መደመርና መደመር (ደ ይጠብቃል)እና በጅምላ መደርመስ!

መደመርና መደመር (ደ ይጠብቃል)እና በጅምላ መደርመስ!

ይህ የአብይ አህመድ አመለካከት ነው፡፡ የብሄር ፌደራሊዝምን ለማፈራረስ ሌት ተቀን ተግቶ እየሰራ ያለው አብይ አህመድ ዓሊ ኦሮሞውን ከኦሮሞው ጋር እስከ ማቃቃር የሚደርስ አስከፊ ስራዎችን መስራቱን ቀጥሎበታል፡፡ «የሃረርጌው ኦሮሞ ለሱማሌው እንጂ ለወለጋው ምኑም አይደለም» የሚል አስተሳሰብ የሚያራምድ ሰው ነው አቢይ፡፡ የከፋፋይነት መሰረታዊ መገለጫ ነው፣ ይህ አስተሳሰብ፡፡ በእርግጥ ከአስተሳሰብነት ደረጃ አልፎ በተግባር በሚገለጽ ደረጃ ዕውን ማድረጉን ጀምሮታል፡፡ ይህ አስተሳሰብ ጋምቤላዊው ለሱዳናዊ እንጂ ለኢትዮጵያዊው ምኑም አይደለም እንደማለት ነው፡፡ የአብይ ታላቅዋ ልጅ ለታናሽ እህቷ ምኗም አይደለችም እንደማለትም ነው፡፡

እኛ ግን እንላለን፣ እንደ ኦሮሞነታችን በኦሮሞነታችን ያጣነው ብዙ ነገር እንዳለ ሁሉ ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችም እንደኦሮሞው ሁሉ የተገፉባቸው የተጫኑባቸው መከራዎች እንዲገፈፉ በብሄር ማንነት ያጡትን በብሄር ትግል ይመልሱታል የሚል አመለካከት አለን፡፡ ፍትህ እኩልነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ስርዓት በትክክል ዕውን ከተደረገ ብዝሃነት ዕሴት እንጂ ተግዳሮት አይሆንም የሚል መርህን እንከተላለን፡፡ ሀቁን እንይ ብንል ኦሮሞ ገፊ አይደለም፤ ተገፊ እንጂ፡፡በባህልም በማህበራዊ ትሥስርም ከኦሮሞና ከኦሮሚያ የበለጠ አቃፊ ማህበረሰብ ካለም የፒፒው መሪ ቢጠቁሙን መልካም ነበር፡፡

የፒፒው ንጉስ የኢዜማን ርዕዮት ለማስፈጸም ከፈለጉ ለራሳቸው፣ አለዚያ ከሚቀበላቸው ቡድን ጋር ሆነው ወደ ኢዜማ መጠቅለል (ጠ ይጠብቃል) ወይ ኢዜማን መጠቅለል መብታቸው ነው፡፡ ለማንኛውም እስከምርጫው ማግስት ህዝቡን ቢታገሱት ጥሩ ነው፡፡ እስከዚያው ድረስ በየዕለቱ በሚፈበርኩት ከፋፋይ አጀንዳ ህዝቡን ከማባላት ሰላም እንዲወርድ ተግተው ቢሰሩ ለእሳቸውም ለህዝቡም ለሃገሪቷም የወደፊት ጉዞ ብሩህ ይሆናል፡፡

ከፌደራሊስቶች ጋር ጉዞ የተረጋጋች በፍትሃዊነት በደሞክራሲና በኢኮኖሚ ዕድገት የመጠቀች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ይረዳል፡፡ አቢይ አህመድ አሊ እንደሚለው ብዝሃነት ተግዳሮት አይደለም፣ ዕሴት እንጂ፡፡ ብሄርንና ብሄረተኝነትን መደርመስ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም፣ ብሄረተኛ አይደለንም የሚሉት እንኳን በአፍ እንጂ በተግባር ለማንና ለምን እንደቆሙ በሚገባ እናውቃለንና፡፡


የዶ/ር አብይ ኢትዮጵያ ሚሌንየም አዳራሽ፣ ኢንተርናሽናል ሆቴልና ሸገር መሆኗን እያረጋገጥን ያ.ሁ.ኖ.ያ… አራዳና ከተማ ቀመስ ፖለቲከኛ ይሉሀል ይህ ነው… በዚህ አካሄድ 80% ህዝባችን ተረስቷል ማለት ነው፡፡

ዩንቨርሲቲዎች ይዘጋሉ
ዜጎች በገፍ ይጨፈጨፋሉ
ምሁራን በአቋማቸውና በማንነታቸው ምክንያት ታስረው ይሰቃያሉ
የኑሮ ውድነቱ ጣራ ነክቷል
ሰዎች በአቋማቸውና በማንነታቸው ምክንያት ከስልጣን ይነሳሉ
የህዝብ ደህንነት በጣም ያሰጋል … ይህች ናት ብልጽግና፡፡

~by Netsanet Burka.


Carraan Oromoo fi Oromiyaa, kan Itiyoophiyaas yoota’e harka jaarmiyaalee hawwii sabboontummaa Oromoo fi dhukkuba Oromoo keessaa dhalatanii jira. Kotteen ‘mootummaa qubattootaa fi dallaalotaa’ Oromiyaa dhoqqeessuun jabina Ashaagree irraa kan dhalate miti, laafina jaarmiyaalee qaqqaalii kanaati. Jabinni jaarmiyaalee kanaa jabina Oromooti, laafinni isaaniis akkasuma. Kanaaf didnee wajjin rincicna, kanaaf jiraa ormaa mannaa du’aa isaanii filanna. #Abiy_Must_Go

Etana Habte