ምርጫ ቦርድ ትናንት አብን በመንግስት ባለስልጣናት መተቸቱ አግባብ አይደለም ብሎ መግለጫ አውጥቷል።

ምርጫ ቦርድ ትናንት አብን በመንግስት ባለስልጣናት መተቸቱ አግባብ አይደለም ብሎ መግለጫ አውጥቷል።

ጥሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል በቃል “ኦነግን ማጥፋት አለብን” ሲሉ ፤ የአማራ ክልል ከፍተኛ ሃላፊዎች በተደጋጋሚ ኦነግን ሲከሱ ፤ የክልሉ ሚዲያ ኦነግ ይህን አረገ ያን አረገ እያለ ሲወቅስ አንድም ቀን ይህን ተግባር አቁሙ ያላለው ቦርዱ አንድ ሁለት የታችኛው መዋቅር ሃላፊዎች አብንን ተቹ ብሎ በሰአታት ውስጥ የማስጠንቀቂያ መግለጫ ማውጣቱ ገራሚ አይደለም? “ኦነግ” ብቻ የሚል ቃል ተጠቅመው በርካታ ክስ ሲያቀርቡ አይተናል። ዛሬ አብን ሲተች የበርካታ ሚዲያዎችን ዘገባ ገመገምን የሚሉት የቦርዱ ሃላፊዎች ኦነግ ኦነግ ሲባል እንዴት ሳይሰሙ ቀሩ? ጠቅላይ ሚኒስትርን ያህል ስልጣን ያለው መሪ “ኦነግን ተባብረን ማጥፋት አለብን” ካለበት ንግግርና ሁለት እዚህ ግባ የሚባል influence የሌላቸው የኦሮሚያ ሃላፊዎች አብንን ከተቹበት ንግግር የትኛው ነበር መግለጫ የሚያስፈልገው? መልሱን ለቦርዱ ትተናል። ፓርቲዎች ላይ ስለተሰነዘረ ትችትና ማስፈራሪያ ማውራት ለኦነግና ኦፌኮ ቅንጦት ነው። ያላግባብ የታሰሩ አባላትና አመራሮቻቸው አራት አምስት ጊዜ እንዲለቀቁ በፍርድ ቤት ታዞ ፖሊስ አልለቅም ሲል አይቶ እንዳላየ የሚያልፍ ቦርድ ለማስፈራሪያ ንግግሮች መግለጫ ያወጣል ተብሎ አይጠበቅም።

#AskNEBE #ምርጫቦርድንይጠይቁ በሚል ርእስ የማህበራዊ ሚድያ በተዘጋጀው የተሳትፎ መድረክ ላይ የተጠየቁ ጥያቄዎች በምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ መልስ እየተሰጠባቸው ነው


Amaarenyaa kana dubbisaa