በርሊን ኤምባሲ የሚሰሩ ስድስት ዲፕሎማቶች ጠቅልለው ወደ ሃገር ቤት እንዲመለሱ መታዘዛቸውን..

በርሊን ኤምባሲ የሚሰሩ ስድስት ዲፕሎማቶች ጠቅልለው ወደ ሃገር ቤት እንዲመለሱ መታዘዛቸውን 𝕿𝔥𝔢 𝕱𝔦𝔫𝔣𝔦𝔫𝔫𝔢 𝕴𝔫𝔱𝔢𝔯𝔠𝔢𝔭𝔱 የደረሰው የኢሜል ልውውጥ ኮፒ  ያሳያል።
 
ለዲፕሎማቶች የሎጂስቲክስ አገልግሎት ከሚሰጠው ድርጅት ጋር ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደጠቆሙት ፍራንክፈርት የሚገኘው ቆንፅላ ሙሉ ለሙሉ የተዘጋ ሲሆን በርሊን የሚገኘው ኤምባሲም ከአምባሳደር ሙሉ በስተቀር ሁሉም ዲፕሎማቶች ከነቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ታዘዋል።

በርካታ ሌሎች ኤምባሲዎችም በተመሳሳይ የተዘጉ ሲሆን ለመዘጋታቸው ዋነኛው ምክንያት መንግስት ከምእራባውያን ጋር ያለው ግንኙነት መሻከሩና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመኖሩ ደሞዝ መክፈል በመቸገሩ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ወዳጆቻችን ጠቁመዋል።

ለደህንነታቸው የፈሩ በርካታ ዲፕሎማቶች በያሉባቸው ሀገራት ጥገኝነት በመጠየቅ ላይ መሆናቸውንም ሰምተናል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአንድ ቀን በፊት ይህን ጉዳይ ፌክ ኒውስ ነው ሲል ማስተባበያ መስጠቱ ይታወሳል።