በመለስ ዜናዊ ስም የተሰየመ ተቋም ውስጥ መስራት አልፈልግም- ጀግና ኢትዮጵያዊ.በምኒሊክ ስም የተሰየመ ተቋም ውስጥ መስራት አልፈልግም- ጠባብ፣ ዘረኛ፣ ሙት ወቃሽ፣ አገር አፍራሽ

*በመለስ ዜናዊ ስም የተሰየመ ተቋም ውስጥ መስራት አልፈልግም- ጀግና ኢትዮጵያዊ

* በምኒሊክ ስም የተሰየመ ተቋም ውስጥ መስራት አልፈልግም- ጠባብ፣ ዘረኛ፣ ሙት ወቃሽ፣ አገር አፍራሽ

የኢትዮጵያዊነት ብያኔ ሰጪ ነን ባዮች logic ይሄንን ይመስላል። እንዴት “ቅዱሱን” ምኒሊክን እና “ጭራቁን” መለስ ዜናዊን ታወዳድራለህ የሚል ጥያቄ ቢነሳ ትንሽ የምልከታ ጥራት እንዲኖረን የምኒሊክ ጦር ወደወላይታ ሲዘምት አብሮ የዘመተው ቫንደርሄይም ያሰፈረውን የአይን እማኝነት እንመልከት። (የአይን እማኞች በጽሁፍ ባይከትቡት ይሄም የፈጠራ ታሪክ ነው ይባል ነበር)። ለሰው አእምሮ በመጠንቀቅ ዘግናኝ ዝርዝሮችን አስወግጃለሁ

“ጭፍጨፋው እጅግ ዘግናኝ ነበር። አንድ በብዙ ጦርነቶች ላይ የተሳተፉ ራስ እንደነገሩኝ እንዲ አይነት እልቂት ከዚ በፊት በተሳተፉበት ጦርነት አይተው አያውቁም። ንጉሱን (ምኒሊክን) የሟቾቹ ወላይታዎች ብዛት ስንት እንደሆነ ስጠይቃቸው መረጃውን የእርሳቸው seal holder እንዲነግረኝ አዘዙ። እሱም ከተለያዩ የጦር አለቆች መረጃውን አጠናክሮ የሞቱት እና የተያዙት ብዛት 96, 000 እንደሆነ ነገረኝ። በእኔ ግምት ግን ትክክለኛው ቁጥር ወደ 20, 000 ይመስለኛል። ”

“ሁለት የምኒሊክ ወታደሮች በተገናኙ ጊዜ አንዱ ሌላውን ምን ያህል (ወላይታ) ገደልክ ብሎ ይጠይቀዋል። መላሹም እጅግ የተጋነነ ቁጥር በጠራ ጊዜ ጠያቂው እስቲ ምኒሊክ ይሙት በል ብሎ በመሀላ እንዲያረጋግጥለት ጠየቀው። መላሹም ምኒሊክ ይሙት ብሎ በመማል ቁጥሩን አረጋገጠ”

“በደም የሰከሩ የምኒሊክ ወታደሮ የቆረጡዋቸውን የወላይታዎች ብልቶች በጠመንጃቸው ጫፍ ላይ እንደሰኩ ታዩ። እንዲህ እያሉም ይዘምሩ ነበር። የሰማይ አሞራዎች ሀሴትን አድርጉ ዛሬ የሰውን ስጋ ትበላላቹና”

“ሚስቶች እና ልጆች በግፍ የተገደሉ ባሎቻቸውን /አባቶቻቸውን ሬሳ እንዲያዩ ይደረጉ ነበር”

“በርካታ ሰዎች በባርነት በግዞት በሚወሰዱበት ሰአት ልጅ የታቀፉ ሴቶች ሰልፉን ሲያንቀራፍፉት ወታደሮቹ ልጁን ከእቅፋቸው ቀምተው ወደ ሜዳ ይጥሉት ነበር”

አሁንም ምኒሊክ ቅዱስ ነው አለማለት ወንጀል ነው? ሁሉም መሪዎቻችን የሚወዳቸውም የሚጠላቸውም የህብረተሰብ ክፍል እንዳለ ማወቅስ እንዴት ከበደን? መለስ divisive ከሆነ ምኒሊክም ነው። ሞተው የተቀበሩ ነገስታት የሀገር አንድነት ማሰሪያ ሊሆኑ አይችሉም!

Rediet Tamire