቀኑ የአካል ጥቃት እንደሚደርስና ግጭቱ የሰዎችን የዕለት ተዕለት ግንኙነት በማበላሸቱ በከተማ ውስጥ ለብቻ መንቀሳቀስ አስፈሪ ሆኗል:: ” የሞያሌ ነዋሪዎች

– “በዚህ ሣምንት ብቻ አራት ሰው ሞቷል ፤ እንደ ጤና ጣቢያና ትምሕርት ቤት ያሉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በተወሰኑ ቀበሌዎች ውስጥ ተዘግተዋል።” የባቢሌ ነዋሪዎች

– “በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስና ሚሊሺያዎች አማካኝነት የሚደርሱ ጥቃቶች አሁንም አልተቋረጡም በየቀኑ ሰዎች እየተገደሉ ነው” በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ድንበሮች ላይ በሚገኙ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች

“በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስና ሚሊሺያዎች አማካኝነት የሚደርሱ ጥቃቶች አሁንም አልተቋረጡም ” ሲሉ ነዋሪዎች አማረሩ:: በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ድንበሮች ላይ በሚገኙ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች፤ “በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስና ሚሊሺያዎች አማካኝነት የሚደርሱ ጥቃቶች አሁንም አልተቋረጡም በየቀኑ ሰዎች እየተገደሉ ነው” ሲሉ አማረሩ።

በምስራቅ ሐረርጌ ባቢሌ ከተማ በዚህ ሣምንት ብቻ አራት ሰው እንደሞተ ገለፀው እንደ ጤና ጣቢያና ትምሕርት ቤት ያሉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በተወሰኑ ቀበሌዎች ውስጥ መዘጋታቸውን ጠቁመዋል።

በሞያሌ የሚገኙ ነዋሪዎችም በበኩላቸው በየቀኑ የአካል ጥቃት እንደሚደርስና ግጭቱ የሰዎችን የዕለት ተዕለት ግንኙነት በማበላሸቱ በከተማ ውስጥ ለብቻ መንቀሳቀስ አስፈሪ መሆኑ ተናግረዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት የኦሮሚያም ሆነ የሶማሌ ክልል ባለሥልጣናትን ለማግኘት አልቻልንም።

የከተማዎቹ የቀበሌ መስተዳድር ኃላፊዎች ግን ሁኔታው አሁን ካለው የከፋ መልክ ሳይዝ አፋጣኝ መፍትሔ ሊፈለግለት ይገባል ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።


Ethiopia ለሕዝብ ያለውን ንቀት በተደጋጋሚ ያሳየው አደገኛው የሕወሓት/ኢሕአዴግ አካሔድ ፦ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዴ መሐመድ ኢሌ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የኦሮሞ ልጆች መፈናቀል ፣ ለበርካቶች መገደል ፣ መታሰርና መሰደድ በዚህ ሰሞን ደግሞ የ104 አመት ዕድሜ ባለፀጋ ለሆኑ አዛውንት መገደል ፣ ለኢትዮጵያዊያን ሶማሌዎች በረሐብ መሰቃየት እና የፖለቲካ ሰቆቃ ተጠያቂ የሆነ ግለሰብ በአደባባይ መሸለም ኢሕአዴግ ለሕዝብ ያለውን ንቀት በገሀድ ያሳየበት ነው ። ወንጀለኞችን መንከባከብ ልምዱ ያደረገው የወያኔ ስርዓት ንፁሀንን ወንጀለኛ አድርጎ ማሰር ደግሞ የየእለት ስራው ነው ። ለፍርድ መቅረብ ያለባቸውን አደገኛ አመራሮቹን መሾምና መሸለም የአሸባሪው ኢሕአዴግ አደገኛነት ምስክር ነው ፤ ሕዝብን መናቅ ዋጋ ያስከፍላል ።

MinilikSalsawi


Ethiopia : የካሳንቺሱ አውራ እንደሚለው ከሆነ ሊ`በሉ የታቀዱ የሕወሃት የብዓዴን እና የኦሕዴድ ሰዎች እየተለዩ ነው። በጌታቸው አሰፋ የሚመራው የደህንነት ቢሮ ኮቴያቸውን ብሎ የሚጥላቸው ነባር ታጋዮችና የድል አጥቢያ አርበኞች ተለይተው በዝርዝር እንዲቀርቡ ቀጭን ትእዛዝ ተላልፏል። ከሃገር እንዳይወጡ ኤርፖርት ላይ የሚታገቱ ሁሉ ይፈለጋሉ። ይህ ብቻ አይደለም የሚፈታውን የፖለቲካ እስረኛ እጥፉን ወደ እስር ቤት ለማጋዝ ታጥቀዋል ፤ ተጨማሪ እቅዶች ከፍተኛ የሆነ እልቂት በየክልሉ ተደግሷል። የተለመደው የእርስ በርስ ማጋጨት በስፋት እንዲካሔድ ለነ አማኑኤልና አዲሱ በዳዳ ሚሽን እየተነደፈላቸው ነው። አዳዲስ የደህንነት ሰልጣኞች ከየክልሉ ተመልምለው በጥሩ ክፍያ እየተዘጋጁ ነው።ለሕዝብ እየተደገሰለት ነው። ሕዝብ በንቃት መቆየት ይጠበቅበታል።

የእስራኤልና የፍልስጤም ደጋፊ ነን ያሉ የሐገሬ ልጆች በሰው ለቅሶ ፍራሽ እየተጓተቱ ነው። የፍልስጤማውያን ጥያቄ የመብትና የነጻነት ጥያቄ ነው። የእስራኤላውያኑ ጥያቄ ደግሞ እነሱ እንደሚሉት ነው ። ሁለቱም አንዱ ላንዱ አይተኛም። እኛ ጋር ስንመጣ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጸምባት በሰብዓዊ ቀውስ ከሶሪያ ቀጥላ የምትጠራ እናት አገራችን የልጆቼ ያለህ ትላለች።

MinilikSalsawi