Amhara Mass Media Agency :የክልሉ አክቲቪስቶች ፤ የኢዜማ የፌስቡክ ሰራዊት እና መንግስት ውስጥ ያሉ አካላት ጃዋርና የኦሮሞ

በመንግስት ሚዲያ ብዙ ነገር ሲቀርብ አይቻለሁ ትናንት Amhara Mass Media Agency ያቀረበው ቃለ መጠይቅ ግን እጅግ ነውረኛና በህግ ሊያስጠይቀው የሚገባ ነው። የአማራ ቲቪ ፤ የክልሉ አክቲቪስቶች ፤ የኢዜማ የፌስቡክ ሰራዊት እና መንግስት ውስጥ ያሉ አካላት ጃዋርና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ከህወሃት ጋር ይሰራሉ የሚል coordinated የስም ማጥፋት ዘገባ በመሰራት ላይ ይገኛሉ። ጃዋርና የኦሮሞ ህዝብን በዚህ አስቂኝ የፈጠራ ወሬ እነጥላለሁ ብሎ የሚያስብ አካል የፖለቲካ ሀሁ ያልገባው መሆን አለበት። ይልቅ ጃዋር ላይ የሀሰትና የጥላቻ ዘመቻው በበረታ ቁጥር ደጋፊው በሱ ዙሪያ የበለጠ ይሰባሰባል። You’re doing him a favor.

አንደኛውና ትልቁ ነውር ሚዲያው አንድ የመንግስት ሃላፊ ከሌላ ሴት ጋር ሲያደርግ የነበረውን private chat ስክሪኑ ላይ ማሳየታቸው ነው። ስዩም ተሾመ ፌስቡክ ላይ ሲለጥፈው የምናፍርበት ጉዳይ በመንግስት ሚዲያ ሲተላለፍ እስኪ ምን ይባላል? እዚህ ጉዳይ ላይ የብሮድካስት ባለስልጣን ምን እንደሚል መስማት አለብን። ባለፈው ጌታቸው ረዳ የኢትዮ ተሌኮም ቁጥሬን ተጠቅመው hack አድርገውኛል ሲል ይሄ የህወሃት ተንኮል ነው ብዬ ከብዙ ሰው ጋር ቸኩዬ ተከራክሬ ነበር። በዋናነት መንግስት ውስጥ ያሉ ሰዎች hack ማድረግ ቢፈልጉ እንኳን blatantly የኢትዮ ተሌኮምን ስልክ ተጠቅመው ሃክ ያደርጋሉ ብዬ አላመንኩም ነበር። ከዛ በኋላ በርካታ ኢሜይሎች መሰረቃቸው ጉዳዩ እውነት መሆኑን ያሳያል። በግሌ ለጌታቸው ረዳ ውይም ለህወሃት ምንም ሀዘኔታ የለኝም። ጌታቸው ቄሮን በ demons & witches የተነሳሳ ሃይል ነው ሲል እንደነበርና ህወሃት ደግሞ ያንን መብቱን ሲጠይቅ የነበረውን ወጣት በመሳሪያ ስታጭደው እንደነበር አልረሳም። ህወሃት አሁንም ስልጣን ላይ ብትሆን ተመሳሳይ የተቀነባበረ የሀሰት ዘገባ ትሰራ እንደነበርም ይታወቃል። No tears to shed for Getachew Reda or TPLF. They gave you a taste of your own medicine. ጃዋር ላይ የሀሰት ክስ ለማቀነባበር የተሰራ ስለሆነ ነው የማነሳው።

የኢትዮ ቴሌኮምን ስልክ በመጠቀም ኢሜይሎችን ከሰበሩ በኋላ መልእክቶች ለጃዋር cc አድርገው ላኩ። ይህ በ #አማራ_ቲቪ መቅረቡ ሴራ ጉንጎናው ላይ የአዴፓ እጅ እንዳለበት ያሳያል። መንግስት እየመራ ያለ አካል ኢትዮ ቴሌኮምን ተጠቅሞ ሰውን hack ማድረጉ ዜጎች በመንግስት ላይ የሚኖራቸውን እምነት የሚሸረሽርና amateurish ነው (ያውም የውሸት ሴራ ለማቀነባበር)። ቢያንስ ትንሽ sophisticated የሆነ የጠለፋ ዘዴ የሚጠቀሙ የቻይና ሃከሮች መቅጠር አንድ ነገር ነው።

በዛ ላይ ኤሜይሎቹን ሃክ አድርገው ወደ ጃዋር የላኳቸው መልእክቶች ህፃን ልጅ የማያሳምኑ ናቸው። በግልፅ መንግስትን እንጣል የሚል ይዘት ያላቸው መልእክቶች ለጃዋር ተልኳል ይላሉ (እራሳቸው እንደፃፉት ይታወቃል)። አንድ ሰው ምን ያህል ነፈዝ ቢሆን ነው በስሙ በተከፈተ ኢሜይል እንደዚህ አይነት እጅግ አደገኛ የሆነ መልእክት የሚለዋወጠው? ያውም በዚህ ዘመን ስንት encrypted የሆኑ የመልእክት መለዋወጫ መንገዶች እያሉ። እንደው ሞኝ እንሁንና መልእክቱን የላኩት የህወሃት ሰዎች ናቸው ብለን እንመን ቢባል እንኳን ጃዋር መልሶ የላከው አንድም ኢሜይል የለም።

ሌላው በቃለ መጠይቁ ላይ ስዩም ተሾመ ጃዋር ወጥታችሁ ሰው ግደሉ ብሏል ብሎ በጭራሽ ያልተባለ ውሸት ሲናገር ነበር። የስዩም መዋሸት አልገረመኝም። ዜና የሚሆነው ስዩም እውነት ሲናገር ነው። የቲቪው ጋዜጠኛና ኤዲተሮች ይሄንን ከማስተላለፋቸው በፊት መቼና የትኛው ፖስት ነው እንደዛ የሚለው ብለው እንዴት አይጠይቁም? ይህንን ያስተላለፈ ክልል በምን የሞራል ልእልና ነው ሌሎች የቲቪ ኔትዎርኮች ይዘጉልኝ የሚለው? እንደውም ዋናው ጥያቄ ኢትዮ ቴሌኮም ውስጥ ሆኖ የኢሜል recovery ቴክስቶችን የሚጠልፈው ግለሰብ (አካል) ማነው? ጠ/ሚ አብይስ ይሄን እንዴት ነው የሚያየው? አንድ ግለሰብ የስም ማጥፋት እንዲያካሄድ ግማሽ ሚሊዮን ብር ሲከፈለው ማነው የከፈለህ ተብሎስ እንዴት አይጠየቅም? ጃዋር የአማራ ማስ ሚዲያን ዘገባ ለብሮድካስት ባለስልጣን ማመልከት ብቻ ሳይሆን በቀጥታ ፍርድ ቤት ነው መውሰድ ያለበት። ዘገባው ጃዋርን ስለሚጎዳው ሳይሆን ይህ ክስ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ምን ያህል independent እንደሆኑ የምናይበት ስለሚሆን።

አሁንም ቢሆን ሺ የማይጨበጥ ክስ ማቅረብ ይቻላል። ጃዋር አንድም ቦታ እከሌ የሚባልን ብሄር ሄዳችሁ አጥቁ ማለቱን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የቻለ የለም።። ብሎ አያውቅም ሊልም አይችልም። በተቃራኒው ማንም ብሄር እንዳይነካ ያሳሰበበትን በርካታ ማስረጃዎች ማቅረብ ይቻላል። ከዚህ በፊት እንዳልኩት ጃዋር ህዝብን አጥቁ የሚል ንግግር ቢያደርግ መጀመሪያ የሚቃወመው ይሄ ገፅ ነው። ይህ ተግባር በነፃ የፖለቲካ መድረክ ፈፅሞ ሊገዳደሩት የማይችሉ አካላት ተስፋ መቁረጣቸውን የሚያሳይ ነው። ይሄን በሃሰት ላይ የተመሰረተ የስም ማጥፋት ዘመቻ የምታካሂዱበት ሰዎች ግን የምርጫ ቅስቀሳ እያካሄዳቹለት መሆኑን እወቁ።

Via: THE FINFINNE INTERCEPT
copy ስናደርግ በአግባቡ ኮፒ እናድርግ
ምንጭም እንጥቀስ 😊 ወይም ” ” እንጠቀም