መላው የቅማንት ብሄር ተዎላጆችና ደጋፊዎች መወያያ መድረክ

መላው የቅማንት ብሄር ተዎላጆችና ደጋፊዎች መወያያ መድረክ

ይድረስ ለመላው ኢትዮጲያውያውያን ፦

(መልእክት ከቅማንት ህዝብ)

“ለካስ ሞትም ይዘረፋል ፥ ይቀማል” (ሰቆቃ ወ ቅማንት)
ይድረስ ለመላው ኢትዮጲያውያውያን ፥ እኛ ቅማንት በዚህ ሶስት አመት ምድር ላይ ያሉ ጭቃኔዎችንና ዘግናኝ ጭፍጨፋዎች ሁሉ አስተናግደናል ። ከነዚህም በጥቂተ በመተማ ዮኋንስ ከተገደሉት 147 ንፁሃን ቅማንቶች ውስጥ ከነቤታቸው የተቃጠሉ 58 ንፁሃን ሬሳቸውን መለየት ስላልተቻለ 58ቱን በአንድ ላይ በጅምላ መከላከያ በዶዘር ቆፍሮ ከ4 ቀን በኋላ የዛሬ አመት ተቀብረዋል። ከዛም ከመተማ እስከ ጎንደር ከተማ ድረስ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በአማራ ክልል መንግስ ቀስቃሽና አስተባባሪነት ሀብት ንብረታችን ተቃጥሎና ተዘርፎ ከ482 በላይ ወገኖቻችን ተገለዋል።

92,583 ቅማንቶች ከመተማ ቋራ ምዕራብ አርማጭሆ ፥ ፀገዴ ፥ ደንቢያ ፥ ታች አርማጭሆና እንዲሁም ጭልጋ ወረዳዎች በግፍ ተፈናቅለዋል ፥ ልክ የዛሬ አመት የመንግስት ሠራተኞች ቅማንት በመሆናቸው ብቻ ከሚሠሩበት ወረዳና መስሪያ ቤት 3,275 በግፍ ተፈናቅለዋል። በየቦታው ብቻቸውን እና በተናጠል የሚገኙ ቅማንቶች በመንጋ ፍርድ የድንጋይ ተቀጥቅጠውና በጩቤና በገጀራ ታርደዋል። በሽንፋ ከተማና ዙሪያዋ በ67 ተሽከርካሪዎች የታጠቁ የሸፍታና ዘራፊ ቡድን (ፋኖዎች) ከተማ ተወራ ከተማውም ሙሉ በሙሉ እንድትቃጠል ሆናለች። በዚህ 121 ቅማንቶች በግፍ ተጨፍጭፈዋል።

ከጎንደር ከተማ 15ኪሜ ወጣ ብሎ በሚገኘው ማውራ ቀበሌ ዘመቻ ተደርጎ ብዙ ቤትና ንብረት ተቃጥሎ 76 ንፁሃን ቅማንቶች ተገለዋል። በዚህ አመት ደግሞ ከጳጉሜ ጀምሮ እስከዚህ ሰዓት ደረስ በክልል የፀጥታ ኃላፊ ባደረገው የዘር ማጥፋት ቅስቀሳና የዘር ማጥፋት ጥሪ መሰረት በጎንደር ከተማ በአዘዞ ፥ በፀዳ (ጠዳ) ፥ በማራኪ ፥ በሆስፒታል ሠፈር ፥ በኮሌጅ ማዞሪያ ፥ በመስጊድ ፥ በገንፎ ቁጭ ፥ በሸዋ ዳቦ ሠፈርና በዙሪያው ባሉ ቀበሌዎች በተለይ በፈንጠር ፥ በደፈጫ ፥ በአንቦ በር ፥ በዳዋ ዳሞት እና በአንገረብ አካባቢ የሚገኙ ቤቶ የቅማንቶች እየተለዩ ተቃጥለዋል ፥ ተዘርፈዋል። ታጭዶ የተከመረ ሠብልም ተቃጥሏል ፥ ተዘርፏል ፥ ሰዎችና እንሣትም ጭምር ከነቤታቸው በእሳት ነደዋል።

በዚህም ከ127 ንፁሃን ተገለዋል በተለይም አዘዞ በቀን በአደባባ የ44ታቦት ባለቤት በሆነችው ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ የአንድ ቤተሠብ አባላት የሆኑ አምስት ንፁሃን ቅማንቶች ከነቤታቸው እንዲቃጠሉና እሬሳቸው በአስፓልት ላይ እንዲጎተት ተደርጓል። የአካባቢው ማህበረሰብ ለመንጋ ግድያውና ቃጠሎው ተሳታፊ ነበር። ከዚያም በመቀጠል ከገጠር መጥተው ተከራይተው የሚማሩ ልጆ በየዶርሙና ከትምህርት በሚመለሱበት ሰዓት እየታፈኑ በየቀኑ ታርደው ተጥለው ይገኙ ነበር። ጎንደር ከተማ ውስጥ በተለይ አራዳ ቅዳሜ ገቢያ ፥ ገንፎ ቁጭ ኮሌጅ እና ጋዜቦ ሠፈር ዋና ዋናዎቹ ነበር ቅማንቶች እየታፈኑ የሚታረዱበት ቦታ። በዚህም የእፈና እና የእርድ ግፎች ከ29 በላይ ቅማንቶች በግፍና ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ተጨፍጭፈዋል ፥ ህይወታቸውን እንዲያጡ ተደርገዋል።

ይህን አጠናክሮ በመቀጠል ትናንት ታህሳስ 21/04/2012 ዓ/ም ጎንደር ከተማና ዙሪያው በተኩስ እየታመሠ ሲሆን በከተማው ዙሪያ የሚገኙት ፈንጠርና ደፈጫ ቀበሌዎች ላይ ሌላ ዙር የጥቃት ዘመቻ ከፍተው ከባለፈው የተረፉ የቅማንትን ቤትና ንብረት እያቃጠሉና እየዘረፉ ይገኛሉ ። በትናንቱ ቀን ጎንደር ከተማ ውስጥ በየቦታ የተከስና የጥይት ድምፅ ደምቆ ይሠማል።

የሚገርመው ይህ ሁሉ ግፍና ጭቃኔ ይመራኛል ባለው በራሱ ክልል መንግስ ድጋፍና አይዞባይነት በንፁሃን ቅማንቶች ሲፈፀም ኣስፀያፊ ግፍ ነው ብሎ ያወገዘ አካል አለመኖሩ ልብ ሠባሪ ነው ። አልሸባብና ISIS ቦንብ አፈንድቶ አምስት ሰዎች ተገደሉ እና ሜሲና ሮናልዶ ቁርስና ምሳ ይህን በሉ ተናገሩ ተብሎ በየሚዲያው በሚዘገብበት አገር የንፁሃን ቅማንቶች ጭፍጨፋ የማይዘገብበትና የሚደበቅበት ድምፃችን ታፍኖ የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈፀብን አገር መሆኑ ነው።

ይህን ጭፍጨፋ የአስተባበሩና የመሩት አረመኔ ጨካኝ ሰዎች ሹመትና እድገት የሚያገኙበትና የሚወደሱበትና እንደጀግና የሚዘመሩበት ክልል መሆኑ ጭካኔውን ያበዛዋል።
በአንፃሩ ግን ለምን ከቤትህ መጥቸ ስገድልህ አልሞትክም ፥ ከቀበሌህ ልዘርፍና ላቃጥልህ ስመጣ ለምን እራስክን ተከላከልክ በማለት እስካሁን ከ1,638 በላይ ንፁሃን የቅማንት ልጆች በእየስርቤቱ ታጉረው ያለምንም ክስና ፍርድ ይሰቃያሉ። የሚጮህላቸው መንግስትና ሚዲያ የሌላቸው ድምፅ አልባዎች ናቸውና ።

ስለሆነም የፌደራሉ መንግስት የቅማንት ሞት ና ጭፍጨፋ የማያስጨንቀውና ግድ የማይሠጠው የፓለቲካ ትርፍ ስለሌለው ነው። የአማራ ክልል መሪዎችን ድጋፍ ለማግኘት ሲል ብቻ በድሃ እናቶች የቅማንት እንባና ደም ቁማር አስይዞብናል ። በዚህ ክፍለ ዘመን የቅማንቶች ሰቆቃና ጭፍጭፋ አይሁዳውያን በናዚ ጀርመን ፥ የሩዋንዳ ቱትሲዎች በሁቱዎች ከተጨፈጨፉት ቀጥሎ ዘግናኝና አረመኒያዊ ጭካኔዎችና በምድራችን ሁሉ ያሉ ኢሠብአዊ ድርጊቶች የተፈፀሙብን የአገሪቱ አምስተኛ ደረጃ ዜጋዎች ነን። ዶከተር አብይ ከልጆችህ አግኘው ሌላ ምን እንላለን። ይህን አረሜናያዊ የዘር ጭፍጨፋ ለማውገዝ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው።

ጎንደር በቅማንቶች ደም እየታጠበች ነው። አኬልዳማ ምድር የጭካኔዎች ሁሉ ማሳያ ተምሳሌት ለድምፅ አልባው ህዝባችን ስቃይ ድምፅ ለሆናችሁን ሁሉ ፈጣሪ ድምፃቹህን ይስማ ።

አሁን የንፁሃን ቅማንቶች የደም እንባ ይጮሃል። እነሱ ገለውን ዘርፈውን አቃጥለውን ጨፍጭፈውንም በየሚዲያቸው ሞታችንን ቀምተው ገልብጠው ይጮሃሉ። ለካስ ሞትም ይዘረፋል ይቀማል። የጉድ አገር !

ፈጣሪ ሆይ ምነው መምጫህ እረዘመ እባክህ ተሎ ናልን ፥ እውነተኛውን ብይን ስጠን ከአንተ ውጭ ተስፋ የለንምና !

(የቅማንቶች ሰቆቃ)