መቃወም መብታቸው ነው፤ ግን ኢትዮጵያዊ ይህ ከሆነ እኛን አይመለከትም!

መቃወም መብታቸው ነው፤ ግን ኢትዮጵያዊ ይህ ከሆነ እኛን አይመለከትም!

ሙሉው መግለጫው ይህን ይመሰላል
 
ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም
➢ ለኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት – አዲስ አበባ
➢ ለኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር – አዲስ አበባ
➢ለምርጫ ቦርድ (አዲስ አበባ
➢ለፍትህ ሚኒስቴር (አዲስ አበባ)
➢በኢፌዴሪ ፓርላማ ለህዝብ ተወካዮች (አዲስ አበባ)
➢ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ-ዋሽንግተን ዲሲ
➢ ለሕብር ሬዲዮን ጣቢያ-ሰሜን አሜሪካ
➢ ለኢትዮ360 ሚዲያ-ሰሜን አሜሪካ
➢ ለአባይ ሚዲያ-አዲስ አበባ
➢ ለአዲስ ድምፅ ሬዲዮ–ሰሜን አሜሪካ
➢ ለርዕዮት ሚዲያ – ስሜን አሜሪካ
➢ ለሚዛን ቴሌቪዥን-ሰሜን አሜሪካ
➢ ለምኒልክ ቴሌቪዥን-ሰሜን አሜሪካ
➢ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ/-ሰሜን አሜሪካ
➢ ለመረጃ ቴሌቭዥን ጣቢያ-ሰሜን አሜሪካ
➢ ለዘመድኩን በቀለ-መረጃ ቲቪ-ጀርመን
➢ ለኢቲቪ-አዲስ አበባ
➢ ለአማራ ቡዙሃን ሚዲያ ኤጀንሲ-ባህርዳር
➢ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ጣቢያ-ሰሜን አሜሪካ
➢ ለጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ጣቢያ -ጀርመን
➢ ለዘሃበሻ-ሰሜን አሜሪካ
➢ ለኢትዮጵያ አንድነት ሬዲዮ-ስዊድን
➢ ለርዕዮት ቲቪ-ሰሜን አሜሪካ
➢ ለአደባባይ ሚዲያ-ሰሜን አሜሪካ
➢ ለኢትዮ-ቤተሰብ ሚዲያ-ሰሜን አሜሪካ
➢ ለመረጃ ሚዲያ-ሰሜን አሜሪካ
➢ ለፍትሀ መጽሄት-አዲስ አበባ
➢ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል ለምትሉ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች በሙሉ-ባላችሁበት
➢ ለሀገር ወዳድ ማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች-ባላችሁበት
➢ ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ
—–
ጉዳዩ:- የኢትዮጵያን ኅልውና አደጋ ላይ የጣሉት ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ስልጣናቸዉን ይልቀቁ!!
——
የኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት ዋና መሰናክል ጠ/ሚ አብይ አህመድ ናቸው። ጠ/ሚሩ እውነተኛ ማንነታቸውን ለመደበቅ ሲሉ ብቻ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ የሚለውን ማራኪ ሥነቃል በተለያዩ መድረኮች ይጠቀሙ እንጂ ከፍተኛ የሕይወት መሰዋዕትነት የተከፈለበትን የሥርዓት ለውጥ ትግልና ሂደት ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ በማደናቀፍ አልፎም የለውጡ መሀንዲስና መሪ የሆኑትን እነ አቶ ገዱንና ዮሀንስ ቧያለውን ጨምሮ ሌሎች ቁልፍ መሪወች ከስልጣን በመግፋትና ፍፁም ገለሰባዊ አምባገነን ስርአትን በመፍጠር ላይ የተጠመዱ መሪ በመሆናቸው ከፍተኛ ድጋፍ ሰጥቷቸው በነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ታላቅ ክህደት ፈጽመዋል።
 
በመሆኑም በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የዘር ፍጅት (Genocide) እና የዘር ማጽዳት (Ethnic Cleansing) ወንጀሎች እየተካሄዱ ነው። በአንድ ሳምንት ብቻ በመተከል ከሰባት መቶ በላይ ንጹሃን ዜጎች በዐማራነታቸዉ/በአገዉነታቸዉ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፤ ከሁለተ መቶ ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ያለ ጠባቂና አይዟችሁ ባይነት በአልባሌ ቦታ ወድቀው የገዳዮቻቸውን የጭካኔ እርምጃ ይጠብቃሉ። ይህም በመሆኑ የዘር ፍጅቱ እና ዘር ማጽዳት ወንጀሎችም አሁንም ተጠናክረው ቀጥለዋል። ይሄም ጭፍጨፋ አልበቃ ብሎ ክቡር የሆነዉ የሰው ልጅ አስከሬን በጅምላ እንደ ቆሻሻ በግሬደር እየተገፋ እንዲወገድ ተደርጓል።
 
ይሄም የወንጀል ድርጊት ከኢትዮጵያዊነት፣ ከክርስትና፣ ከእስልምና ከአይሁድነት ሃይማኖታዊ ድርጊቶች ወይም ከማንኛውም የዓለም እምነት ያፈነገጠ እና የረከሰ አረመኒያዊ ድርጊት እየተከናወነ ያለው ጠ/ሚሩ በሚመሩት በብልፅግና መንግስት ተባባሪነት ነው። እዚህ ላይ ቅድሚያ ግንባዝቤ ሊያዝበት የሚገባው ጉዳይ ልክ እንደ ኢህአዴግ የትህነግ ዘመኑ ሁሉ የብልፅግና መንግሥት “የኦሮሙማ ጭምብል” መሆኑ ልብ ይላሉ።
የዜጎችን ደኅንነት ቅድሚያ ሰጥቶ የመጠበቅ ግዴታ ያለበት መንግሥት ሆኖ እያለ በፀረ ኢትዮጵያዊነቱ የሚታወቀው ኦነግ “ኦነግ ሸኔ” የሚል የዳቦ ስም ወጥቶለት ከ19ኝ በላይ ባንኮችን በጸራራ ፀሓይ እንዲዘርፍ እና ለንጹሃን መጨፍጨፊያ የሚውል ወታደር እንዲያሰለጥን ሲደረግና በተፈናቃዮች ስም የተላከን እርዳታ ጭምር በተቀናበረ መልክ እንዲዘርፍ ተደርጓል። ሕዝብ በርሃብ እንደ ቅጠል እንዲረግፍ ከማድረግ ባሻገር ይሄው አማፂ ኃይል በጅምላ የመጨፍጨፍ ጉልበቱ ይበልጥ እንዲበረታ እየተደረገ ነው። በወለጋና በመተከል እየተከናወነ ያለው የዘር ፍጅትና የዘር ማጽዳት ወንጀሎች መጀመሪያም በአብይ ጉዳይ አስፈፃሚዎች በኢትዮጵያ ሱሴ ለማ መገርሳ፣ በሽመልስ አብዲስና አሻድሊ ሃሳን በኩል ሲከናወን ይቆይ እንጂ የዘር ፍጅቱና የዘር ማጽዳቱ ወንጀል ተባብሶና የጭካኔውን ዓይነት ጨምሮ በጠ/ሚሩ ቀጥተኛ ትዕዛዝ እየተካሄድ መሆኑ ገሃድ ሆኗል።
 
በብልፅግና ስም ባህር ዳር ላይ ያለው ብአዴን ልዩ ኃይል ወደ መተከል ልኮ ለወገን እንዳይደርስ ጠ/ሚ አብይ አግዶ ሕዝብ ማስጨፍጨፉ ሳያንስ አሁን ደግሞ ሱዳን ድንበራችን ስትደፍር ልዩ ኃይሉ ወደ ድንበር መላኩ ግልፅ የሆነ መልዕክት ያለው ሲሆን ብአዴን ይህን ትዕዛዙን በጸጋ በመቀበሉ የዘር ፍጅቱና የዘር ማጽዳቱ ወንጀሎች ቀጥሏል። ይሄም የሚያሳዬዉ ብአዴን የአማራ/አገዉ ማኅበረሰብ በርስቱና በቀየው ላይ ግድያና ማፈናቀል ሲፈጸምበት እጁን አጣጥፎ መቀመጡ ለወንጀሉ መፈጸም ፈቃደኛ ከመሆን አልፎ ጉዳይ አስፈፃሚ ጭምር ስለሚያደርገው በወንጀሉ ላይ በቀጥታ ተሳታፊ መሆኑን ልብ ይላሉ። በተመሳሳይ ሁኔታ አጠቃላይ በብልፅግና ፓርቲ ውስጥ የተሰባሰቡ ልዩ ልዩ የየክልሉ ፓርቲዎችም እንደ ብልፅግና መንግሥት አካልነታቸው እነሱንም በሕግ ተጠያቂዎች ያደርጋቸዋል። በተለይም ደግሞ ይህን በጠ/ሚ አብይ አህመድ መር የሆነን የተቀነባበረ የዘር ፍጅትና የዘር ማጽዳት ወንጀሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች በሰላማዊ መንገድ ለመቃወምና ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ ለመሆን በተለያዩ ጊዜያት በጠ/ሚዉ ትዛዝ ብአዴን ተደጋጋሚ አፈና ማካሄዱ እጅግ በጣም ይቆጫል።
 
በአሁኑ ሰዓት ከወለጋ እና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብቻ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከሰባት መቶ ሽህ በላይ እንደሚሆን የተለያዩ ምንጮች እያሳዩ ሲሆን እነዚህ ተፈናቃዮች በጎዳና፣ በጫካ እና በልዩ ልዩ ቦታዎች ተበትነዉ ይገኛሉ። ቀሪዎችም የአውሬ እራት ሆነው በእየጫካው ቀርተዋል። ከሞት የተረፉ ተፈናቃይ ዜጎችን መንግሥት ተብዮው መልሶ የማቋቋም ግዴታዉን መወጣት ሲገባው ይባስ ብሎ ሕይወታቸው በጨፍጫፊዎች እጅ እንዲወድቅ ሁኔታዎችን ሲያመቻች ይስተዋላል። የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው ተመልሰው መቋቋም ባይችሉ እንኳን በርሃብ እንዳያልቁ የዕለት ጉርስና አልባሳት ድጋፍ እንዳይደርሳቸው ትልቅ መሰናክል ከመሆኑ ባሻገር በዳቦ ስም በሚጠሩት በኦነግ ሸኔ ሁኔታዎች አስቸጋሪ እንዲሆኑ ተደርጓል። በዚህም የዘር ፍጅቱ ወንጀል ዒላማ እንዲሆን የተደረገው ሕዝብ በርሃብ፣ በብርድና ኮሮናን ጨምሮ በልዩ ልዩ በሽታዎች እንዲያልቅ ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጧል። ብልጽግና የሚመራዉ መንግስት ከኦጋዴንና አካባቢው ኦሮሞ የሚላቸውን በገፍ አምጥቶ አዲስ አበባ ላይ ቤት ሰርቶ ሲያኖራቸው ለካድሬዎቹ ደግሞ በመቶ ሽህ የሚቆጠር የቁጠባ ቤቶች ከአዲስ አበባ ሕዝብ ነጥቆ ያደለ ከመሆኑ በላይ የራሱን ነገድ ጥቅም ለማስጠበቅ ዐይኑን በጨው አጥቦ ቢሮዎችን በራሱ ሰዎች እየሞላ ይገኛል።
 
በአጠቃላይ በቅርቡ በወለጋና በመተከል እየተፈጸሙ ያሉትን እጅግ በጣም አስጨናቂና ዕረፍት የሚነሱ ወንጀሎች አነሳን እንጂ በድፍን ኢትዮጵያ ጠ/ሚሩ ከመጡ በኋል በሐረር የአማራና የሶማሌ ነገዶች አባላት እንደ በግ ሲታረዱ፣ በጌድዮ ወገኖቻችን ላይ የዘር ማጽፋት ወንጀል ሲፈጸምባቸው፣ በአጠቃላይ ከጥቅምት እስከ ጥቅምት የዘለቀውና በተለይ ደግሞ የአጫሎ ሁንዴሳን “ሴራ አዘል” ግድያ ሰበብ አድርገው በአሩሲ፣ በምሥራቅ ሸዋ፣ በሐረር፣ በባሌ፣ በጉራፈርዳና በተለያዩ ከተማዎች ሰላማዊ ዜጎች በማንነታቸውና በሃይማኖታቸው እየተለዩ የደረሰባቸውን የዘር ፍጅትና የዘር ማጽዳት ወንጀሎች የጠ/ሚሩ መንግስት መር ወንጀሎች፣ ሀብት ንብረት ዘረፋና ቤት ንብረት ቃጠሎዎች መገለጫዎች ናቸው። ለዚህም ድርጊት ዋና ተጠያቂውም ጠ/ሚሩ ናቸው።
 
“የሌባ ዐይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ” እንዲሉ “ጉዳዩ አደገኛ እየሆነ ነውና ኃይል ይላክልን” ያሉትን የሻሸመኔ ከተማ ኃላፊዎችን እነ ሽመልስ አብዲሳ “አርፈህ ተኛ” እያሉ በባላይነት ተሰባስበው በመሩት ጭፍጨፋ እነ እስክንድር ነጋንና የባልደራስ ፓርቲ የሥራ ባልደረቦችን በወንጀል ከሰው አስረዋቸዋል። እነዚህን ንጹሃን የባልደራስ አመራሮች “የሕሊና እስረኛ” ማድረግ የአብይ መንግስት ቁልፍ ወንጀል ማሳያ ነው። እነ እስክንድርን ማሰር ማለት የኢትዮጵያ ሕዝብ አማራጭ መሪዎች እንዳይኖረዉ እየተሰራ ያለ ሴራ መሆኑን ሕዝብ በገሃድ እያየ ነው። ይሄም የአብይ መንግስት አደርገዋለሁ የሚለዉን ምርጫ የፌዝና ያው ከተለመደው የምርጫ ኮሮጆ ግልበጣ የተለየ ሊሆን እንደማይችል ማሳያ ነዉ። እናም የምርጫ ጉዳይ አስቀድሞ “የተበላ እቁብ” ከሆነ ቆይቷል ማለት ነው። ምክንያቱም ብርቱካን ሚደቅሳ የምትመራው የምርጫ ቦርድ የሚባለውም በማስመስል ስራ ከተጠመደ ይሄው ሦስት አመቱ ነው። እውነተኛ ተወዳዳሪዎች አንድም የሕሊና እስረኞች ሆነዋል፤ አልያም እንደ ወፍ ተባረዋል፣ ወይም ደግሞ ዛሬም በጫና ውስጥ ናቸው። ምርጫ ለማድረግ ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ “የራሴ የሚለው ሕገ መንግሥት” ቅድሚያ ሊኖረው የግድ ይላል፤ እውነተኛ የምርጫ ፖለቲካና ነፃ የምርጫ ቦርድ ተቋም መኖር አለባቸው። በዚህ ወቅት ምርጫ ላድርግ ማለት የኢትዮጵያን ሕዝብ እና እውነተኛ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ተጨፈኑና ላሞኛችሁ እንደ ማለት ነው።
 
ለዘመናት ተደፍሮ የማያውቀው የኢትዮጵያ ዳር ድንበር በሱዳን ወራሪ ጦር በይፋ ተጥሶና ወደ 40 ኪሎ ሜትር በላይ ዘልቆ በመግባት የኢትዮጵያ ገበሬዎችን ንብረትና ሰፊ የእርሻ ምርት እየዘረፈ፣ ሰላማዊ ዘጎችን እየገደለና ምሽግ ሰርቶ እየተቆጣጠረ ይገኛል። እንደዚህ ያለው የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንቦር ጥሶ መያዝ በየትኛውም የኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ ያልታወቀ ሲሆን የጠ/ሚ አብይ አህመድ መንግስት ከመጋረጃ ጀርባ ከሱዳን ጋር በማሴር የኢትዮጵያን ሉዐዋላዊነት እያስደፈረ ነው። በተለይም የአገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ተሿሚዎች የአንድ ጎሳ ስብስቦች መሆናቸው ከአሁን በፊት በተለያዩ ጥናታዊ መጽሔቶች የቀረበ መሆኑና በአገር ሉዐዋላዊነት ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ደባ የአብይን መንግስት የሚወክለው ዲና ሙፍቲን በኢቲቪ “እኛ ያስቀመጥነው ግልፅ እና ግልፅ precondition ወደነበራችሁበት ተመለሱ እና በግልፅ እንነጋገር” ሲል የራሱን መንግስት አጋልጧል። ምንም እንኳን የአገር ድንበር አልተደፈረም እያሉ ሲዋሹ ቢሰነብቱም እውነቱን ግን እራሳቸው በራሳቸው አንደበት አጋልጠዋል።
 
በአጠቃላይ የአገራችንን ተጨባጭ ሁኔታዎችና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊና ጥልቅ ተከታታይ ዓለም አቀፍ የዙም ውይይቶችን በማድረግ በመጨረሻም ጥር 9/2013 ዓ.ም ጠንካራ አቋም መያዝ ተችሏል። ይህንም ተከትሎ ለሁሉም የአገራችን ችግሮች ዋናውና ግንባር ቀደሙ ሰው ጠ/ሚ አብይ አህመድ ወደ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ የሥርዓት ለውጥ የሚወስደውን ሂደት ሆን ብለዉ ያደናቀፉና የዘጉ መሆኑ በሚገባ የታመነበት በመሆኑ ይህን መሰረት ባደረጉ ጉዳዮች ላይ የሚከተሉትን ዝርዝር ጉዳዮች የያዘ የአቋም መግልጫ እንደሚከተለው ወጥቷል:-
 
1. ጠ/ሚ አብይ አህመድ ይህችን ታላቅና ታሪካዊ አገር ለመምራት ለሃቅመ መንግሥት ያልበቁ፣ ኃላፊነት ጭራሽ የማይሰማቸው፣ ትቢተኛና ጭራሽ የማይታመኑ መሪ መሆናቸውን አምነው በመቀበል፣ አንድ መንግሥት ሊያደርግ የሚገባውን የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅን ጥቂቷን ኃላፊነት እንኳን ለማስከበር አልቻሉም። በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄድ ያለው የዘር ፍጅትና የዘር ማጽዳት ወንጀሎችና ሀብት ንብረት ዘረፋውና ውድመቱ ሁሉ “መንግሥት መር” መሆናቸው በሚገባ በመታወቁና በተለይ ደግሞ በወለጋና መተከል ተባብሶ የቀጠለው አስከፊ ጭፍጨፋ ሙሉ በሙሉ እየተመራ ያለው በቀጥታ በጠ/ሚሩ መሆኑ ገሃድ ወጥቷል። እንዲሁም ከውጭም በሱዳን በኩል የተፈጸመብን አሳፉሪ ወረራ ሴራን የኢትዮጵያን ሕዝብ በአስቸኳይ አስተባብሮ ለመመከትና ሉዐላዊነታችንን መልሰን ለማስከበር ያልቻልነዉ በጠ/ሚዉ የብቃት ችግር ነው። ስለሆነም ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ በራሳቸው ፈቃድ ሲያምናቸው የከደቱን የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርታ ጠይቀው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ራሳቸውን ከኃላፊነት በሰላም እንዲያነሱ እንጠይቃለን፣
 
2. እውነተኛ የሆኑ የፓለቲካ ድርጅቶች፣ የተለያዩ ስብስቦችና ማኅበራት አገራችን ኢትዮጵያ የገባችበትን እጅግ በጣም አደገኛ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የውስጥ መሳሳቦችን ትተውና በጋራ አገራዊ አቋም ዙሪያ አብሮ በመቆም ከላይ በተራ ቁጥር አንድ ላይ የተነሱትን ቁልፍ ጭብጦች ግምት ውስጥ በማገባት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ኃላፊነታቸውን በሰላም እንዲያስረክቡ የያራሳቸው ያልተቆጠበ ሚና እንዲጫወቱ፣
 
3. ከላይ በቁጥር አንድ የተጠቀሱትን አሳማኝ ምክንያቶች ባለመቀበል ጠ/ሚሩ ለሕዝብ ጥሪ ጀሮ ዳባ ልበስ ብለው አሁንም በዚያው በሥልጣን ኮረቻው ላይ ለመቀጠል ከወሰኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱን በሚመቸው አደረጃጀት እያደራጀ የተናበበ ሕዝባዊ ትግል ማድረግና ራሱን ከመንግሥት መርና የተለያዩ ጥቃቶች የመከላከል እርምጃ መውሰድና በየአካባቢው የራሱን መሪዎች እየመረጠ ትግሉን ማፋፋም፣
 
4. በውጭው ዓለም ያለንና ስለ ኢትዮጵያና ሕዝቧ የምንጨነቅ አገር ወዳድ ተቋማት፣ ማኅበራት፣ ስብስቦችና ታዋዊ ግለሰቦች በአጠቃላይ የትግሉ የጀርባ አጥንት የሆነው ሕብረተሰብ የተናጠል ጥረታችንን ወደ የጋራ የትግል ማዕከል በማምጣት የአገራችንና የሕዝባችንን መጻኢዊ ዕድል ፈንታ በጋር ሁነን መወሰን እንድንችል የጋራ የመታገያ መድረክ መፍጠር፣
 
5. ጠ/ሚ አብይ አህመድ የሚመሩት ጦር የአገር መከላከያ ሠራዊት መሆኑ ቀርቶ የኦሮሙማ ጉዳይ አስፈፃሚ ሆኖ ቀርቧል። ይህም በመሆኑ ያለቦታው የተኮፈሱ ተሿሚዎቻቸው ከወታደራዊ ሥነምግባር ውጭ በጣም እርቀው በመሄድ ከወታደራዊ አዛዥነት ወደ ተራ የአብይ ካድሬነት የወረዱ ምልምሎች መሆናቸውን ተመዝግቧል። ስለሆነም በመከላከያ ውስጥ ያላችሁ እውነትኛ የኢትዮጵያ ልጆች በዚች ታሪካዊ ወቅት ሕዝብ ኃላፊነት ጥሎባችኋልና በያላችሁበት ያላሰለስ ትግል ልታደርጉ ይገባል፣
 
6. እስክንድር ነጋ እና አጠቃላይ የባልደራስ አመራር እና አባላት የሕሊና እስረኛ ተደርገው በእስር ቤት የሚማቅቁት ለህዝባቸዉ ድምጽ በመሆናቸው ለህዝባቸው ዲሞክራሲያዊ እና ሰበአዊ መብት በመታገላቸው መሆኑ ታውቆ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም የአዲስ አበባ ሕዝብ እነዚህን ጀግኖች ሆ ብሎ ወጥቶ እንዲያስፈታ የትግል ጥሪ ቀርቦለታል፣
 
7. የብልፅግና መንግስት የኢትዮጵያን ሕዝብ በሚያወናብድበት ሂደት ሁሉ የመንግስት ጥገኛ እና ተለጣፊ ሆነው የተሰለፉት እንደ ኢዜማ ዓይነት አስመሳይ ተቃዋሚዎች ሕዝባችንን ከማጭበርበር እና ከማወናበድ እንቅስቃሴአቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን። ይሄም ማለት ወይ እውነተኛ ተቃዋሚ ሆነው እንዲቆሙ እና ለእውነተኛ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ እና ሰላም እንዲታገሉ አለዚያም ሙሉ ለሙሉ የብልፅግና መንግስት አካል መሆናቸውን ለሕዝብ ይፋ አድርገው በተቃዋሚነት ስም ሕዝብን ከማወናበድ እንዲቆጠቡ እናሳስባለን፣
 
8. ጠ/ሚ አቢይ አጠቃላይ ሀገራዊ ለዉጡን የማደናቀፍ እንጂ የማስቀጠል ፍላጎት ስለሌለዉ ከጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ ስልጣኑን የሚረከበዉ የብልጽግና አካል እንዲሁም ከልዩ ልዩ ሀይሎች የሚዉጣጣዉ አካል አጠቃላይ ሁል አቀፍ ህዝባዊ የሽግግር መንግስት እንዲያቋቁም ብሎም የህዝብ እንደራሴዎች: ተቃዋሚ ፓርቲዎች:የሲቪል ማህበራት:ከተባበሩት መንግስታት እና የኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያገባቸዉ ሀይሎች ሁሉ በሂደቱ ላይ በግልጽ እና በገሃድ ተሳትፈዉ በሁሉም አካላት ቅቡል የሆነ ህገመንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ከጸደቀ ብኋላ ወደ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ሀገሪቱ እንድትሸጋገር የሚያስችል ሁኔታ እንዲፈጠር የሚመለከተዉ ሁሉ በጋራ መስራት ይኖርበታል ፣
 
9. በመጨረሻም ኢትዮጵያን የመረከብ እና የአገር ባለቤት የመሆን ኃላፊነት በዚህ ትውልድ ጫንቃ ላይ እንደወደቀ በመረዳት የኢትዮጵያ ሕዝብ በአጠቃልይ የአገሪቱን ኅልዉና ለማስከበር እና የአገር ባለቤት ለመሆን ለቆራጥ ትግል በጽናት ቆርጦ እንዲነሳ ጥሪ እናቀርባለን!!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ!!
 
ይህ መግለጫ ከዚህ በታች ሥማቸው የተዘረዘሩ ድርጅቶች፣ ማኅበራትና ስብስቦች ተወያይተው እና ተስማምተው ለኢዮጵያ ሕዝብና ጉዳዮ ለመመለከታቸው ሁሉ የብዙሃ መገናኛዎች እንዲደርስ የተዘረጋ የአቋም መግለጫ ሲሆን ውሳኔውን ያሳለፉት አካላት ዝርዝርም፦
 
1. ሀገራዊ የምክክር አደባባይ–(ሰሜን አሜሪካ)፣
2. ሀገር አድን–(ሰሜን አሜሪካ)፣
3. የኢትዮጵያ ኅልዉና አድን ኅብረት–(ሰሜን አሜሪካ)፣
4. የዓለም አቀፍ የአማራ ኅብረት–(ሰሜን አሜሪካ)፣
5. ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት–(ሰሜን አሜሪካ)፣
6. ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት-(ሰሜን አሜሪካ)፣
7. የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ የድጋፍ ማህበር በሰ/ሜን አሜሪካ–(ሰሜን አሜሪካ)፣
8. የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ የድጋፍ ማህበር በሰ/ሜን አሜሪካ–(ሰሜን አሜሪካ)፣
9. የአማራ ማህበር በአሜሪካ (AAA)፣
10. የታኅሳስ ሶስት መታሰብያ ለአንድነትና ዴሞክራሲ፣
11. የምኒልክ ማህበር (ሰሜን አሜሪካ)፣
12. ኢትዮጵያዊነት–(ሰሜን አሜሪካ)፣
13. አጋር – የዐማራ ማኅበራት ኅበረት በአውስትራሊያ!
የአማራ ሚድያ ማዕከል – አሚማ

1 Comment

  1. በእሳት እያነደዱ ዘረፋ ሀገሪቷን ወደ የማትወጣው ኪሳራ በከተተበት በአሁኑ ዘመን ሴቶችን በመረጃ ምርመራ እና የደህንንነት ሥራዎች ላይ በብዛት ማሳተፍ ያስፈልጋል።

Comments are closed.