“ምርጫው ለምን በድቅድቁ የዝናብ ወቅት እንዲሆን ተፈለገ? ጥቂት እውነታዎች፤

“ምርጫው ለምን በድቅድቁ የዝናብ ወቅት እንዲሆን ተፈለገ?
ጥቂት እውነታዎች፤
ከሀምሌ አጋማሽ እስከ ነሐሴ 16 አካባቢ (የፍለሰታ ፆም ወቅት)
1.  በዚህ ወቅት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ በሀገሪቱ የሚዘንብበት፣ በተለይም ቀንና ለሊት እኝኝ የሚልበት ወቅት ነው፡፡

2.  መሬቱ ውሃን በመጥገቡ ምክንያት ወንዞች የሚሞሉበት፤ ደራሽ ጎርፍ የሚበዛበት ወቅት ነው፡፡ ወቅቱም በየቦታው ውሃ የሚተኛበት እና ለመገናኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ በዚህም በአንዳንድ ቦታዎች አርሶ/አርብቶ አደሩ ከብቶቹን የሚያበላበት ቦታ ስለማያገኝ ከእረሻ በሬዎች ውጪ ያሉትን እንስሳቱን ይዞ አካባቢውን ለቆ (ደረባ) ወደ ታራራ የሚሄድበት ፤ ቤተሰብ ሁለት የሚከፈልበት ወቅት ነው፡፡ አብዛኛውን የሸዋ አካባቢ ማንሳት ይቻላል፡፡ የገጠር ቀበሌዎችን መድረስና መገናኘት ይቅር እና ከአዲስ አበባ – ጅማ ያለው መንገድ እራሱ መዘጋት የሚጀምረው በዚህ ወቅት ነው፡፡

3. አርሶ አደሩ የተለያዩ አዝርእቶችን በተለይም የጤፍ መዝሪያ ዋነኛው ወቅት በመሆኑ አርሶ አደሩ ፋታ የለውም፡፡ ያ የብልግና ተወካይ እርሻ ይጠናቀቃል ብሎ እንዳወራው አይደለም፡፡ ከብልግና መንደር ቢያንስ ያገሬ ገበሬ ምን ይለኛልን እንኳን የለም፤ ፖለቲካ ብቻ፡፡

4. በአንዳንድ አካባቢዎች የተዘሩ ሰብሎች እና ቡቃያ ከአውሬ የሚጠበቅበት ጊዜ ነው፡፡

5. በአጠቃላይ የሀገራችን አርሰ አደር በዚህ ወቅት ፋታ የለውም፡፡
ስለሆነም ምርጫው በዚህ ወቅት ቢሆን፤

1) መራጮች ድምጽ የሚሰጡበት እለት በከፍተኛ ዝናብ ውስጥ ቆመው ረጃጅም ሰለፍ ተሰልፈው መጠበቅ አለባቸው፤ በመሆኑም ዝናቡ አብዛኛውን መራጭ ተስፋ በማስቀረጥ የመራጮች ቁጥርን ይቀንሳል፡፡ ከዚህ ማን እንደሚጠቀም ግልጽ ነው፡፡

2) የምርጫ ቁሳቁሶችን ፤ ድምጽ መስጫ ወረቀት እና ኮሮጆን ጨምሮ እስቀድሞ በየምርጫ ጣቢያው ማድረስ የግድ ስለሆነ፤ ከምርጫው እለት በፊት ምርጫው ተጠናቆ ኮሮጆዎች ተሞልተው በእለቱ ደራማ ለመስራት አመቺ ነው፡፡

3) ምርጫውን እንዲታዘቡ የሚደረጉት ታዛቢዎች በጭቃ ምክንያት መንገዶች ስለማይኖሩ በከተሞች አካባቢ ብቻ እንዲወሰኑ በማድረግ ያልሆነ እይታን ለመፍጠር ያግዛል፡፡ በዚህ ወቅት በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ከዋና መንገድ 100 ሜትር እንኳን በተሸከርካሪ መግባት አይታሰብም፡፡

4) “የድምጽ መስጫ ኮሮጆ“ አመቺ በሆነ መጓጓዣ ወደ ማእከል በሚፈለገው ሰዓት እና ደህንነቱ ተጠብቆ ማድረሰ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ቀድሞ የልተቀሸበ ኮሮጆ እንኳን ቢኖር ለመቀሸብ አመቺ ነው፡፡

5) የምርጫ ውጤቱን በመንገድ አሳቦ ለማዘግየት እና ብለግና የወደቀበትን አካባቢ ለማረም አመቺ ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ምርጫ ቦርዱ የሲዳምን ክልል ውሳኔ እንኳን ለማሳወቅ ምን ያህል ጊዜ እንደወሰደ ይታወቃል፡፡

ምርጫ ቦርዱም ሆነ ፅ/ቤቱ ድሮም ተአማኒነቱ ጥያቄ ውስጥ ነው፡፡ በግልጽም የብለግና እና የኢዜማ አባላት መሆናቸው ይታወቀል፡፡ ለምሳሌ ቃል አቀባይዋ ሶሊያና ሽመልስ የኢዜማ ሰው መሆንዋ ከምታደርጋቸው ብዙ ማስረጃ መቅረብ የቻላል፡፡
ባጠቃላይ የዘንድሮው መርጫ ወደ ክረምት መገፋት ድራማ ደራሲ አሻግሬ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ “ምርጫውን እናሸንፋለን፣ የመለስ ልጆች መሆናችን መዘንጋት የለበትም፡፡“ ያለውንም ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ ያዘገዩትም ሆን ብለው ነው፡፡ አሁንም በጸጥታ ማስከበር ስም በኦሮሚያ ውስጥ እየተተወን ያለው ድራም የታወቃል፡፡

ስለዚህ “ተአማኒ እና እውነተኛ“ ምረጫ ማድረግ እንኳን ባይቻል በመጠኑ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ቢያንስ የጊዜ ሰሌዳው እንዲስተካከለ ተፎካካሮ ፓርቲዎች ጠንክረው መስራት አለባቸው፡፡ ካልተሳካ ፕላን ቢ በሁሉም መስክ ከአሁኑ መታሰብ አለበት፡፡”

#Inbox

Via: Tsegaye Ararssa


ጥያቄው ሲከብድበት personal attack ጀመረ እንዴ? የልጅቷ ጥያቄ መልስ ሊሰጥበት ይገባል::