የሕዝብ ተወካዮች አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ የሥራ መልቀቂያ አስገቡ

ዝብ ተወካዮች አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ የሥራ መልቀቂያ አስገቡ

አባዱላ ገመዳ

ሰበር ዜና ፖለቲካ

የሕዝብ ተወካዮች አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ የሥራ መልቀቂያ አስገቡ

(ethiopianreporter)—የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ ባልተጠበቀ ሁኔታ የሥራቸውን መልቀቂያ ለኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አስገቡ፡፡

አቶ አባዱላ መልቀቂያውን ለኢህአዴግ አስፈጻሚ ኮሚቴ የዛሬ 15 ቀን አካባቢ ያስገቡ ሲሆን አስፈጻሚ ኮሚቴውም መልቀቂያቸውን ተቀብሏቸዋል፡፡

ለፓርላማው በጣም ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት አፈ ጉባዔው መልቀቂያውን ካስገቡ በኋላ እስከትናንት ድረስ በሥራ ገበታቸው ላይ የነበሩ ሲሆን የፓርላማው የአመቱ የሥራ ዘመን መክፈቻው ላይ ሰኞ መስከረም 29 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚኖሩ ታውቋል፡፡

በፓርላማው አሠራርና ሥነ ምግባር ደንብ መሰረት መልቀቂያው ለፓርላማው ምልዓተ ጉባዔ ይቀርብና ኢህአዴግ ለፓርላማው የሚያቀርበው እጩ በቦታው ይሾማል፡፡


Oromia Media Network’s live video.