” ምርጫ ወቅቱን ጠብቆ በትግራይ ይካሄዳል።” ደብሪፅ

” ምርጫ ወቅቱን ጠብቆ በትግራይ ይካሄዳል።”
ደብሪፅ

Senait Mebrahtu
“እኛ ሁልግዜም ለውይይት ዝግጁ ነን።ዛሬ እዚህ የመጣችሁ የሀገር ሽማግሌዎችም በመምጣታቹ አመሰግናለሁ።
ግን ደግሞ ከሁለት አመት በፊት ጀምሮ ከአማራ ክልል ወደ ትግራይ የሚወሰድው መንገድ ሲዘጋ፣የትግራይ ህዝብ ላይ ጥቃት እንዲሰነዘር ተደጋጋሚ ዶክመንተሪ እየተዘጋጀ መንግስት በሚመራቸው ሚድያዎች ሲለቀቅ፣የትግራይን ሰላም ለማናጋት በየሚድያዎቹ አመፅ የማነሳሳት ስራ ሲሰራ፣ከኤርትራ መንግስት ጋር በመተባበር ትግራይን ለመውጋት ዝግጅት ሲደረግ፣የትግራይ ተወላጆች በማንነታቸው ሲፈናቀሉ እና ሲታሰሩ እንደዚሁም በእስር ቤት ሲሰቃዩ፣የራሳችንን እድል ራሳችን እንወስናለን በማለት ምርጫ እናካሂዳለን በማለታችን ምርጫ ካደረጋቹ እርምጃ እንወስዳለን ብለው ጦርነት ሲያውጁብን የት ነበራችሁ?
እስከዛሬስ ለምን ዘገያቹ?

እኛ ተደብቀን ተሸሽገን የምናደርገው ውይይት የለም።ህዝቡ በቀጥታ እየተከታተለው የሚደረግ ውይይት መሆን አለበት።
አሁን ያለው ሁኔታ የከፋ ነው።ጥይቷ ናት እንጂ ያልተተኮሰችው ሁሉም ነገር ተበላሽቷል።ለማስተካከልም የሚያስቸግር ሁኔታ ላይ ደርሰናል። ህግ እና ስርኣት የለም። ተጥሷል።አሁን ደግሞ ህገመንግስት እየፈረሰ ነው።
ስለዚህ አሁን ስልጣን ላይ ያለው ሀይል ችግር የፈጠረው ከትግራይ ጋር ሳይሆን ከመላው ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ነው።
ሰላም አውርድ መባል ያለበት ሀይል አለ።በግልፅ ሊነገረው ይገባል።እውነታው ይውጣ እናንተም በሀገሪቱ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት መድረክ ይዘጋጅ እንነጋገር

ሰላም አውርድ መባል ያለበት ሀይል በግልፅ ይነገረው።ህዝቡም እውነታውን ይወቅ።
እኛ የክልላችንን ሰላም ጠብቀን የህዝባችንን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ እየሰራን ነው።የህዝባችንን ጥያቄ እየመለስን ምርጫ 2012 በወቅቱ እናካሂዳለን።”
ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል