#ሰበር ዜና ”የዎላይታ ህዝብ ክልል ጥያቄ ከህዝቡ አንደበት አስተፋለው” በማለት ፎክሮ የተነሳውን ብልፅግና በሁሉም ሥልጠና መድረኮች በጠንካራው በዎላይታ ህዝብ ክንድ ድባቅ ተመታ

”የዎላይታ ህዝብ ክልል ጥያቄ ከህዝቡ አንደበት አስተፋለው” በማለት ፎክሮ የተነሳውን ብልፅግና በሁሉም ሥልጠና መድረኮች በጠንካራው በዎላይታ ህዝብ ክንድ ድባቅ ተመታ‼
 
ገሱባ፣ ኦፋ ወረዳ፣ ለሶዶ ዙሪያ፣ ሶዶ ከተማ፣ ዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ወይዴ፣ ዳሞት ሶሬ፣ ዳሞት ፑላሳ፣ ሁምቦ ወረዳ፣ ጠበላ ከተማ አስተዳደር፣ አባላ አባያ…. በሁሉም ወረዳዎች አሁን በደረሰን መረጃ የተስፋዬ ይገዙ ኮንዶሞች ያዘጋጁት የፓብሊክ ሰርቫንት ጨምሮ በሁሉም መሰረቶች ላይ በዎላይታ ህዝብ ዘንድ ምንም ዕጣ ፈንታ እንደሌለው ተረጋገጠ።
 
ከተነሱ ሀሳቦች የተወሰኑ፦
 
ብልፅግና የሚባል ፓርቲ ከዎላይታ ህዝብ ጋር ወደማይታረቅበት ፀብ ስለገባ ፓርቲው ህዝባዊ መሰረት የለውም፣
የታሰሩ እውነተኛ የህዝብ ልጆች ይፈቱ፣
የዎላይታ በክልል የመደራጀት ህገ መንግሥታዊ ጥያቄ ይመለስ፣
 በርካታ የመልማት ጥያቄዎች ህዝቡ የደረሰበትን ደረጃ በሚመጥን መንገድ ይመለሱ፣
በሁሉም መዋቅሮች ህዝብን የማይመጥኑ ደካማ የተስፋዬ ይገዙ ተላላኪዎች በሌቦች ከሥልጣናቸው ይውረዱ እና ወዘተ…. በማለት ብልፅግና እንዳይዳይነሳ አድርጎ ግብዓተ መሬት ፈፅምዋል።