OMN: ስበር ዜና Dec 21,2017 || Ethio

OMN: ስበር ዜና Dec 21,2017 || Ethio

በዛሬው ቀን የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህራንን እንዲያወያዩ በትምህርት ሚኒስቴር አማካኝነት አንድ ልዑካን ተልኮ ነበር። የልዑካኑ ስብጥር ከሶስቱ እህት ድርጅቶች ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ነበር

Ambo: “በዛሬው ቀን የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህራንን እንዲያወያዩ በትምህርት ሚኒስቴር አማካኝነት አንድ ልዑካን ተልኮ ነበር። የልዑካኑ ስብጥር ከሶስቱ እህት ድርጅቶች ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ነበር
1. ዶ/ር አለሙ ከ ኦህዴድ
2. አቶ አየልኝ ከ ብአዴን እና
3.ወ/ሮ ታደለች ከደኢህዴን 
“በዚህ ልዑካን የህወሀት አባል አልተካተተም። ውይይቱ ከጠዋቱ 3:30 በሀገራችን በተለያዩ አከባቢዎች በግፍ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የ አንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነበር የተጀመረው።
“ውይይቱን የጀመሩት ዶ/ር አለሙ ሀገራችን አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንዳለች ገልፀው ይህንን ችግር እንዴት ነው ማለፍ ያለብን በተለይ የትምህርት ተቋማት ይሄን ችግር እንዴት ተቋቅመው ነው ማለፍ ያለባቸው በማለት ከመምህራኑ ሀሳብና ጥያቄ ካለ በማለት ውይይቱን አስጀምረውታል።

“በመቀጠልም መምህራኖች ያላቸውን ሀሳብና ጥያቄ ሰንዝረዋል
ከተነሱት ሀሳቦች ውስጥ ጥቂቶቹ
“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዜጎችን በአንድ አይን ማየት ለምን ተሳነው? እንዴት የአንድ ሀገር ዜጎች ሞት ሁለት ስም ይሰጠዋል የአንደኛው “ድንገት የተፈጠረ ክፍተት” ሌላኛው “የጅምላ ፍጅት” እየተባለ እንዴት
ልዩነት ይፈጥራል።”
ሌላው ተሳታፊ ደግሞ
“ከ ስድስት መቶ ሺህ በላይ ህዝብ ተፈናቅሎ ሳለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዴት ያሉበትን ሁኔታ ሄዶ ለማየት እንኳ ተሳነው?”

“ህጉ ለምን አይከበርም? አንድ ክልል የፌደራል ሀይል እገዛ ሳይጠይቅ ፌደራል ለምን በክልል ስልጣን ጣልቃ ይገባል?”
አንድ በእድሜ ገፋያሉ ሰው ደግሞ እንዲህ አሉ
“እኔ በእድሜዮ እንዲህ አይነት አስከፊ ጊዜ አይቼ አላውቅም። ይዋል ይደር እንጂ በሀገራችን እየተፈፀሙ ያሉ ወንጀሎች በአለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ለፍርድ መቅረባቸው አይቀርም”
ይህ እና መሰል ሀሳቦች በሰፊው ሲነሱ የቆዩ ሲሆን በአንድ አጋጣሚ ግን በአደራሹ የነበረው ታዳሚ በግርምት ሳቅ ተጥለቅልቋል። ነገሩ እንዲህ ነበር አንድ ታዳሚ እንዲህ ሲል ይጠይቃል
“ትላንት ከትላንት ወዲያ ተማሪዎቹን ስታወያዩ ነበር ግን ያወያያቹበት ሁኔታ ተማሪዎቹን በብሔር በመከፈፈል ነበር። ይህ ለምን ሆነ?? ይህ በራሱ ተማሪዎቹ ሌላ ጥያቄ እንዲያነሱ አያደርግም ወይ?? የሚል ነበር።”
የደኢህዴኗ ወይዘሮ ታደለች እንዲህ ስትል መልስ መስጠት ጀመረች
” አዎ ልክ ነው ኦሮሞዎችን ለብቻ፣ አማራና ቤኒሻንጉልን ለብቻ፣ ትግሬዎቹ እንኳ አዲስ አበባ ላይ ነው ስብሰባ እያደረጉ ያሉት….።” ብላ ወደ ዝርዝሩ ከመግባቷ በፊት በአደራሹ የነበረው ታዳሚ በግርምት ሳቅ አቋረጣት።

“እዉነት ነው አንዱ ተማሪ ከሌላው በተለየ መልኩ እንክብካቤ ሲደረግለት ያስገርማል። አዲግራት ላይ ወይም አክሱም ላይ ችግር ሲፈጠር የአማራ ወይም የኦሮሞ ተማሪ ችግር እንዳይደርስበት ተብሎ ወደ አዲስ አበባ አልተላከም። ወደ ቤቱ እንኳ እንዳይሄድ በር ላይ ሲከለከል። አማራ ወይም ኦሮሚያ ክልል ያሉ የትግራይ ተማሪዎች በፍጥነት ወደ አዲስ አበባና ቤተሰቦቻቸው ትራንስፖርት ተመቻችቶላቸው ሲላኩ የትግራይ ክልል ተማሪዎች ከሌላው ኢትዮጲያዊ የተለዩ ናቸው ማለት ነውን?? እነዚህ የትግራይ ተማሪዎች ወደ ትምህርታቸው ሲመለሱ በጎደኞቻቸው ፊት የሚኖራቸው አመለካከት እንደበፊቱ ይሆናልን። አንድ ተማሪ ከነበረው ጭንቀት ወደ ቤተሰቡ መሔድ እየፈለገ በፌደራል ፖሊስ ሲከለከል አንድ ክፍል አብሮት የሚማረው ዶርም የሚጋራው ጓደኛው ግን ትግሬ ስለሆነ ብቻ ትራንስፖርት ተመቻችቶለት ወደ ቤቱ ሲሄድና ከሌላው የተለየ እንክብካቤ ሲደረግለት ሲያይ ምን ይሰማው ይሆን?? ይህ ነጥብ አስተዛዛቢ አስገራሚም ስለነበር ነው ታዳሚው የአግራሞት ሳቅ የሳቀው።

“ባጠቃላይ የሁሉም አስተያየት ሰጭ አቋም የነበረው በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ቢኮንም ትምህርት መቀጠል እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተው ሲናገሩ ነበር።

“በሌላው በኩል የብአዴኑ አቶ አየልኝ እንዳሉት ከኢትዮ ሶማሌ ክልል የተፈናቀሉትን ሰዎች የአማራ ክልል ልዑካን ልኮ እንዳያቸውና አስፈላጊውን ትብብር እያደረጉ እንደሆነ አስረድቷል።
“በመጨረሻም ስብሰባውን ያጠቃለሉት ዶ/ር አለሙ እንዲህ ነበር ያሉት “የሚገርም ትውልድ ነው የተፈጠረው በዚህች ሶስት ቀናት ብቻ ባየሁት ነገር የተረዳሁት በማታለል የምታልፈው ተማሪ አለመኖሩን ነው። በፍፁም ደግሞ ልትጭንበት እሺ አይልህም። ተማሪው ቀድሞን ሄዷል። ከፋፍለን ብናወያያቸውም ጥያቄያቸው ተመሳሳይ ነው። ህገ መንግስት እያጣቀሰ ነው የሚጠይቅህ።
ስለዚህ እንደ መንግስት የህዝቡን ጥያቄ የመመለስ ግዴታ አለብን። ካልቻልን ደግሞ ለሚችለው ማስረከብ ነወ። የኢትዮጲያ ህዝብ ይቅር ባይ ነው ይህንን እኛ ኦህዴዶች አይተነዋል ይህንን ይቅር ባይነቱን በጊዜ ካልተጠቀምነበት ግን ሁልጊዜ ላናገኘው እንችላለን።
Tsegaye Ararssa