መረጃ! ቀዳማዊ እመቤት ያስገነቡትን ት/ቤቶች ለማስመረቅ እና ለገዳ ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ለማስቀመጥ ደቡብ ኦሮሚያ

መረጃ
“ቀዳማዊ እመቤት” “ያስገነቡትን” ት/ቤቶች ለማስመረቅ እና ለገዳ ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ለማስቀመጥ ደቡብ ኦሮሚያ (ቦረና እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች) አንገታቸው ላይ የኦነግ ባንዲራ እና የኦሮሞ የነፃነት ትግል ተምሣሌት ቀለማት (አረንጏዴና ቀይ) ያሉትንጨሌ በአንገታቸው አጥልቀው በቦረና ሴቶች አለባበስ ወግ መምጣቸው ባያስመሰግናቸውም ጥሩና ይበል የሚያሰኝ ነው:: ልማትንና ባህልን እብድ ካልሆነ የሚጠላ የለምና::
ሆኖም “የቀዳማዊቷ እመቤትን” ፕሮጄክቶች በሚመለከት ግልፅኝነትና ተጠያቂነት (transparency & accountability) የሚባሉ ቃላት ሲታዩ ቀላል ነገር ግን እጅግ ከባድ መርሆዎችን (principles) ተከትሎ መሥራት ወደፊት ለሚደርስ ተጠያቂነት ያድናል::
እነዚህን “የቀዳማዊት እመቤት” ፕሮጄክቶች በሚመለከት ግልፅ መሆን ያለባቸውን አካሄዶችና አሰራሮች በሚገባ መጠየቅና ምላሽ ማግኘት የግድ ይላል:: አጥጋቢ ምላሽ ከሌለ ኇላ ላይ ተጠያቂነት አይቀሬ ነው:: ከብዙ በጥቂቱ መጠየቅ ያለብን 10 ዋና ዋና ጉዳዮችን እስቲ አንድ በአንድ እንመልከት:-
 
1. የገንዘቡ ምንጭና የተገኘበት ሂደት ግልፅ መሆን አለበት:: ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ይዞ መገኘት በሕግ እንደሚያስጠይቅ በአዋጅ ቁጥር 657/2002 (Proclamation No. 657/2009
Prevention and Suppression of Money Laundering and the Financing of Terrorism Proclamation) ተደንግጏል::
 
2. የገንዘቡ ምንጭ ቢታወቅ እንኳን ገንዘቡ የተገኘበት ሂደት ከጥቅም ግጭት ነፃ (free from conflict of interest) መሄኑን ማረጋገጥ ግድ ይላል:: ገንዘቡ የተገኘው አምጪዎቹ ባላቸው የመንግሥት ሥልጣን ምክንያትና ተሰሚነት ከሆነ ገንዘቡ በቀጥታ ወደ መንግሥት ካዝና ገብቶ ባለው መንግሥታዊ አሰራር ሥራ ላይ መዋል አለበት::
 
3. “የቀዳማዊ እመቤቷ” ፕሮጄቶች የሚተገበሩት ራሱን በቻለ ድርጅት ከሆነ ይህ አስፈፃሚ ድርጅት አስፈላገውን ህጋዊ ሂደቶችን አሟልቶ ለምሳሌ እንደ አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት (መ.ያ.ድ) ተመዝግቦ ህግና ሥርዓትን ተከትሎ የፕሮጀክቶቹን ፕሮፖዛል ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የክልል ቢሮዎች አቅርቦ ከፀደቀ በኇላ እንደ ማንኛውም መ.ያ.ድ ፕሮጄክቶቹን በሚደረሰው የሥምምነት ውል (project implementation agreement) መሰረት ማከናወን ይኖርበታል:: ለምሣሌ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ Clinton Foundation, Carter Center; Melinda & Gates Foundation and thousands of Civil Societies and Charities (including NGOs) በዚህ መልኩ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ::
 
4. “በቀዳማዊት እመቤት” የተገኘው ገንዘብ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በምን ዓይነት መመዘኛዎች ወይም ቀመር (criteria) ተከፋፈለ? የሚለው ጥያቄም ተገቢ ምላሽ ያስፈልገዋል:: ለምሣሌ የፌዴራል መንግሥቱ ለክልሎች “ድጎማ” (መደጎም ያለበት ፌዴራል መንግሥቱ ቢሆንም because in principle to be a State in Federal Arrangement each State should be financially independent ማለትም እያንዳንዱ ክልል: ክልል ለመሆን የግድ በበጀት ራሱን መቻል አለበት በመርህ ደረጃ) ሲያከፋፍል የህዝብ ብዛት (population size about 60%), የሚያስገባው ገቢ (revenue generation capacity, about 25%) እና የእድገት (የኇላቀርነት) ደረጃው (level development/underdevelopment level, about 25%) የመሳሰሉትን ታሳቢ ያደርጋል:: በዚህ መሰረት ኦሮሚያ: አማራ: ሶማሌ: ትግራይ: የደ/ብ/ብ/ሕ: ሲዳማ: አፋር: ቤኒ-ሻንጉል ጉሙዝ: ጋምቤላና ሐረሪ ክልሎችና አዲስ አበባ እና የድሬ ዳዋ (የድሬዳዋ ጉዳይ ምንም እንኳን ኢ-መንግሥታዊ ቢሆንም) ከተማ አስተዳደሮች በየቅደም ተከተላቸው ግልፅ በሆነ መንገድ ከፕሮጄክቶቹ የሚያገኙት ድርሻ መታወቅ አለበት::
 
5. እስካሁን በሚስተዋሉት የፕሮጄህቶቹ አሰራር መሰረት የፕሮጄቶቹ የግንባታ ሥራዎች የሚከናወኑት በግለሰብ ወይም ሃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ድርጅቶች የግንባታ ተቋራጮች ነው:: እነዚህ ተቋራጭ ድርጅቶች በምን ሂደት ውስጥ አልፈው ተመረጡ? ለምሣሌ ግልፅና ከአድልዖ ነፃ የሆነ ትክክለኛ የጨረታ አሰራር መኖሩን የሚያመለክት ማስረጃ አለ? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል::
 
6. እስካሁን እንደሚታየው “በቀዳማዊት እመቤቷ” በብዛት የሚተገበሩት የት/ቤቶች ግንባታ ፕሮጄክቶች ናቸው:: እስካሁን ባልሳሳት ከአስር ያላነሱ ት/ቤቶች ተገንብተው “በቀዳማዊ እመቤቷ” ተመርቀዋል:: በፕሮጄክት ዝግጅት (project preparation including problem and need assessments, feasibility study, etc) ወቅት መታየት ያለባቸው አስፈላጊ ጥናቶች/ዳሰሳዎች (studies/assessments) ምን ያህል በጥልቀት ታይተዋል? ይህ ተደርጎ ከሆነስ እንዴት አብዛኛዎቹ ፕሮጄክቶች የት/ቤቶች ግንባታ ሊሆኑ ቻሉ? በተለይ ብዙዎቹ በቆላማው አካባቢዎች (ለምሣሌ ሶማሌ: አፋር: በደ/ብ/ብ/ሕ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እና ደቡብና ደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ የሚገኙ አርብቶ አደሮች ዛሬም ትልቁ ችግራችን ብለው የሚያነሱት በአንደኛ ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃ የሚጠይቁት የሰውና የእንሰሳት መጠጥ ውሃን ነው:: ይባስ ብለው ሰሞኑን “ቀዳማዊቷ እመቤት” በውሃና የግጦሽ ችግር ለሚሰቃየው የቦረና ዞን ሕዝብ “ለእናንተ የሚያስፈልገው ውሃ ሳይሆን የገዳ ማዕከል ነው” በማለት ለማዕከሉ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አኑረዋል:: Is it really the pressing and priority need of drought affected Borana people?
 
7. ፕሮጄቶቹ እውን በገለልተኛ ባለሙያዎች እና ኦዲተሮች (external evaluators and auditors) እየተገመገሙ ነው? ብሎ መጠየም ግድ ይላል:: ይህ ዓይነቱ አካሄድ በማንኛውን የፕሮጄክት አሰራር የተለመደና ግዴታም ነው:: ምንም እንኳን ውሥጣዊ ግምገማ: ክትትል እና ውሥጣዊ ኦዲት (internal monitoring & evaluation as well as internal audit) ቢኖሩም በገለልተኛ አካል ግምገማና ኦዲት ማድረግ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆኑ ግዴታም ናቸው::
 
8. በፕሮጄክቶቹ ግምገማ ወቅት አንዱ መታየትና መጠየቅ ያለበት “የቀዳማዊቷ እመቤት” የፕሮጄት አሰራር ምን ያህል አሳታፊ (participatory approach in project cycle management) ነው የሚሉ ቁልፍ ጥያቄዎችም መነሳታቸው የግድ ነው:: የፕሮጄክቶቹ ባለድርሻ አካላት አሳታፊነት (participation of project stakeholders) ከፕሮጄክቶቹ ቀረፃ (project preparation) ጀምሮ በፕሮጄክት ትግበራ (project implementation): ክትትል (project monitoring) እና ግምገማ (project evaluation) ጊዜ መኖሩንበትክክል ማረጋገጥ ያስፈልጋል:: በተለይ ተጠቃሚው ህብረተሰብ ለፕሮጄክቱ ምን አስተዋፅኦ (ሃሳብ በመስጠት ወይም በዓይነት ወይም በገንዘብ ድጋፍ) አደረገ? በተለይ የእኔነት ስሜት እንዲሰማው (feeling of sense of ownership)?
 
9. በገለልተኛ ግምገማ ወቅት ሌላው በሚገባ መታየት ያለበት የፕሮጄክቶቹ ግንባታና ሥራ ካለቀ በኇላ ቀጣይ የዘላቂነት (sustainability)ጉዳይ ነው:: ምክንያቱም ግንባታው በጥሩ ሁኔታ ቢጠናቀቅ እንኳን ተጠቃሚው ሕብረተብ በቀጣይነት ካልተጠቀመ የሃብት ብክነትን መፍጠሩ አይቀሬ ነው:: “ቀዳማዊ እመቤቷ” ፕሮጄክቶቹን ተረክቦ ከሚያስተዳድረው አካል/አካላት ጋር ምን አይነት ውል አደረጉ (handing over agreement) በተለይ ቀጣይነትን/ዘላቂነትን ለማረጋገጥ (to ensure sustainability of the project impact/s)?
 
10. “የቀዳማዊቷ ፕሮጄቶች” አዋጪነት (cost effectiveness) ከኦዲት ባለፈ በገለልተኛ አካል በሚገባ መገምገም አለበት:: ለፕሮጄክቶቹ የፈሰሰው ሃብት (ገንዘብ: የሰው ሃይል: ማቴሪያልና ጊዜ) ፕሮጄቶቹ የሚሰጡት ጥቅምና ፋይዳ በትክክል መነፃፀርና መታየት አለባቸው:: ጥቅሙና ፍይዳው ለፕሮጄክቱ ከፈሰሰው ሃብት ካነሰ ተጠያቂነትን ይዞ መምጣቱ የግድ ነው::
ከላይ ከተገለፁት 10 ዋና ዋና ነጥቦች በተጨማሪ ብዙ ጉዳዮችን ማንሳት ቢቻልም ለጊዜው ለነዚህ 10 ጉዳዮች/ጥያቄዎች ብቻ እንኳን በቂ ምላሽ ካገኘን ለተቀሩት ይቅርታ ልናድርግላቸው እንችን ይሆናል:: ይዋል ይደር እንጂ በውዴታም ሆነ በግዴታ “ቀዳማዊ እመቤቷ” እና ባላቸው (ጠቅላይ ሚኒስቴሩ) በነዚህ ጉዳዮች ላይ ለምርመራ (investigation) እንደሚቀርቡ አውቀው ከአሁኑ እንዲዘጋጁ እመክራለሁ::
 
By Haqabaas Jaalata
January 26, 2021
Finfinnee