መጠጡ ሰዉዬዉን ጠጣው:-By Mekbib Gebeyehu

“መጠጡ ሰዉዬዉን ጠጣው”

By Mekbib Gebeyehu

ይህን ጆክ ሰምታችሁ ይሆናል. መጠጥ ሶስት ደረጃዎች አሉት. የመጀመሪያው ደረጃ ሰዉዬዉ መጠት ሲጠጣ ነዉ. አጣጥሞ ድንበር ሳያልፍ የሚጠጣበት ደረጃ ነዉ.”መጠጥ ለጫወታ”. በዚህ ደርጃ መጠጡ ሰዉዪዉን ይጠጣዋል ብሎ የሚያስብ ብዙ አይሆንም. ሁለተኛዉ ደረጃ መጠጡና ሰዉዬዉ የሚጠጣጡበት ደረጃ ነዉ. ሰዉዬዉ ከድንበር አልፎ ብዙ ጠጥቶአል፣ ራሱን ግን ሙሉ በሙሉ አልሳተም. “ሰዉዬዉና መጠጡ ተጣጡ” ይላሉ. ይህ ደረጃ መጠጡና ሰዉዬዉ የሚጠጣጡበት ደረጃ ነዉ. ሶስተኛዉና የመጨረሻዉ መጠጡ ሰዉዬዉን የሚጠጣበት ደረጃ ነዉ. “መጠጡ ሰዉዬዉን ጠጣዉ” በሚል ይቀለዳል.
 
አቢይ አህመድ ቄሮ ተሸክሞት ወደ ስልጣን ሲመጣ ከመጀመሪያው ደረጃ ጋር ይመሳሰላል. ጫወታዉ ቢያንስ በንግግር ደረጃ ያምር ነበር. ለማስታወስ ያህል “መግደል መሸነፍ ነዉ፣” “ያለ ህዝብ ፍላጎት ስልጣን ላይ መቆየት አልፈልግም፣” “አጣርተን እንጂ ሳናጣራ አናስርም” “አሳዳጅም ተሰዳጅም አይኖርም” “የኛ መንግስት ተረርስት ነበር” ወዘተ ወዘተ. ብዙ መዘርዘር ይቻላል. በዚህ ጊዜ የአቢይን ንግግር ጥያቄ ዉስጥ ያስገባ ጥቂት ሰዉ ነዉ. አቢይ ትያቄ ምልክት ዉስጥ የገባዉ ልክ እንደጠጪዉ ሰዉዬ ስልጣን ጥሞት ብዙ ማስገብገብ ሲጀምር ነበር. ከጋራ ጉዋደኞቹ ጋር ቅራኔ ዉስጥ ገባ፣ ምን ጊዜም አንድ ነን እያለ እነ ለማ ማጋርሳን አባረረ፣ በቀላሉ ሊወገድ ወይም ቢያንስ ማሳነስ የሚቻለዉን ቅራኔ [ለምሳሌ ከ ኦነግ፣ ክወያኔና ክደቡብ ክልሎች ጋር] ወደ ከባድ ጥል ለወጠዉ. ይህንን ለማቆም ብዙ ውይይቶች ምክክሮች ተካሄደዋል. ትንሽም ቢሆን ባላንስ ነበር. “መጠጡና ሰዉዬዉ ተጠጣጡ ከሚለዉ ደረጃ ጋር ይመሳሰላል.
 
ዛሬ አቢይ ሰክሮአል. መጠጡ ሰዉዪዉን ጠጥቶታል. በጭንቅላቱ ማሰብ አቅቶታል. ከሰከረ ጭንቅላት መልካም ነገር አይጠበቅም. ለምሳሌ፡
1. በጭንቅላቱ የሚያስብ ሰዉ በራሱ ዜጋ ላይ ጦርነት ክፍቶ “አሸነፍኩ” ብሎ አያቅራራም.
በሰመነኞች [እሪትረያ፣ ትግራይ አማራ} መካከል ያለዉ ጥል ዘመናትን ያስቆጠረ ነዉ. በኤሪትራና በትግራይ መካከል ያለዉ መናናቅና መጠላላት ለባድሜ ጦርነትነ ለብዙ ሰዎች ሞት ምክንያት እንደሆን የሚታወቅ ነዉ. እሪትረያኖች ትግራዮችን ይንቃሉ. ነገሩ ገና ጥንት ጀምሮ ትግሪያኖች በኤሪትሪያኖች ቤት እንዳገልጋይ ይሰሩ ስለ ነበር ነዉ የሚሉ አሉ. ይህን ግንኙነት መግልጽ ይህ ቦታዉ አይደለም.
አማራ ከትግራና ኤሪትሪያ ጋር ያለዉም ጥላቻ፣ መናናቅና ቅናት ብዙዉ የሚረዳ ይመስለኛል.
አቢይ በስካር አአምሮ ከፈጸማቸዉ ትላልቅ ስህተቶች አንዱ በዚ ቅራኔ ዉስጥ ወግኖ አንዱን ይዞ አንዱን መምታቱ ነዉ. ኢሪትሪያንና አማራን ይዞ ትግራይን መትቶአል. ይህ የራሱ የሆነ ግምገማ የሚኖረዉ ለዚያ አከባቢ ሰላም ትልቅ ሚና የምጫወት ድርጊት ነዉ. የኤሪትሪያ ሌላ ሃገር መሆንና የአቢይ በሌላ ሃገር ተረድቶ የራሱን ዜጋ መፍጀት ደግሞ የበለጠ ያስገርማል.ስካር ዉስጥ ያለ አአምሮ ነዉ. !!
 
2. በፖለቲካ ኤሊቶች መካከል የሚኖር ቅራኔ አያስገርምም. በኢትዮጵያ ዉስጥ የብሄርና የማንነት ጥያቄ ሁል ጊዜ ነበር፣ ጥያቄዉ እስካልተፈታ ይቀጥላል. አቢይ አህመድ በሰከረ አአምሮዉ ይህ ጥያቄ ወደ ጎናዊ ግጭት [horizontal conflict ] ክፍ አድርጎታል. ህዝቦች አማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሞ፣ ጉሙዝ ወዘተ በመጥፎ አይን እንዲተያዩ አድርጎአል. ለመተላለቅ አመቺ ሁኒታን ፈጥሮአል. ይህ የሰከረ አአምሮ ስራ ነዉ.
 
3. ይህ ሁሉ ሃቅ እያለ አቢይ ራሱን ለምርጫ እያዘጋጀ ነዉ. ተውዳዳሪዎችን አስሮ ከማን ጋር ተወዳድሮ እንደሚያሸንፍ ሁሉም ያውቃል. ድንቄም ምርጫ! ይህም ከሰከረ ጭንቅላት እንጂ ከሌላ አይጠበቅም. ሳይሰክር “ህዝብ ካልመረጠኝ ስልጣን ላይ መቆየት አልፈግም” ያላትን ያሳስታዉሰናል.
አቢይ አህመድ ዛሬ መጠጡ እንደጠጣዉ ሰዉዬ ሁኖአል. በጭንቅላቱ ማሰብ አልቻለም. የዚህን አይነት ሰዉ በተገኘዉ አጋጣሚና ሃይል ተዋግቶ ከዚያ ማባረር የጉዳቱን መጠን ይቀንሳል.
“የጀርባ አጥንቱ ሲመረመር” ይል ነበር ደርግ. ለነገሩማ የአቢይን ማንነት እየተረዳን ስንመጣ [ወሸቱን፣ ክህደቱን፣ ጭካኔዉን] አቢይ የሚዘመትበት እንጂ የሚያዘምት መሆን አልነበረበትም. አቢይ አህመድና ዛሬ ባከባቢዉ የተሰገሰጉት ሁሉ ከወያኔ ያላነሱ ወይም ደግሞ የባሱ ወንጀለኞች ናቸዉ.