ሰበር ዜና-አቶ ደመቀ መኮንን ከጉባኤ የቀረበውን ሀሳብ ተቀብለው በማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ለመቀጠል ተስማሙ

ሰበር ዜና-አቶ ደመቀ መኮንን ከጉባኤ የቀረበውን ሀሳብ ተቀብለው በማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ለመቀጠል ተስማሙ

(FBC)–አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ደመቀ መኮንን ስያሜውን ወደ አማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንዲቀጥሉ ከድርጅታዊ ጉባዔው የቀረበላቸውን ሀሳብ በመቀበል ለመጠቀል ተስማምተዋል።

ድርጅታዊ ጉባዔው ስያሜውን ወደ አማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ለማዕካዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ባይወዳደሩ ያላቸውን 12 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የቀረበውን መነሻ ተቀብሎ አፅድቋል።

አቶ ደመቀ መኮንን በማእከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው ለመቀጠል የተስማሙት ከማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ለመቅቀቅ የቀረበውን ሀሳብ የ12ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ተሳታፊዎች በከፍተኛ ደረጃ በመቃወማቸው ነው።

ድርጅታዊ ጉባዔው ስያሜውን ወደ አማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ባይወዳደሩ ያላቸውን 12 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የቀረበውን መነሻ ተቀብሎ አፅድቋል።

በዚህም መሰረት፦

በክብር

አቶ ከበደ ጫኔ

አቶ መኮንን የለውምወሰን

ወይዘሮ ፍሬህይወት አያሌው

አቶ ጌታቸው አምባዬ

በትምህርት

አቶ ዓለምነው መኮንን

አቶ ለገሰ ቱሉ

አቶ ጌታቸው ጀምበር

አቶ ኢብራሂም ሙሀመድ

አቶ ደሳለኝ አምባው

ወይዘሮ ባንቺይርጋ መለሰ

በአምባሳደርነት እያገለገሉ ያሉ

አቶ ካሳ ተክለብርሀንና

ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ ናቸው።

በዳዊት መስፍን