ሰበር ዜና: የሰላም ሚንስትሯ ወ/ሮ ሙፍሪያት ከሚል አራት ልጆቻቸውን ይዘው ጀርመን ገቡ።

ሰበር ዜና: የሰላም ሚንስትሯ ወ/ሮ ሙፍሪያት ከሚል አራት ልጆቻቸውን ይዘው ጀርመን ገቡ።
 
የማለዳ የውስጥ ምንጮች እንደገለፁት ወ/ሮ ሙፍሪያት ላለፉት በርካታ ቀናት ከልጆቻቸው ጋር ጀርመን ፍራንክፈርት ያሉ ሲሆን የአብይን ቡድን ለመካድ ጫፍ መድረሳቸው ታውቋል። ወ/ሮ ሙፍሪያት ወደ ጀርመን ያመሩት በህክምና ምክንያት(ሰበብ) እንደሆነ እና ኦፕራሲዮን እንደተደረገላቸውም ለማወቅ ተችሏል። ማለዳ ሚዲያ የህመማቸውንም አይነት የሰማች ቢሆንም ለ ግለሰቧ ‘Privacy’ ሲባል ከመግለፅ ተቆጥባለች።
 
ምንጮቻችን ወ/ሮ ሙፍሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከነ አብይ ቡድን ጋር ልዩነታቸው እየሰፋ መምጣቱን፣ ልጆቻቸውንም ይዘው መጓዛቸውን እና የቅርብ ሰዎቻቸውን ስለ መቅረት ማማከረቸውን በማንሳት ላይመለሱ እንደሚችሉ ተናግረዋል። (ማለዳ ሚዲያ የመቅረታቸውን ጉዳይ/መረጃ ለማረጋገጥ እየጣረች ነው።) ይህን የሚንስትሯን መንሸራተት የተረዳው የአብይ ቡድንም ወ/ሮ ሙፍሪያት እንዲመለሱ ጥረት እያደረገ ሲሆን ከተመለሱ ሰበብ ፈጥሮ ሊያስራቸው ወይም ከዚያም የከፋ ነገር ሊያደርግ እንደሚችል የማለዳ ምንጮች ያስረዳሉ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኮረኔል አብይ አካሄድ ተስፋ የቆረጡ በርካታ የስርዕቱ ደጋፊ የነበሩ ፖለቲከኞችና የፀጥታ አካላት(መከላከያን ጨምሮ) በተለያየ መንገድ እየኮበለሉ እንደሆነ ይታወቃል። ማለዳ ሚዲያ በዚህ ዜና ዙሪያ የበለጠ መረጃ በማሰባሰብ በቀጣዩ የአለን-Jirra ፕሮግራም ላይ ለውይይት የምታቀርብ መሆኑን ታሳውቃለች።
ማለዳ ሚዲያ


“Marroo marii sabaa”..