በሰሜን ወሎዋ ራያ ቆቦ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ሊሊቱን ሙሉ ከተማዋን ሲንጥ አደረ ። የቆቦ ህዝብ እሰረኞችን ነፃ አወጣ

ሌሊቱን ቆቦ በደፈጣ ታጣቂዎች ስትናጥ አደረች!! የቆቦ ህዝብ እሰረኞችን ነፃ አወጣ

(mereja) ከትላንትና ምሽት 11 ፥00 ጀምሮ በሰሜን ወሎዋ ራያ ቆቦ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ሊሊቱን ሙሉ ከተማዋን ሲንጥ ማደሩን ከስፍራው የሚገኙ የአይን እማኞቻችን ገልጸዋል።

እንደ አይን እማኞቻችን ገለጻ በቆቦ የተካሄደው ህዝባዊ ቁጣና ተቃውሞ በተደራጅ ሁኔታና ሁለገብ እንደነበር ሌሊቱን ሙሉ በመሳሪያ ቶክስ ስትናጥ ማደርዋን አያይዘው ገልጸዋል።

የቆቦው ህዝባዊ አመጽ መነሻውን ከከተማዋ መግቢያ 5ኪሎ ሆርማት እንዲሁም መውጫው 12 ኪሎ ሜትር ዋጃ ላይ መንገዶቹን በተጠናና በተደራጀ ሁኔታ የአጋዚም ሆነ የመከላከያ ሰራዊት እንዳይገባ መንገዶቹ ሙሉ ለሙሉ ከተዘጉ በሁዋላ መሆኑንና በሁለቱም አቅጣጫዎች ወደከተማዋ ለመግባት የሞከሩ የመንግስት ታጣቂዎች በደፈጣ ታጣቂዎች ጥቃት ስለተፈጸመባቸው ወደሁዋልቅ ለማፈግፈግ መገደዳቸውን ምንጫችን አክሎ ገልጾዋል።

በቆቦ ከተማ እከስርአቱ ጋር በማበር ህዝብን ሲያሰቃዩ ነበር የተባሉ የመንግስት ባለስልጣናትና በአካባቢው የሚኖሩ ለስርአቱ መረጃ በማቀበል የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች የጥቃቱ ሰለባ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሎዋል።

በቆቦ ከተማ በተነሳው ህዝባዊ አመጽ የቆቦ ከተማ ማዘጋጃ_ቤት እና ተሽከርካሪዎ እንዲሁም ፍርድ_ቤት በእሳት መውደማቸውንና እስረኞችን ለማስፈታት የተደረገው ብርቱ ጥረት ግን ሊሳካ አለመቻሉን ምንጮቻችን ከስፍራው አያይይዘው ገልጸዋል።

ይህን ዘገባ እስካጠናከርኩበት ግዜ ከተማዋ በህዝብ ቁጥጥር ስር እንደሆነችና ከተማዋ እየተካሄደ የሚገኘው ህዝባዊ ተቃውሞ በተለያዩ ገሩፕ መሪዎች በተጠናና በተደራጀ ሁኔታ መሆኑንም ከመረጃ ምንጮች ለማወቅ ተችሎዋል።

የቆቦ ህዝብ እሰረኞችን ነፃ አወጣ

ለሊቱን ከ 6ግዜ በላይ ተሞክሮ ያልተሳካው የቆቦ እስረኞችን የማስፈታት ዘመቻ በህዝብ ያለተቋረጠ ትግል እስረኞች ነፃ ወጡ፡፡ ቆቦ ሁንም በከፍተኛ የመሳሪያ ተኩስና የእሳት ቃጠሎ እየታመሰች ነው፡፡እሰካሁን 3 የህዝብ ለጆች ሲሰዉ 2 የፌደራል ፖሊሶችም መገደላችው የአይን እማኞቻችን ከስፍራው ገልፀዋል፡፡

ያሬድ Amare


እጅግ ልብ የሚሰብር በጣም አስደንጋጭ አሳዛኝ
ዜና በአሁኑ ስአት የቆቦ ሕዝብ በትግራይ ወንበዴዎች በሒሊኮብተር እየተደበደበ ነው ::

በጣም ከፍተኛ ጉዳት በሰላማዊ ህዝብ ላይ ደርሷን ::
የቆቦ ህዝብ ለመላው ኢትዬጵያውያን አስቸኳይ የድረሱልኝ ጥሪ በማድረግ ላይ ይገኛል እባካችሁ ይህን መልዕክት ሸር በማድረግ ተባበሩ ::

Tilaye Tarekegn ZE Ethiopia

ዛሬ ቀትር ላይ የአጋዚ ወታደሮች በራያ ቆቦ ህዝብ ላይ በኢሊኮፍተር በታገዘ ባደረጉት ጭፍጨፋ ከዘጠኝ በላይ ዜጎች ሲገደሉ ከጠላት ወገን ሁለት የአጋዚ ወታደሮች መገደላቸው ታውቋል።


Waloo Rayya hidhamtota isaa bilisa basee jecha jiruu. Qobbo diree warana fakkatee jirti yeroo amma . I think Oromo should think before too late .
TPLF must go .