ሰሞኑን አንድ ሁለት ጠቀም ያሉ መረጃዎች ከኢዜማ መንደር ወደ FI ተወርውረዋል። ኢዜማ ማን ወዳጅ ማን ጠላት እንደሆነ የለየበትና የሃገሪቷን ወቅታዊ የደህንነት ስጋት የተነተነበት ሚስጥራዊ ሰነድ አዘጋጅቷል።
ፕሮፈሰር ብርሃኑ ከጠሚ አብይ አህመድና ከኢዜማ በስተቀር ለሀገር ደህንነት ስጋት ብሎ ያልፈረጀው ሃይል የለም። ሰነዱ የሃገሪቷ ወቅታዊ የደህንነት ስጋት ትንተና ይሰኛል ወይም በሌላ ስሙ ጠሚውን ነጥሎ የመቀርጠፍ እቅድ ሊባል ይችላል።
የብሬን አምልኮተ አብይ ለጊዜው ችላ ብለን ሰነዱን ስንፈትሸው በኢዜማ ግምገማ መሰረት ጠሚው ከማህበራዊ መሰረቱ ብቻ ሳይሆን ከካድሬ መዋቅሩም ክፉኛ መነጠሉን ይጠቁማል። ፕሮፍ ብርሃኑ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት (ከንቲባነት) አቶ ክቡር ገናን አጭቶ ለተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር መወሰኑ የንጉስ አብይ አህመድ መንበር ላይ አይኑን እንደጣለ መገመት ይቻላል።