መታየት ያለበት አስደናቂና አስተማሪ ቃለ-መጠይቅ!የአድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ዶ/ር አብዱዋሳ

 መታየት ያለበት አስደናቂና አስተማሪ ቃለ-መጠይቅ!የአድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ዶ/ር አብዱዋሳ አብዱላሂ ዛሬ ላለንበት ችግር እንዴት ሊንደርስ በቃን በሚል አስገራሚ ማብራሪያ ሰጥተዋል

Rajo

መታየት ያለበት አስደናቂና አስተማሪ ቃለ-መጠይቅ!
የአድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ዶ/ር አብዱዋሳ አብዱላሂ ዛሬ ላለንበት ችግር እንዴት ሊንደርስ በቃን በሚል አስገራሚ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በዝህ አጭር በሆነ ቃለ-መጠይቃቸው ብዙ አስገራሚና አስደንጋጭ መረጃዎችን ስለአብዲ ኢሌ ሰጥተዋል፡፡ በዝህ አስር አመት አብዲ መሪ ሆኖ ክልሉን ሲመራ በዓለም ካሉት ንጉሳውያን ቤተሰቦች በተለየ ሁኔታ ያሻውን እንዲያደርግ የተፈቀደለት ብቸኛ ሰው ነው ይሉናል፡፡ አብዲ ማለት ሲሻው የሚያስር፣ የሚገድልና የሚደፍር ሰው ነው፡፡ የሚሰራውን ደግሞ ጠንካራ መንግስት እንደሆነ የሚታመነው ፌዴራል አያውቀውም ማለት ደግሞ ይከብዳል ብለው ሀቋን ተናግረዋል፡፡ አይተው ያላዩበት፤ ሰምተው ያልሰሙበት ጅግጅጋ ሲሄዱ በቦርሳ ሙሉ ብር አሸክሟቸው ስለሚመለሱ ይሆን? ብለው ምሁሩ ይጠይቃሉ መልሱንም ለኛ ይተዉልናል፡፡ አብዲ በመቶ ሺህ ብሮች በመኪናው ውስጥ አድርጎ የሚያድል መሪ ነበር፡፡ ማን ይህን እንድያደርግ ፈቀደለት? አብዲ አንድን ጎሳ ወደራሱ ደጋፊነት ለማምጣት ሲሻ ምን ይገደዋል-ወረዳ ይሰጣቸዋል፡፡ በጀት ከዬት ይመጣል የለ ሌሎች ታሳቢ የሚደረጉ ነገሮች ግምት ውስጥ አይገቡም እሱ የፈለገው ይሆናል፡፡ ይህን ቃለ-መጠይቅ ሲትሰሙ ራሳችሁን መጠየቅ ያለባችሁ ዋንኛ ጥያቄ የሱማሌ ክልል በእርግጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ነበረችን? ወይስ ለሱማሌ ክልል የሚትተዳደርበት ለብቻዋ የሆነ ቻርተር ነበራት? በኢትዮጵያ ህገ-መንግስት የበላይነት ሥር ትተዳደር ከነበረ አብዲ ኢሌ ላለፉት አስር ዓመታት ህገ-መንግስቱ ላይ ሲጨፍርና ህዝቡ የፍትህ ያለህ ሲል የኢትዮጵያ መንግስትና ሌላው ህዝብ ዬት ነበረ? ስለዝህ ዛሬ እንድህ ለዘቀጥንበት ደረጃ ሊንበቃ የቻልነው በአብዲ ኢሌ የክፋት ሥራ ብቻ አይደለም -ተጠያቂዎቹ ብዙ ናቸው ብለው ምሁሩ ይናገራሉ፡፡ ተጠያቂዎቹ ማን እንደሆኑ ከግዜ ጥበት አኳያ ለመናገር ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሰፊ ዝግጅት በማድረግ ዶ/ር አብዱዋሳ አብዱላሂ ሰፋ ያለ ማብራርያ እንድሰጡ ማድረግ የግድ ይለዋል፡፡ እንድህ ነካክተውን ማምለጥ አይቻልም!


ማሳሰቢያ!
የቀድሞው አራጅ መሪ አብዲ ኢሌ ርዥራዥ ባለስልጣናትና ሄጎ የተሰኘው አደገኛ የቦዘኔዎች ቡድን “አብዲ ኢሌን እንፈልገዋለን ከእስር ይፈታልን” በማለት በጅግጅጋ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እየተዘጋጁ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ቀብዮ በሚባለው ሆቴል ተሰብስበው በእቅዳቸው ላይ እየተወያዩበት ይገኛሉ፡፡ ሰላማዊ ሰልፉ በዋናነት እያዘጋጀ ያለው የሱማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፈርሃን ናቸው፡፡ እኝህ ኮሚሽነር በቱለጉሌድ አካባቢ በጃርሶና ገሪ ጎሳዎች ለተቀሰቀሰው ግጭትና ሁከት በማስተባበር የሚታወቁ ሰው ናቸው፡፡ ሰላማዊ ሰልፉ ሁከትና ረብሻ ለመፍጠር የታለመ እንደሆነ ምንጮች ለረጆ አሳውቀዋል፡፡

ነገሮች እስኪሰክኑ ድረስ የመከላከያ ኃይሉ እንድህ ያለውን ሰላማዊ ሰልፍ መፍቀድ የለበትም፡፡ ካለበለዝያ ከተማዋ እያገኘች ያለውን ሰላሟን ታጣለች “ግርግር ለሌባ ያመቻል” እንድባል ሁለተኛና ሦስተኛ ዙር የንብረት ዘረፋ እንድሁም የንፁሃን ሰው ክቡር ህይወት ይጠፋል ልክ እንደቅዳሜው ማለት ነው፡፡ መከላከያ እነዝህን የጥፋት መልዕክተኞችን ዓላማቸውን እንዳያሳኩ ከኅብረተሰቡ ጋር በመተባበር ማቆም ይጠበቅበታል!


Ethiopia: አብዲ ኢሌ ታሰረ ወይስ አልታሰረም? ጽዮን ግርማ በቪኦኤ ያሰራጨችው ግልጽ ያለ ዘገባ.