ስለ ምርጫ ተብየው: የነፍጠኛ ልጆች ተረት ተረት እያሉን ነው ምን ይሻለናል ዘንድሮ ?  የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ይባል የለም!

ስለ ምርጫ ተብየው: የነፍጠኛ ልጆች ተረት ተረት እያሉን ነው ምን ይሻለናል ዘንድሮ ?  የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ይባል የለም!

የኦዴፓው አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን አምርረው ያወግዛሉ። ክፍለሀገርና ጠቅላይ ግዛት የሚል የአስተዳደር ሽንሸና ዳግም ለመጫንና ብዝሃነትን ለመጨፍለቅ ተዘጋጅተዋል ሲሉ በተንሸዋረረ እይታ፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እያብጠለጠሉ ነው። ሁለቱ የቀድሞ መዋቅሮች ከፌደራሊዝም ስርዓት ግንባታ አንጻር ተፈትነው የወደቁ ብለውም ግምት ላይ የሚጥላቸውን አስተያየት ሰጥተዋል። እነዚህ የቀድሞ መዋቅሮች ማዕከላዊ አስተዳደርን የሚከተሉ ሆነው በፌደራሊዝም መስፈርት እንዴት ተመዝነው በፈተና ሊወድቁ እንደቻሉ ሊነግሩን መሞከራቸው ትዝብት ላይ የሚጥላቸው ይመስለኛል። ቀድሞውኑ ፌደራል ስርዓት ያልሆኑትን ክፍለሀገርና ጠቅላይ ግዛት መዋቅሮችን አሁን ካለው በስመ ፌደራሊዝም ሀገሪቱን የባሰ አደጋ ውስጥ ከከተተው ‘ፌዘራሊዝም’ ጋር በማወዳደር የእኛ የተሻለ ነው ብሎ አደባባይ መውጣት ገዢውን ፓርቲ “ቆሞ ቀር፣ መለወጥ የማይችል” ወደሚል ድምዳሜ እንድንደርስ የሚያደርገን ነው።
 
ይልቅስ በጎሳ ላይ የተመሰረተው፣ የፌደራሊዝም ሽታ እንኳን የሌለው የአሁኑ ስርዓተ መንግስት ነው በተግባር ተፈትኖ የወደቀው። በብዝሃነት ባዶ ዲስኩር ላለፉት 30ዓመታት ሀገሪቱ የቆየችበት መዋቅር የብሄረሰቦችን መብት የፓለቲካ ማድመቂያ ከማድረግ ያለፈ የፈየደው ነገር እንደሌለ በተቃራኒው ከነችግራቸውም ተስማምተውና ተቻችለው ለዘመናት ሲኖሩ በነበሩ ኢትዮጵያውያን መሀል የጸብ ግድግዳ ያቆመ፣ በካራ እንዲገዳደሉ ያደረገ፣ የሀገሪቱን ህልውና ከገደል አፋፍ ያስጠጋ መሆኑን ሰምተን ሳይሆን ኖረንበት ያየነው እውነት ነው። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከሌሎች የኦዲፒ አመራሮች በተለየ የዘር ፌደራሊዝሙን ጣጣና መከራ በተመለከተ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ላይ ጭምር በግልጽ ሲያወግዙት ሰምተናል። አቶ አዲሱ “የዘር ፌደራሊዝሙን ክፍተት ሸፍነን፣ የጎደለውን ሞልተን፣ የተጣመመውን አቅንተን፣ የተሳሳተውን አርመን እናስቀጥላለን” ሲሉም ይነግሩናል። ሲጀመር የተበላሸን፣ ከአፈጣጠሩም የተወላገደን፣ ከስሪቱም የተጣመመን ነገር ኦዲፒ በምን ተአምር አስተካክሎ ለማስቀጠል እንደፈለገ ሊገባኝ አልቻለም።
 
ህወሓት ላይ ያላማረ የዘር ፌደራሊዝም በኦዲፒ ዘመን እንዴት ሊቆነጅ እንደታሰበ ግራ የሚያጋባ ነው። የዘር ፌደራሊዝም ዓለም ላይ የቀረው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው። ሀገራት በህግ እስከማገድ የደረሱበትን፣ የሰውን ልጅ መርጦ ባልተፈጠረበት ማንነቱ እንዲሸለምና እንዲቀጣ የሚያደርግን ፍጹም ኋላቀር የሆነን የዘር ፓለቲካና አስተዳደራዊ መዋቅር “አርመን እናስቀጥላለን” ማለት ሀገሪቱን ለሌላ ዙር የማያባራ ቀውስ አሳልፎ ከመስጠት ውጪ አንዳች አወንታዊ ትርጉም የለውም። ፈጣሪው ህወሓት በገዛ እጁ ኮትኩቶ ባሳደገው የዘር ፓለቲካ ተጠልፎ መጨረሻው አሳፋሪ ውርደት መሆኑን እያየን ዛሬም ይህንኑ መርዛማ ፓሊሲ እንከተላለን ማለት ከትልቅ አደጋ ጋ ተፋጠናል ማለት ነው። ፈጣሪዎቹና አስተማሪዎቹ የወደቁበትን ጉዳይ ተማሪዎቹ በምን ጥበብ ሊያልፉ እንደተዘጋጁ የሚያውቁት እነሱ ብቻ ናቸው። ኦዲፒ የዘር ፓለቲካን የሙጥኝ እላለሁ፣ የዘር አስተዳደራዊ መዋቅርን አርሜ አስቀጥላለሁ ሲል አቅሙን ፈትሿል?
#ምርጫ2013 ክርክር
የለውጡ ባለቤት ማን ነው? #ብልጽግና#አብን እና #ኢዜማ የሚከተሉትን ሀሳቦች በጉዳዩ ላይ አንጸባርቀዋል።
(ምንጭ፦ ኢቴቪ)