በህዳር ወር 2009 ከሚሰራበት ቦታ ተይዞ ከታሰረ በኋላ ሽብርተኞችን በገንዘብ ትደግፋለህ

በህዳር ወር 2009 ከሚሰራበት ቦታ ተይዞ ከታሰረ በኋላ ሽብርተኞችን በገንዘብ ትደግፋለህ በሚል የፀረ ሽብር አዋጁን አንቀፅ 7(1) ተላልፈሃል ተብሎ ክስ የተመሰረተበት የ41ድ አመቱ እና የሁለት ልጆች አባት የሆነው አቶ ጋሪ ዱጉማ ትላንት የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ተይዞ በነበረው ቀጠሮ ምስክሮቹ አልቀረቡም በሚል ተለዋጭ ቀጠሮ ለጥቅምት 22 እና 23/2010 ሲሰጥ በምሬት የሚከተለውን ተናግሮ ነበር።

Via Mahlet Fantahun 

“የምሰራው የኮንሰልተንሲ ስራ ነው። ስራዬ ተበላሽቶብኛል። እኔን ተክቶ የሚሰራልኝ የለም። ልጆቼን እና ቤተሰቦቼን የማስተዳድረው እኔ ነኝ። በራሴ ወጪ የፒኤችዲ ትምህርቴን እየተማርኩ ልጨርስ ስል ነው የታሰርኩት። ማእከላዊ ቶርች እና ከፍተኛ ድብደባ ነው ሲፈፀምብን የነበረው። ”
አቃቤ ህግ ምስክሮቹ ግማሾቹ መጥሪያ ደርሷቸው እንደቀሩ፤ የተቀሩት ደግሞ በአድራሻቸው ተፈልገው ሊገኙ እንደልቻሉ በመጥቀስ ነው ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው የጠየቀው።

ከአቶ ጋሪ ዱጉማ ጋር የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው ሌሎች 8 ሰዎችም በመዝገቡ ይገኛሉ።

ጉዳያቸውን በእስር ሆነው መከታተል ከጀመሩ 1 ዓመት ከ7ወር የሆናቸው፤ የኦፌኮ ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር የሆነውን አቶ በቀለ ገርባ ጨምሮ ሌሎች የኦፌኮ አመራሮች የተካተቱበት የእነ ጉርሜሳ አያና መዝገብ የአቃቤ ህግ ምስክሮች እና ማስረጃዎቸ ተሰምተው ካለቁ 4ት ወራት አልፈዋል። ዳኞች የዐቃቤ ህግ ምስክር እና ማስረጃዎች ብይን እናሰማለን እያሉ የማይመስል ምክንያት እየደረደሩ ተደጋጋሚ ቀጠሮዎች ሲሰጡ ነው አራቱ ወራት እንደዋዛ የተቆጠሩት።
የነገው ቀጠሮ ብይን ለማሰማት እየተባለ ቀጠሮ መሰጠት ከጀመረ በኋላ 7ኛ ቀጠሮ መሆኑ ነው።
የነገው ቀጠሮ በምን ይቋጭ ይሆን?
የምንችል ነገ ጠዋት 3 ሰዓት ላይ ከፍተኛ ፍ/ቤት 4ኛ ችሎት ተገኝተን አጋርነታችንን በተግባር እናሳያቸው።