ስልጤ ወራቤ ላይ በዛሬው ዕለት ፀረ አሀዳዊ መንግሥት ፀረ ብልግና ተቃውሞ ሰልፍ ፈንድቶ ውሏል።

ስልጤ ወራቤ ላይ በዛሬው ዕለት ፀረ አሀዳዊ መንግሥት ፀረ ብልግና ተቃውሞ ሰልፍ ፈንድቶ ውሏል።
ብሔር ብሔረሰቦች አንድ በአንድ ወደማይቀረው የትግል ግራ በይፋ እየተቀላቀሉ ነው።
አምቤው በል!

ሰበር ዜና: በዛሬው እለት በስልጤ ወራቤ ልዩ ስሙ ዱና በሚባል አከባቢ መስጅድ መፍረሱ ታወቀ።
 
ጥቅምት 15/2013 እሁድ
በዛሬው እለት ከጠዋቱ 4:00 ላይ ሕገ ወጥ ነው በሚል ሰበብ 99 በመቶ ሙስሊም በሆነበት ስልጤ ወራቤ ከማሕበረሰቡ ጋር ምንም አይነት ውይይት ሳይደረግ በዞኑ አስተዳደርና በፖሊስ ልዩ ኃይል ትብብር የዱና መስጂድ መፈረሱ ተሰማ።
ወራቤ ከተማ ዱና ተብሎ የሚጠራው በወራቤ ዩኒቨርስቲ ዙሪያ የሚገኘው መስጂድ በዛሬው እለት ሲፈርስ ማህበረሰቡ በመውጣት ጥገና ያደረገ ቢሆንም የዞኑ መስተዳድር የክልሉን ልዩ ኃይል በማሰማራት በድጋሚ አፍርሷል።
የወራቤ ከተማና አጎራባች አከባቢዎች ወደ አደባባይ በመውጣት ከፍተኛ ተቃውመውን አሰምቷል። በዚህ ተቃውሞ ሳቢያም ቁጥራቸው በውልል ያልታወቁ ምዕመናን መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሏል።
የስልጤ ዞን አስተዳድር አቶ ዓሊ ኸድር፣ አቶ ሙዲን ሙኒር የዞኑ ኮምኒኲሽን ኃላፊንና አቶ ነስሩዲን የወራቤ ከተማ ኮምኒሌሽን ኃላፊን ለማናገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
ስለፍትህ እንጮሀለን፣ ሠላምን እንሰብካለን፣ አንድነትንና መከባበርን እንሻለን!