በስላማዊ መንገድ ተቋውሞ የሚያደርጉን ዜጎች የታጠቁ የመንግስት ኃይሎች የሚፈፅሙትን ድብድባ እና ግድያ ኦነግ ያወግዛል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር መግለጫ 11/02/2021 ዓም

በስላማዊ መንገድ ተቋውሞ የሚያደርጉን ዜጎች የታጠቁ የመንግስት ኃይሎች የሚፈፅሙትን ድብድባ እና ግድያ ኦነግ ያወግዛል
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር መግለጫ 11/02/2021 ዓም
 
በየካቲት ወር መጀመሪያ የብልጽግና ፖርት ሕብረተሰቡን በማስገደድ ለዶ/ር አብይ አህመድ የድጋፍ ስልፍ እንዲያካሂድ መደረጉ ይታወሳል. ይህ ስልፍም በመንግስት የታጠቁ ኃይሎች በመታጀብ በስላም እንድጠናቀቅ ተደርጓል። ይሁን እንጂ በመገደድ ዶ/ር አብይ እንድደግፉ የተደረጉ እና አሉታው መልስ የስጡ ዕጣ ፋንታቸው መገደልና መደብደብ ሆኖ ነበር. እንዴምሳሌ ለመጥቀስ ያህል የካቲት 02 ,2021 ዓም በምሥራቅ ሐረርጌ ጨለንቆ ከተማ በማስገደድ በተሽከርካሪ ይዘው እየተጎዙ በመገለበጡ የ45 ወጣቶች ሕይወት አልፋል።
ይህ በእንድሁ እያለ፣ በአሁኑ ስዓት በኦሮሚያ የኦሮሚያ ዜጎች በስላማዊ መንገድ የተቋውሞ ስልፍ እያደረጉ ያሉትን የመንግሥት የታጠቁ ኃይሎች በመሳሪያ አፈሙዝ እንድታገት እያደረጉ ይገኛሉ።
 
ከየካቲት 05/2021 ጀምሮ የኦሮሚያ ዜጎች የኦሮሚያ የሽግግር መንግሥት ምስረታን በመደገፍ ,፣የኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች ጥያቄ እንድመለስ እና በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ እና እስራት እንድቆም ስላም እና ዲሞክራሲያዊ መብት እንዲከበር በመላው ኦሮምያ ስልፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። እየተካሄደ ባለው ስልፍም የኦሮሞ ወጥቶች ያለምንም ትንኳሳ ስላማዊ በሆነ መንገድ እያካሄዱ መሆኑ በገሃድ የሚታይ እውነት ነው.። ይሁን እንጅ የብልጽግና ፓርት ቡድን የሆነው የታጠቀ ኃይል ድብደባ፣ግድያ እና ለከፍተኛ የአካል ጉዳት እየዳረገ መሆኑን ያለን መረጃ በገሃድ ያመለክታል። ከግድያ እና አስቃቂ ድብደባ ባሻገር በጥይት የተመቱ ቁስለኞች ጭምር በጅምላ ታፉስው በእስርቤት እየታጎሩ ናቸው.፣ብዙዎች ለዚህ መስል ጥቃት የተዳረጉ ስሆን እስካሁን ባገኘነው መርጃ ፣
 
1. አቶ ዲቃ ዳባሶ የካቲት 08/2021 በነገሌ ቦረና, ያበሎ በመንግስት የታጠቁ ኃይሎች የተገደለ፣
2. የካቲት 10/2021 በድሬዳዋ 3 ወጣቶች በታጠቁ የመንግስት አካላት በጥይት ክፉኛ ቆስለዋል ። እነዚህም,
1. ዳቻስ ሁሴን
2. ፎሃድ መሐመድ
3. 3.ናስማ ያያ
 
3. አቶ ገዳ ገብሳ የኦነግ መኮንን የሆነው በመንግስት የታጠቁ ኃይሎች በፊንፊኔ የምርጫ ቅስቀሳ ሂደት ላይ ከስልጠና ስመለስ ይተይዞ ያለምንም ጥያቄ ቡራዩ እስር ቤት ታስሮ ይግኛል. ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች በሺህ የሚቆጠሩ ንጽሐን ዜጎች በሚታወቁ እና ባልታወቁ እስርቤቶች ታጉረው እያለ በተመሳሳይ ሁኔታ አሁንም ዜጎችን ወደ እስር ቤት ማጎር መደብደብ መግደል ወደ ሀገሪቷን እያመራ እንዳለ ለሁሉም ግልፅ የሆነ መሆኑ አያጠራጥርም።
ኦነግ ይህ በደል ለደርስባቸው ቤተስብ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆቻቸው መፅናናትን ይመኛል. በተለይ ሁኔታ በስላማዊ መንገድ ስልፍ ባደረጉት ወጣቶች ሕይወት እልፈት ደግሞ ሐዘናችን ጥልቅ ነው ፣በፅኑም ይህን ግዲያ እናወግዛለን. የስብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም በተለየ መልኩ ትኩርት ስጥተው እንድያስቆሙ አጥብቀን እንጠይቃለን ።
 
በአሁኑ ስዓት በኢትዮጵያ ስብዓአዊ መብትን ከመጣስ አልፎ ወደ ዘር ማጥፋት ደረጃ እየተዳረስ ያለውን የኦሮሚያ ዜጎች ፣የሀገሪቱ ጭቁን ሕዝቦች እና የዓለም ማህበረሰብ መገንዘብ አለበት። ሀገርቷን እያስተዳደራት ያለው የብልጽግና ፖርት በይስሙላ ምርጫ አምባገነንነቱን ለማረጋገጥ እየጣረ ባለበት ሂደት በስቨል ማህብረሰብ ላይ ሊደርስ የሚችለው ጉዳት እጅግ ያሳስበናል።
 
ኦሮሚያ የአስተዳደር መዋቅሩ ተስባብሮ ፣ ሥርዐት አልበኝነት ስፍኖ በየዕለቱ የዜጎች ሕይወት እየተቀጠፈ ያለበት ሁኔታ ላይ ትገኛለች። ንብረት እየተዘረፈ እና እየወደመ ይገኛል.። የኦሮሚያ ዜጎችም ስላም እና መረጋጋት የተሳናትን ኦሮሚያ የላቀ ስላም እንዲታገኝ የኦሮሚያ ሽግግር መንግስትን በማቋቋም ላይ ይገኛሉ ። ይህን ላለማሳካት እንቅፋት መሆን ሀገሪቱን ወደባስ አቅጣጫ እንደምወስዳት ገዥው ፖርት ማውቅ አለበት ። ኦነግ ሁሉን አቀፍ (all inclusive) የሆነ ዲሞክራሲያዊ ሂደት ግንባታ ለማድረግ ሕብረተስቡን በሚያቀራርብ መልኩ (peace dialogue) እንዲኖር ጥረት እያደረገ እና እየሰራም ነው ።
 
ስለዚህ የኦሮሚያ ዜጎች የኦሮሚያ ሽግግር መንግስት ግንባታን በማጠናከር ሌሎች ጭቁን ሕብረ በሔራዊያን ክልላቸውን በማረጋጋት የፈረስውን መዋቅር መልስው መገንባት ላይ አትኩረው እንድስሩ እናሳስባለን።
ድል ለስፊው ሕዝብ !
 
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
ፊንፊኔ/የካቲት 12/2021
ABO