መተከል:እያለቀ ያለው ማን ነው? #ምክንያቱስ?

መተከል:እያለቀ ያለው ማን ነው? #ምክንያቱስ?

By Temesgen Gemechu

(oromedia)–በዚህ ሰዓት ለስሙ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ይባላል እንጂ መተከልን እያስተዳደረ ያለው የአማራ ክልል ብልጽግና ከሆነ ውሎ አድሯል ፣ ኮሽታ በተፈጠረ ቁጥር የቤንሻንጉሉ ፕሬዝዳት አሻይዲሊ እንዴ ሎሌ በደቂቃ ውስጥ ባህርዳር ይጠራል ስራዎች የሚገመግሙ ባህርዳር ሰማዕታት ሐውልት መታሰቢያ አዳራሽ ነው ።

እንዴ ራያ ወልቃይት ሁሉ መተከል የአማራ ነው የሚለው የአማራ ፖለቲካ ልሂቃን አስተሳሰብ እውን ለማድረግ ክልሉ አጀንዳ ቀርጾ መንቀሳቀስ ከጀመረ ውሎ አድሯል ፣ ይህንን ጥያቄ እውን ለማድረግ ከባለ ሃብት እስከ ባለሥልጣን ሌቴ ቀን በስውር እየሰሩ ይገኛሉ ፣ ለዚህ መሳካት ደግሞ የብልጽግና መመስረት ከፍተኛ አጋጣሚ ፈጥሯል ከመንግሥት ባለሥልጣናት ምክትል ጠቅላይ ሚንስቴር #ደመቀ_መኮንን እና #የሰላም_ሚንስቴር ደታ Dr #ስዩም መስፍን ስዩም በፀጥታ ስም ጨዋታውን በግንባር ቀደምትነት እየተጫወቱ ይገኛሉ እኒህ ባለሥልጣን የአካባቢው ተወላጅ ጭምር ስለሆኑ ሕዝቡን በቀላሉ እያደራጁ ጭምር ሥራውን እየሰሩ ይገኛሉ ፣ግጭት በተፈጠረ ቁጥር እንዴ ትልቅ አጋጣሚ ይጠቀማሉ።

ለምሳሌ 100 ሰው በግጭት ከተፈናቀለ መልሶ ማቋቋም በሚል የአማራ ክልል መንግሥትና ባለሃብቱ ሌላ 100 ሰው ጨምረው 200 ሰው እንዴ አዲስ ያሰፍራሉ ።
ከወርቁ አይተነው ጀምሮ ትላልቅ የብልጽግና ደጋፊ የአማራ ባለሃብቶች በኢንቨስትመንት ስም ሰፋፊ መሬትእየተሰጣቸው ነው ። ለኢንቨስትመንት ታስቦ ቢሆን መልካም ነው ግን አይደለም ዋና ዓላማው በሠራተኛ ስም ሰፊ የሰው ሃይል ከአማራ እያመጡ እዛው ማስፈር ነው ፣ ይህንን መንገድ ሕወሐት ህዳሴ ግድብ እንደተጀመረ በሰፊው ተጠቅሞ ነበር የህዳሴ ግድብ ተፈናቃይ ተብለው ጭምር ካሳ መውሰዳቸው የቅርብ ዓመት ትዝታ ነው። ዛሬም የአማራ አመራሮች ያንን መንገድ እየተከተሉ ይገኛሉ ዛሬ መተከል እየገቡ ያሉት የአማራ ባለሃብቶች ሠራተኛ የሚያመጡት ከአማራ ክልል እንጂ ነዋሪውን አይደለም።

መተከል ውስጥ በሰፊው የሚኖር ማህበረሰብ #ጉሙዝ ነው ፕሬዚደንት #አሻዲሊ_የበርታ ተወላጅ እንደመሆኑ መጠን ስለ አሶሳ እንጂ ስለመተከል ምንም ስሜት የለውም አሳልፎ ለአማራ እየሰጠን ነው ፣ ጃዊ ላይ ያ ሁሉ ጉሙዝ አልቆ አንድም ሰው ፍርደኛ ያልሆነ ለኛ ተቆርቃር ስለሌለ ነው የሚል አብዛኛው የጉምዝ ብሔር ተወላጅ የብልጽግና አመራር ወጣቱ የተማረው ያልተማረው እያጉረመረመ ይገኛል።

ለዚህም መፍትሔ ብለው የተከተሉት ከመከላከያ ከፌዴራል ፖሊስ የተመለሱ ተጠባባቂ መከላከያ ሚሊሻ የነበሩ የጉምዝ ተወላጆችን አደራጅቶ ውስጥ ለውስጥ የገንዘብ የመሳሪያ ድጋፍ በማድረግ በቀለም ከእነሱ የተለዩ የጉምዝ ቀለም የሌላቸውን ብሔር ላይ ጥቃት በማድረስ ከዞኑ ማስወጣት የሚል መርህ በመከተል ገለው እየሞቱ ይገኛሉ።

የእልቂቱ ሰለባ ማን ነው?

ለስሙ አማራ ተባለ እንጂ መተከል ዞንን የሚያዋስነው የአማራ ብሔር ሳይሆን #የአዊ ብሔረሰብ ዞን #የአገው ሕዝብ ነው። ከምዕራብ ጎጃም የሚመጡ አማሮች 90% ለዓመታዊ ሥራ እንጂ ቋሚ ነዋሪ አይደሉም፣ ቤንሻንጉል ውስጥ በቋሚነት በወሰንተኝነትም በአብሮ መኖርም የሚታወቁት አገዎች ናቸው፣ የአማራ ፖለቲካ ልሂቃን እና ባለሃብቱ በሚጫወቱት ጨዋታ ከአቸፈር እና ከዳሞት የመጣው ሠራተኛ እሳት ጭሮ ሲሄድ መከረኛው ጉምዝና አገው ያለ ርህራሄ ይጨረሳል። የነሱ ፍንጣሪ ለኦሮሞ ለሽነሻ እንዲሁም ለወሎዬ ይተርፋል። አብዛኛው እልቂቱ የሚፈፀመው #በጉምዝና_አገው ላይ ነው ፣ አለቀ ተብሎ ከበሮ የምመታ ግን አማራ ነው ፣ ይሄ የፖለቲካ ቅጥፈት ጨዋታ ነው። ስለዚህ የመተከል ጉዳይ ችግር በቀላሉ የማይፈታ የጉምዝ ወይንም የአካባቢው ነዋሪ ችግር ሳይሆን የብልጽግና አመራሮች ችግርና የግዛት ማስፋፋት ችግር መሆኑን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያውቅ ይገባል።