ስለ ሀገር- የሶመሌ ህዝብ ጥያቄ ሳይመለስ ተጨፍልቋል! መሐመድ ኦላድ|

ስለ ሀገር//- የሶመሌ ህዝብ ጥያቄ ሳይመለስ ተጨፍልቋል! መሐመድ ኦላድ| የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የቀድሞ አማካሪ -ክፍል 1

አቶ መሀመድ ኦላድ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የቀድሞ አማካሪ በታች በተለጠፈው ሊንክ አንኳር የሆኑ ጉዳዮችን ያነሳሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል፦
• ብልጽግና የህዝቡን መሰረታዊ ፍላጎት ሳያሟላ ሶዴህፓን ጨፍልቆ የተፈጠረ አገር አቀፍ ፓርቲ ስለመሆኑ!
• ፒፒ የሶማሊ ህዝብ ዝንድ መሰረት እና ተቀባይነት የሌለው ድርጅት መሆኑን፡፡
• የሶማሊ ህዝብ ጥያቄ ላለፉት 120 ዓመታት እንዳልተመለሰ፡፡ ከምኒልክ ግዜ ጀምሮ የህዝቡ ፍላጎት ራሱን በራሱ የማስተዳደር፣ የራሱን ዕጣ ፈንታ የመወሰን ነበር፡፡ ነገር ግን በመጡት መንግስታት ሁሉ ይህን ፍላጎቱ ሲዳፈንበት ነበር፡፡ አሁንም ሆነ በኢህአዴግ ግዜ ወይ በጣልቃ ገብነት አልያም ባለው የፖለቲካ አደረጃጀት የሶማሊ ህዝብ ፍላጎቱ እንድከስም መደረጉ፡፡
• የሶማሊ ክልል የተገነባለት ገጽታና በመሬት ላይ ያለው እውነታ የማይገናኝ መሆኑ፡፡ አሁንም ድረስ ሰዎች ያለጥፋታቸው በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት መታሰራቸውን እና መገደላቸውን ይዘረዝራል
• የአብዲ ኢሌ play book የተደገመበት ሁኔታ በክልሉ ስለመኖሩ ይናገራል፡፡
ይመልከቱት