ምርጫ ቦርድ በኦነግ አመራሮች መሃል የተከሰተውን እሰጣገባ የዳኘበት መንገድ ጥሩ ነው ብዬ አምናለሁ።

ምርጫ ቦርድ በኦነግ አመራሮች መሃል የተከሰተውን እሰጣገባ የዳኘበት መንገድ ጥሩ ነው ብዬ አምናለሁ።

የብልጥግና ኤጀንቶች በተለያየ መንገድ ጣልቃ ለመግባት መሞከራቸው የማይቀር ቢሆንም ያንን መከላከል ቢቻል የፓርቲው አባላት አመራሮቻቸውን ራሳቸው እንዲመርጡ መደረጉ ጥሩ ነው። ከሁለቱም ወገን በወሳኔው ላይ ተቃውሞ የቀረበ አይመስለኝም። ውሳኔው ፍትሃዊ የሚሆነው ግን በእስር የተጓደሉ አባላትና አመራሮች ተለቀው ጉባኤው ላይ መሳተፍ ከቻሉ ነው።
 
ወሳኔው ላይ ግን አንድ ቀልብ የሚስብ አገላለፅ አለ። “የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት እስከሚቀጥለው የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ድረስ ከሃላፊነታቸው ታግደው እንዲቆዩ የተወሰነው ውሳኔ ስብሰባው በትክክል መካሄዱን የሚያሳይ #ቃለጉባኤ የሌለው፣ ምን ያህል #የምክር_ቤት አባላት እንደተሳተፉበት እና በምን አይነት #ድምጽ_አሰጣጥ መሆኑን የማያሳይ በመሆኑ ህጋዊ ተቀባይነት የለውም” ይላል።
 
መረጃው ካልቀረበ ቦርዱ ይህን ማለቱ ስህተት ነው ብዬ አላምንም። ነገር ግን ባለፈው የኦሮሚያ ብልጥግና ለብቻው ተሰብስቦ ሶስት የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን አግጃለሁ ሲል ውሳኔው በምን የህግ አግባብ ነው ተቀባይነት ያገኘው? ብልጥግና እንደ ወጥ ብሄራዊ ፓርቲ ነው። የክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች የማኮ አባላትን የማገድ ስልጣን የላቸውም። ምርጫ ቦርድ በዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ቃለ ጉባኤ አለ? ካለስ እንዴት ተቀባይነት አገኘ የሚል ጥያቄ ያጭራል። በእርግጥ ቦርዱ የታገዱት ግለሰቦች ቅሬታ ስላላስገቡ ጉዳዩን አልተመለከትኩትም ሊል ይችላል። ግን የፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ ሲጣስ ቦርዱ እያየ ቅሬታ ስላልገባልኝ በቸልታ አልፌዋለሁ ማለት ይችላል? ቦርዱ ለብልጥግና ፅ/ቤት የማኮ አባላትን ያገዳችሁበት መንገድ የፓርቲውን ህገ-ደንብ ያልተከተለ ነው ማለት አልነበረበትም? ተመልካች ደብል ስታንዳርድ እንዳለ ቢጠረጥር ይፈረድበታል? ነገሩን ነው እንጂ በምርጫ የሚመጣ ለውጥ ይኖራል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው።

1 Comment

  1. የቅኝ ገዣችን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በኦሮሚያ ጉዳይ ገብቶ የመዳኘቱ ጡሩነት በፍጹም አይታየኝም። ለቅኝ ገዢዎች እውቅና መስጠትም ሆነ ቅኝ ገዢዎቻችንን ዳኙን ብሎ በኦሮሚያ ጉዳይ ገብተው እንዲፈተፍቱ መጋበዝን አልደግፍም። ፀረ ቅኝ ገዢዎች ትግላችን እንዲጠናከር ወቦን በምንችለው አቅም በመደገፍ የኦሮሞያዊ ዜግነት ግዴታችንን እንወጣ። በ፳፩ ኛዉ ሺ ዘመን በነፍጠኞች ቅኝ መገዛትን ተቀብለን የምንኖር ወይም በቅኝ ገዢዎቻችን ሕግ የምንተዳደር ተሸናፊ ሕዝቦች መሆን የለብንም። የኦሮሚያ ነዓነት ወይም ሞት ብለን በሕብረት እንነሣ!

Comments are closed.