ሰይጣንን ማወደስ: ህወሃቶች በነውጥና በቀውስ እየታመሱ ባሉበት በዚህ ፈታኝ ጊዜ ያገኙት

ሰይጣንን ማወደስ : ህወሃቶች በነውጥና በቀውስ እየታመሱ ባሉበት በዚህ ፈታኝ ጊዜ ያገኙት አንድ መጽናኛ ሰይጣንን ማወደስ ሆኗል። የዛጉ የፕሮፓጋንዳ ማሽኖች ሁሉ እንደምንም እየተንቋቁ የሙት መንፈስ ለማንገስ መለስ “ዜናዊ የዘመን ክስተት ከአህጉር በላይ የገዘፈ” ስብእና እደነበረው እየደሰኮሩ ነው።
ነገሩ ለሰይጣኑ በማሰብ አይደለም። በሰይጣን መንፈስ ተከልሎ እኩይ ተግባርን ለመቀጠል የሚደረግ ከንቱ የጣር ጩኸት መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው።
ከ26 አመታት በላይ ስልጣንን መከታ አድርገው በምስኪን ህዝብ ላይ ተዘርዝሮ የማያልቅ መከራና ግፍ ፈጽመው፣ ንጹሃንን በየእስር ቤቱ አጉረው ገድለውና አስገድለው በዝርፊያ ሃብት ተጨማልቀው መቃብር አፋፍ ላይ ቆመው እራሳቸውን “ታጋይ” ሲሉ አለማፈራቸው ምን ያህል በጭንቀት መታመሳቸውን ከማጋለጥ ያለፈ ፋይዳ የለውም።
አዜብ መስፍን መለስ ታላቅ የቀውስ ማኔጀር ነበር ብላለች። ይህ እውነታ አለው። መለስ ያለቀውስ ሊኖር አይችልም ነበር። እኩዩ ሰው ማለቂያ የሌላቸው ቀውሶች እየፈጠረ ማኔጅ ሲያረጋቸው፣ ለዚህም “ጥበቡ” እነበረክትና አዜብ ሲያውድሱት ይደሰት ነበር። ይሁንና ዛሬ የዚህ ዲያቢሎስ መንፈስ እነርሱን ከከባዱ የቀውስ ማእበል ፈጽሞ አያወጣቸውም። የህወሃቶች የአፓርታይድ ስርአት የንቧይ ካብ መሆኑ እንኳን ለኛ ለውጭው አለም ግልጽ ሆኗል።
ይሄን በቋፍ ላይ የሚገኝ የእኩዮች ስርአት በጋራና በህብረት እንፋለመው። የጭቁኖች ህብረት የጫቋኞችን ሞት ያፋጥናል

I find this picture very striking. Meles Zenawi denied freedom to the people of Ethiopia. He imposed a supremacist ideology, committed crimes against humanity and bled the nation with daylight robbery. Because of all the crimes he has committed against his own people, he doesn’t even feel safe in his grave without the protection of armed guards. The moral of the story: Have the courage to do good and serve your people to enjoy a meaningful life and feel safe after your death. Otherwise, cowardice will follow and haunt you to your grave and you lose your freedom to Rest In Peace. 

via: Abebe Gellaw