#ሰበር_ዜና: “ኦሮሚያ ውስጥ አንድ #አማራ_ከተገደለ #ስልጣኔን እለቅቃለሁ‼️” ጠ/ሚ አብይ አህመድ

#ሰበር_ዜና: “ኦሮሚያ ውስጥ አንድ #አማራ_ከተገደለ #ስልጣኔን እለቅቃለሁ‼️” ጠ/ሚ አብይ አህመድ

በአማራ ክልል የታየውን ህዝባዊ ተቃውሞ መነሻ በማድረግ በኦሮሚያ ክልል ብሔር ተኮር ግጭትና ብጥብጥ ለማስነሳት ውስጥ ለውስጥ እንቅስቃሴ መጀመሩን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየወጡ ይገኛል። በተለይ በተወሰኑ የአማራ ክልል ከተሞች “ዶ/ር #አብይ ኦነግ/ገዳይ ነው” የሚሉ መፈክሮችን እንደ መነሻ በመውሰድ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አከባቢዎች በሚኖሩ “#የአማራ_ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጥቃትና መፈናቀል ሊያጋጥም ይችላል” የሚል ስጋት አይሏል። ይህን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከኦሮሚያ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና አባገዳዎች፣ በጥቅሉ ብዛታቸው 30 ከሚሆኑ ሰዎች ጋር መወያየታቸው ተሰምቷል። ለጉዳዩ ቅርበት ያለው አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራ ክልል የተፈፀመው ሳያንስ በኦሮሚያ ክልል ተመሣሣይ ጥቃት ሊፈፀም መሆኑ ክፉኛ ያበሳጫቸው ከመሆኑም በውይይቱ መዝጊያ ላይ ለተሳታፊዎቹ አንድ #ጥብቅ ማሳሰቢያ፥ ማስጠንቀቂያ፥ መርዶ አሊያም ውርጅብኝ… ብቻ ምን እንደምለው አላውቅም! አዎ… ዛሬ..አሁን ከመሸ በኋላ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የተናገሩት ነገር እንዲህ የሚል ነው፤ “በኦሮሚያ ክልል ውስጥ አንድ የአማራ ተወላጅ ቢገደል በገዛ ፍቃዴ ስልጣኔን እለቅቃለሁ!” ብለዋል። እደግመዋለሁ… “አንድ የአማራ ተወላጅ ኦሮሚያ ውስጥ ቢገደል ስልጣኔን እለቅቃለሁ!” በእርግጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ማለታቸውን እኔ ለራሴ ማመን አልቻልኩም። እናንተም እንድታምኑኝ አልጠብቅም። ሆኖም ግን የሰማሁት ነገር እውነት ነው! አሁን እዚህ ጋር የፃፍኩት ነገ ጠዋት ለእኔ ለራሴ ሚስጥሩን የሰማሁት በህልሜ ይሁን በእውኔ እንዳይምታታብኝ “for the record” ብዬ ነው‼️ በል እንግዲህ ምድረ ጉጠት እርምህን አውጣ❗️ ማን ነህ ባለተራ… አይይይይ ኢትዮጵያ… አንቺማ #ሰው_አይውጣልሽ ተብለሽ ተረግመሻል🇪🇹