በሱዳን ትራንዚሽን እና ኮቪድ በአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚ ላይ ያሳደረው ተፅእኖና መፍትሄዎቹ ላይ የሚመክር ታላቅ የመሪዎች ስብሰባ በፓሪስ እየተካሄደ ነው።

በሱዳን ትራንዚሽን እና ኮቪድ በአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚ ላይ ያሳደረው ተፅእኖና መፍትሄዎቹ ላይ የሚመክር ታላቅ የመሪዎች ስብሰባ በፓሪስ እየተካሄደ ነው።

የግብፅና የሱዳንን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ መሪዎች በተገኙበት በዚህ ስብሰባ ላይ ጠሚ አብይ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ልከው ሳይገኙ ቀርተዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትና የኢኮኖሚክ ኮሚሽን መቀመጫ እንደመሆኗ ጠሚው በመሰል አለም አቀፍ መድረኮች ላይ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ቢቻል አፍሪካን ወክለው የምእራባውያንን ድጋፍ መጠየቅ ነበረባቸው። ሆኖም የአለም አቀፍ ማህበረሰቡ ውግዘት እረፍት የነሳቸው ጠሚው ኢትዮጵያን እንኳን ወክለው ለመሳተፍ ፍላጎት አላሳዩም።
 
ዲፕሎማሲ የአለም አቀፍ ጋዜጦች ላይ ከሜትድራንያን ማዶ op-ed በመፃፍ ብቻ አይሰራም። የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ምክትል መልእክተኛ ፔይተን ኖፕፍ በአንድ ፓነል ላይ ሲናገር “አብይ በአካል ካናገራቸው የምእራብ ሀገር መሪዎች ይልቅ በጋዜጣ ላይ ያፃፈው ኦፔድ በቁጥር ይበልጣል” ብሎ ነበር (https://bit.ly/33SMwNX)።
 
በአንድ ወቅት የአራት ኪሎ ጥሩ ፎቶግራፈር በመሆን ያገለገለው አምባሳደር ፍፁም አረጋም ኒው ዮርክ ታይምስና ዋሺንግተን ፖስትን እንደ መንግስት ፕሮፓጋንዳ አውትሌት ለመጠቀም ቢመኝም ፅሁፌን አትሙልኝ በሚል ውትወታው የተሰላቹት ኤዲተሮች እባክህ ተወን ብለውታል። በዚህ ተስፋ ያልቆረጠው አምባሳደሩ ብዙም ተደራሽነት የሌላት የጦማር ገፅ Medium.com ላይ በራሱ ስም ከፍቶ በመንገታገት ላይ ይገኛል። ሌላው በጡረታ መልክ የተመደበ ዲፕሎማትማ ይህን ያህልም የመሞከር አቅም የለውም። የኦፔድ ዲፕሎማሲው ብዙ አላራመደም።
 
ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ማህበረሰቡ ዘንድ ወደ ተገለሉት ኤርትራ ወይም ወደ የአልበሽር ዘመኗ ሱዳን ደረጃ ዝቅ ብላለች። ኢሳያስ የሚሰራውን ያውቃል። ዋና አላማው ሀገሪቱን አዳክሞ የቀጠናው ዋና ፓወርብሮከር መሆን ነበር። በተወሰነ መልኩም ያንን አሳክቷል። ምእራባውያኑ አሁንም ቦታ ባይሰጡትም በግድቡ እሰጣ ገባና ሌሎች ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ዋና አደራዳሪ በመሆን በካይሮ ካርቱም አቡዳቢና ሞቃዲሾ shuttle diplomacy ተጠምዶ ቆይቷል። ለዚህ አገልግሎቱ ጠቀም ያለ የነዳጅ ገንዘብ ከአቡዳቢ ወደ አስመራ ካዝና ገቢ መደረጉ ብዙ አያጠራጥርም። ነገር ግን ይህ ስኬት ብዙ የሚያስኬድ አይሆንም። ጄፍሪ ፌልትማን የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከኢሳያስ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያቀዘቅዙት ግፊት ለማድረግ ማሰቡን ፍንጭ በመስጠቱ ኢሳያስና ኤርትራ ወደ ነበሩበት መገለል ከመመለስ አይድኑም።
ካርቱም ጨዋታውን እያሸነፈች ይመስላል። አሜሪካና አውሮፓ የቀጠናው አዲሷ ዳርሊንግ ሱዳን መሆኗን ማወጃቸው ያበሳጨው የኤርትራው ቃል አቀባይ የማነ ገብረመስቀል (ትሮል ቢባል ይቀላል) ሰሞኑን ትዊተር ላይ ዛቻ መሰል ቢጤ ወደ ሲዳን ሰንዝሯል። የሚያሳዝነው ኢትዮጵያም ካልጠፋ ምሳሌ በደመነፍስ የኢሳያስን ዱካ ተከትላ ተያይዛ የቀጠናው ውራ መሆኗ ነው። ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ እንደሚባለው (ለተረቱ ሃፉ በሉኝ ግርማዊነታቸውና አድናቂዎቻቸው ጨዋታ በተረት ካልተዋዛ አይመቻቸውም በሚል ነው)።
 
ለማንኛውም ለማሳረግ ያህል የገንዘብ ተቋማት ጭምር በሚገኙበት በፓሪስ አፍሪካን የተመለከቱ ቁልፍ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ውይይት በሚካሄድበት በዚህ ሰአት ኢትዮጵያ በመሪ ደረጃ አልተወከለችም። በምትኩ ጠሚው በሚኒልክ የግብር አዳራሽ ግድንግድ ፖስተር አሰርተው የአረንጓዴ አሻራ ቀንን እያከበሩ ነው። የሚነገረን ቁጥር የተቀሸበ ባይሆን ዛፍ መትከሉ ባልከፋ ነበር። ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል ያለፈው አመት የዛፍ ተከላ ማገባደጃ ላይ በዚህኛው አመት በካርቱም የሚተከሉ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞች እየፈሉ እንደሆነ ጠሚው ነግረውን ነበር። የትኞቹ የካርቱም አካባቢዎች የዚህ መርሃ ግብር ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አያይዘው ቢነግሩን።

1 Comment

  1. Braking news , Demeku mekonen engaged in an increasingly bitter war of words with Colonel Abiy . And people who were present at that moment are predicting they might advance furher in their hostility .
    Nama and mahar party demagogue will eat eachother soon and Sudan will gain power and control the entire Gonder, according to people who know calsh between Abiy and mister Demeku, ex-Abiy telalaki and deviant amhara elites.

    Prof Al Mariam, Zewdu Gebre-Hiwet Roman tesfaye , Ittu Aba Farda , Habte Selassie, henok sheokakaw , Almaz asefa, yetsfa chilanchil, zeregnawi ethiopiawi are all prosperity party (PP)cadres and must be sent to stay behind bars. they are supporting genociders
    ማህበረ ቅዱሳን ተብሎ የሚታወቀው ድርጅት ምርቶችን ከገበያ እንዳትገዙ፥በጥንቆላ የተካኑ ተብታቢዎች ስለሆኑ ተጠንቀቁ፥፥ቦይኮት ማህበረ ቅዱሳን እና ምርቶቻቸውን ሁሉ አትግዙ፥፥ Boycott soccaled Mahibrekiduisan and its products. FYI, Mahibrekiduisan is spying for prosperity party Agency, INSA, and imprisoning Tgeru and other ethnic members with Shabiya agents from Eritrea.

Comments are closed.