በሁላ-ሃገረ-ሰላም ወረዳ የሲዳማ አርሶ አደሮች ጩሄትና የመንግሥት ዝምታ፤

በሁላ /ሃገረ-ሰላም ወረዳ የሲዳማ አርሶ አደሮች ጩሄትና የመንግሥት ዝምታ፤

-“በየወረዳው የተገደለው የሲዳማ ህዝብ ብዙ ነው፤ እስከ አሁንም ግድያው ቀጥሏል። ለኢትዮጵያ መንግሥት ምን በድለን ነው ይህ ሁሉ ግፍና በደል የሚፈፀምብን?  ወታደር ዝም ብሎ ይተኩስብናል፤ በመከላከያ ዩኒፎርም ማን እየገደለን እንደሆነ አናውቅም፤ መከላከያ ለሁሉም ወገን ይቆመ እንደሆነ ነው የምናውቀው። እየተፈፀብን ያለውን ነገር መንግሥት አውቆ ነው ወይስ ከመሃል የወጣ አጥቂ ኃይል
እንደሆነ አናውቅም፤ መንግሥት እንደዚህ ይፈጽማል ብለን አናምንም። ነገር ግን አሁን እየገደሉን ላሉ ግለሰቦች ሽፋን እየሰጠ እኛን ለይቶ እያጠቃን ነው። ግለሰቦች በቂምና በበቀል ተነሳስተው ወታደሮችን እየመሩ ንጹሃን አርሶ አደሮችን እያስገደሉ ነው። ጤጥቻ ላይ ወታደሩ ሄዱ አርሱ አደሩን በማሳው ላይ ገድሎ ሄዷል። ስለንብረት ጉዳት እንጂ በእኛ ላይ እየተፈፀመ ያለውን በደል የሚያሰማልን የለም፤
የልጆቻችን ደም ከጎመን ዋጋ አንሶ ተገኝቷል።  በግፍ የተገደሉ ልጆቻችንን እንዳንቀብር እንኳን እየተሳቀቅን ነው።ተደብቀን ጉድጓድ
ውስጥ ጥለን ለነብሳችን ስንሸሽ ከርመናል። ዛሬ ነው ይህንን ልጅ ልንቀብር በግልጽ የወጣነው። አምስት ስድስት ሬሳ ከአንድ ቦታ እንለቅማለን። ይህንን የኢትዮጵያም የዓለምም መንግሥት እንድሰማልን እንፈልጋለን”።

(ተናጋሪዎቹ ሶስት ግለሰቦች ናቸው፤ አሳጥሬ ወደ አማርኛ ከመተርጎም ውጪ አስቀረሁ
እንጂ አንዳች አልጨመርኩም።) copy KKL
Sidama page


ሰበር ዜና: በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከዳሌ፣ወንሾ፣ሎካ አባያ ወረዳና ይርጋአለም ከተማ ኤጄቶ በጋራ በመሆን የተሰጠው አቋም መግለጫ!!

የሲዳማ ሕዝብ በህገ መንግስቱ የተደነገገውን ራስን በራስ የማስተዳደር የመብት ጥያቄ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ላለፉት አንድ አመት መጠየቁ ይታወሳል።

ይሁን እንጅ ሐምሌ 9/2011 ዓ.ም በወቅቱ ከኢትዮጵያ ብ/ምርጫ ቦርድ የተሰጠው ግልጽ ያልሆነ መግለጫ እና የህገ መንግስታዊ ጊዜ ገደብ በመጠናቀቁ ምን መደረግ እንደሚገባው ለመነጋገር ከሁሉም የሲዳማ አከባቢዎች ተወክለው የተወጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፥
እናቶች፥ሞቴዎች፥ሲዳማ ሙራሀኖች፥ተፎካካሪ ፖርትዎች እና የኤጄቶ በተገኙበት ወደ ሀዋሳ ሶሬሳ ጉዱማሌ በሚያመራው ህዝብ ላይ ወታደሮች እንዳይገቡ መከለሉን ተከትሎ፣ሀዋሳ ጉዱማሌ አከባቢ በተነሳው አለመረጋጋት ወደ የተለያዩ ሲዳማ ከተሞች እንድዛመድ ሆኗል፡፡በዚህ ሁከትና ብጥብ ምክንያት መንግስት ባልታጠቁና ሰላማዊ የሲዳማ ህዝብ ላይ በወሰደው ወታደራዊ እርምጃ በርካታ ዜጎች ለሞት፣ለአካል ጉዳት፣ለንብረት ውድመት ተዳርገዋል።እነዚህ ጉድዳዮችን አስመልክቶ ከአራቱም ወረዳ የተወጣጡ ሲዳማ ኤጄቶች ዛሬ በአስቸኳይ ስብሰባ ያደረገው ሲሆን ባለ ስድስ( #6) ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

1.#ሐምሌ_11_11 ጀምሮ በይርጋለም ከተማ ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ባነሱ ሰላማዊ የሲዳማ ብሄር ተወላጆች ብቻ ተለይቶ መንግስት የወሰደውን ወታደራዊ እርምጃ በጽኑ እናወግዛለን።
በዚህም ወታደሮች የወሰደው #ኢ_ህጋዊ እርምጃ የደረሰውን ውድ የሰው ህይወትና በጥቃቱም ምክንያት አካላቸውን የተጎዱ ዜጎቻችን ሀዘናችን ጥልቅ መሆኑን እንገለፀን፡፡

2.በይ/ዓለም ከተማና ዳሌ ወረዳ የተለያዬ ቀበሌዎች ያለ ወንጀላቸው ታስረው ለምንገላቱ ወገኖቻችን መንግሥት በአስቸኳይ አጣርቶ እንድፈቱልጥ አጥብቀን እንጠይቃለን።

3.በይርጋለም ከተማ እና ዳሌ ወረዳ ውስጥ ለዘመናት አብሮ የኖረው ህዝባችን ላይ የደረሰው የንብረት ውድመት መኖሩን አረጋግጠናል፡፡
በዚህ ንብረት መጥፋቱን ኤጄቶ በፅኑ እናወግዛለን፡፡ከዚህ ጋር ተያይዘው ንፃን ኤጄቶን ለወንጀሉ ተባባሪ ናቸው የሚለው አካላት የተሳሳተ መሆኑን እያስገነዘበን፣ይህ ተግባርን የፈፀመው አካል ኤጄቶን የማይወክልና መሰረታዊ የትግል አቋም ውጭ የሆነና የኤጄቶን አላማ የማይወክል መሆኑን በድጋሜ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡

4.ዳሌ ዞን ኤጄቶ(ዳሌን ማዕከል በማድረግ) ላለፋት 12 ወራቶች ፍፁም ሰላማዊ መንገድ የምታገሉ ኤጄቶ እንዳሉ የሚታወስ ሲሆኑ፣ከሐምሌ 11 ጀምሮ በይርጋለም ከተማና አንዳንድ ዳሌ ወረዳ ውስጥ የተፈጠረው ግርግርን ምክንያት የወደመው ንብረት ኤጄቶ እጃቸው አለ ተብሎ ስም ዝርዝር ለኮማድ ፖስት የሰጡ ግለሰቦች እንዳሉ ኤጄቶ በሰፊው ገምግሟል፡፡ስለሆነም እነኝ ኤጄቶ አሳዳጆች ከድርጊታቸው እንድቆጠቡ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡

5.ከሐምሌ_11_11 ጀምሮ የሲዳማ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጆችን ጨምሮ በሐዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ክልል ውስጥ የተለያዩ ወረዳዎች ያለበቅ ምክንያት የታሰሩ ኤጄቶቻችን በአስቸኳይ እንድፈቱልን አጥብቀን እጠይቃለን፡፡

6.ምርጫ ቦርዱ ህገመንግሥቱ አካሄድ ባይሆንም፣ ህዳር 11 በፍት ሪፊረንዴም ( #የህዝብ_ውሳኔ) ተደርጎ ከህዳር 12 ጀምሮ ሲዳማ ብሔር ክልል እንደምሆን ሐምሌ 9/2011 በመግለጫቸው ያስገነዘበው ብሆንም፣እስኳን ድረስ ሪፊረንደም ቀን ባለመቁረጡ ምክንያት ህዝባችን ውስጥ ብዙ ጥርጣረ እየፈጠረ ስለሆነ በአስቸኳይ ሪፊረንዴም ቀኑን ይፋ እንድደረጉልን እንጠይቃል፡፡

ሀምሌ 29/2011