ሕገ-መንግስትንና ህብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓትን ማዳን በሚል መሪ ቃል በመቐለ የተካሄደው ጉባኤ ላይ ፕ/ር ሕዝቅኤል ገቢሳ ተሳተፈ በሚል ርዕስ የfb ክስተት ሆኗል።

ሕገ-መንግስትንና ህብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓትን ማዳን በሚል መሪ ቃል በመቐለ የተካሄደው ጉባኤ ላይ ፕ/ር ሕዝቅኤል ገቢሳ ተሳተፈ በሚል ርዕስ የfb ክስተት ሆኗል።

Kush Media Network (KMN:- DEC. 06/2019)

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያያታቸዉን እንዲሰጡኝ እንደ ወትሮዉ ሁሉ ፕ/ር እዝቅኤል ገባሳ ጋር ደዉዬ ነበረ። “በጉዳዩ የድሮ ስረዓት ናፋቂዎች በቡድን ተደራጅተዉ ተቃዋሚ የሚሉት ሁሉ ለማጥላላት እና ህዝብ ዘንድ ለማስጠላት የሚጠቀሙበት የፖሎቲካ ታክቲክ እንጂ ብሔራዊ ዲያሎግ ለማድረግ የሚጠቅም ትችት አይደለም። መልዕክቱን ሳይሆን መልዕክተኛዉን አጥቃ የሚል ያረጀ እና ያፈጀ የፖሎቲካ ታክቲክ ስለሆነ በመሰሪ ሀሳባቸዉ ሀሳብ አልሳተፍም” ። ብለዉኛል።

ይህን ዘመን ከሳሾቻቸዉ በዋናነት “የቀድሞ ስርዓት ናፋቂዎች” እና የኦዴፓ (አሁንም ሕግ የሚያውቀውድርጅት) ተቀጣሪ ተላላኪዎች ናቸው።ለነዚህ መልስ መስጠት ከነርሱ ጋር መጨቅየት ነው ። አጭሩ መልስ አያገባችሁም ነዉ። በጨለማ እንጂ በብርሃን ወጥተው ሀሳባቸዉን የማይሰጡ ተላላኪዎችን ጥርቅም አድርጎ መዝጋት ነው ተገቢው መልስ። እናንተ በጮሃችሁ ቁጥር ቁርጠኝነታችን ይጠነክራል”ብለዋል። በንግግራችን መሃል በ eskype መልዕክት ያስተላለፉትን ዋና ዋና ነጥቦች እንደሚከተለዉ አዉግተኛል።

ሃሳቦቻቸውን ትዝ እንደሚለኝ አስቅምጨዋለሁ

“እኔ አንድ ሰው ነኝ። እንደ አንድ ሰው ነው ዉሳኔ የማደርገው። ማንም ሰው አላማክርም። የሚጠይቀኝ የለም። ኦነግ ኦፌኮና ኦብነግ የፖለቲካ ድርጅቶች ናቸዉ። የፖለቲካ ነፋስ ወዴት ነው የሚነፍሰው ብለው ነው የሚወስኑት። ልክ እንደነሱ ለምን አልሆንክም ለሚባለው ክስ እኔ ነፃ ሰው ነኝ። ግለሰብ ነኝ። ያላመንኩበትን አላደርግም። ያመንኩበትን አልተዉም። ካልተመቻችሁ የራሳችሁ ጉዳይ።”

“በዚያ መድረክ የተናገርከው የኦሮሞን ህዝብ ትግል ይጎዳል ወይም እውነት አይደለም አላለኝም። የተነገረበት መድረክ ነው ችግሩ። እውነት በመልክአ ምድር አይወሰንም። እኔ የማውቀዉን እውነት ቦታና ሁኔታ አይቼ ሳይሆን የምናገረው እውነት ስለሆነ ነው።የተመቻቸ ቦታና ጊዜ መፈለግ አድርባይነት ነው። የኦሮሞን ህዝብ ሀቅ በየትም ቦታ በማንም ፊት በየትኛውም ሰዓት እናገራለሁ።የኦሮሞን ህዝብ እውነት ለኔ በገባኝ መጠን ከመናገር አልቦዝንም፣ በመቐለ ይሁን በሞያሌ። ወደፊትም ትንፋሽ እስካለኝ ድረስ እቀጥላለሁ።”

“ህወሓት ባዘጋጀው መድረክ መካፈል ህወሓትን መደገፍ ይሆናል የሚሉ ይሉኝታቢስ ተመፃዳቂዎች አሉ። ባብዛኛው የኦሮሞ አክትቪስት ነን ባዮች ናቸው። መቐለ ከሆነ ችግሩ እናንተ ፍንፍኔ ላይ አዘጋጁና ጥሩኝ። ህውሃት ከሆነ ችግሩ ብልጽግናዎች ሲያዘጋጁ እንዲጠሩኝ ንገሯቸው። እንጂ የኔን ያሳበን የመግለፅ መብት ለመግፈፍ አትራኮቱ።”

“ስብሰባው ህገ መንግስትና ሀብረብሔራዊ የፌደራል ስርአት ማዳንየሚል ርዕስ ነበረው ። አሁን በሥራ ያለው ሕገ መንግስትና (አንቀፅ 8 (1፣2፣3 እንዲሁም አንቀፅ 39ንያጠቃለለው) እና ሀብረብሔራዊ የፌደራል ስርአት የተቅናጀ ጥቃት እየተካደበት እንደሆነ አምናለሁ። ህገ መንግስቱም የፌደራል ስርዓቱም የኦሮሞ ህዝብ በትግሉ ያገኘው ድል ነው። የህወሓት ስጦታ አይደለም። ነፍጠኞች አሁን በሥራ ላይ ያለው ሕገ መንግስት እና ህብረብሔራዊ የፌደራል ስርአትን ይቅርና ብሄሮችንና ብሔረተኝንትን የፈጠረው ህወሓት ነው ይሉናል። ተባባሪዎቻቸው ደግሞ የነፍጠኛ ስርአት አቀንቃኝ የሆነው በልፅግያለሁና ተዉኝ የሚለው ኦዴፓ ሆኛለሁ የሚለው የቀድሞ ኦህዴድ ተቀጣሪዎች ናቸው። ከሳሾቼ ሳታውቁ የነፍጠኞች ክስ እያራመዱ ነው። ሕገ መንግስቱ እና ህብረብሔራዊ የፌደራል ስርአት መጠበቅ አለበት” ብሎ ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች መናገር ህወሓትን መደገፍ ነው ብሎ ክስ ማቅረብ የደንቆሮ ክርክር መድገም ነው ።

ህወሓት ይጥራው እንጂ የስብሰባዉ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች ተወካዮች ናቸው። በትግራይ ስለተሰበስቡ ለነሱ መናገር ጥፋት ነው ማለት የአዕምሮ ድንኮች ሃሳብ ነው ። የራሳቸውን ህዝብ ወክለውበግልፅ ቋንቋና ወደር በሌለው ጀግንነት የህዝባቸውን እውነት የተናገሩ ታላላቆች ከዚያዉ ከመቐለ ስብሰባ መድረክ ነበር ።

ለወደፊቱም አንድ ነገር ግልፅ ይሁን። እኔ ባሁን ሰዓት ከህወሓት ጋር የተለየ ትግል የለኝም። ከህወሓት ጋር እጅግ መራር ትግል አድርገን ስድስት ሺህ ነፍስ ገብረን፣ ብዙዎች ተሰደው፣ መቶ ሺህዎች ታስረው ተሰቃይተው በድል አድራጊነት ወጥትናል። አልሰማችሁ እንደሆነ እንጂ ህወሓት ዘርግቶት የነበረው የአምባገነን ስርአት ተሸንፎአል። ያሸነፍነውን ትግል ደግመን አንገጥምም። ህወሓት ትናንት ሕገ መንግስቱና ህብረብሔራዊ የፌደራል ስርአቱን ተጠቅሞ ከፍተኛ በደል አድርሶአል። ለዚያም በደል ኢህአዴግ ይቅርታ ለምኖ ነው ያለንበት ለውጥ “ትልቅ ተሃድሶ” አድርገዋል ለተባሉ የኢህአዴግ አባላት አደራ የተሰጠው።

የነበረው አምባገነንነት ህወሓት መራሽ ነበር ቢባልም ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ነበር። አብረዉ ነው የበደሉት፣ አብረው ነው ጥፋታቸውን ያመኑት፣ አብረው ነው የኢትዮጵያንን ህዝብ ይቅርታ የለመኑት። የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ አድርጎ ከሆነ ይቅርታው ለኦዴፓ ለአዴፓ እና ለደህዴን ተስጥቶ ህወሓት ዘንድ ሲደርስ ይቆማል የሚል አስተሳሰብ ከኔ የሞራል መርህ ጋር አይጣጣምም። ከኦዴፓ እየተመፀወቱ የሚኖሩ ብልሹዎች እኔን ለመተቸት የሞራል ልዕልና የላቸዉም።

አስተሳሰቡ ሎጂክም የለዉም። በኦዴፓ መሪዎች ስሌት ለ27 ዓመት የህወሓት ተላላኪ የነበሩት እራሳቸው ነበሩ። በራሳቸው በኦዴፓ መሪዎች እሳቤ በኦሮሞ ህዝብ ላይ በተፈፀመው ወንጀል ህወሓት አዛዥ ነበር፣ ኦዴፓ የወንጀሉ ፈፃሚ ነበር። ሁለቱም እኩል ወንጀለኞች ናቸው። የተግባር ወንጀለኛ የነበረው ገዳይ አሳሪ አሳዳጅ አባራሪ የመሬት ቸብቻቢው ኦዴፓ ነበር። ኦዴፓ “የለውጥ መሪ” ህወሓት ግን ብቸኛ ተጠያቂ የምትለዋ ዘይቤ ቀሽም የሌባ ታክቲክ ነች። አሁን በመፈንቅለ መንግስትና ዘርን በማጥፋት ወንጀል ሊከሰስ ከሚችል አዴፓ ጋር እየሰሩ ትናንት በሰራው ወንጀል ተጠያቂ ነው ከሚባል ህወሓት ጋር ንክኪ ማድረግ ወንጀል ነው ማለት ችግር አለው ። ከዓብይ አህመድና ደመቀ መኮንን ጋር ሸራተን ሲሳሳሙ መዋል ፅድቅ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የተገኝበት ስብሰባ ግን ኃጢያት ነው የምትል አካሄድ አታዋጣም።

“ትናንት የኦሮሞን ህዝብ ሲጨፈጭፍ ከነበረዉ ህወሓት ጋር መታየት ትክክል አይደለም” የምትል መመፃደቂያም አትሰራም። ትናንትስ ትናንት ነው። ዛሬስ? በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ የኦሮሞ ተማሪዎችን እየገደለ የተረፉትን አስሮ እያሰቃየ ያለው ከአዴፓ ጋር የሚሰራውና ካልተርጋጋችሁ ዩኒቨርሲቲውን እዘጋለሁ እያለ በወጣቶች ስቃይ የሚያላግጠው አብይ አህመድስ? ከግድያ አደጋ ሸሽተው ፍንፍኔ ደርሰው አቤት ሲሉ “እኔን አይመለከተኝም” ብሎ የበተናቸው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መሪ ተብሎ ቢሮ የተሰጠው ግለሰብስ?። የወለጋንና የጉጂ የቦረናን ህዝብ ላንድ ዓመት ተኩል በኮማንድ ፖስት ጠፍሮ እያሰቃየ ያለው፣ በጊዳሚና በቤጊ አካባቢ በሄሊኮፕተር ጋንሺፕ የደበደበውአመራርስ ? መግቢያ መውጫ አሳጥቶ ወጣቶችን በጥይት ሲደፋ የሚውለውስ? በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኦሮሞዎችን እስር ቤቶች ስላልበቁት ቤተመንግስትና የቀበሌ ቤቶችን እንዲሁም የፖሊስ ማሰልጠኛ ካምፖችን የኦሮሞዎች ማጎሪያ ያደረገውስ ? የራሱን ወንጀልና አገር የማስተዳደር ድክመቱን ሁሉ በህወሓት ላይ እያላከከ በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚደረግ ታክቲክ እምብዛም እርባና የለውም።

ሌላዋ ድኩም ምክንያት ደግሞ “ኦዴፓ ኦሮሞ ነው። ባይሆን እቤታችን ውስጥ እንመካከር እንጂ ገመናችንን በአደባባይ አናውጣ ፣ እዚሁ በጓዳችን እናሾክሹክ” የሚሉ አሉ። ወዳጆቼ ናቸው። ሳያውቁ የብልፅግናና የኢዘማን አጀንዳ ነው። እንዲህ ያለ አባባል እየተካሄደ ያለዉን ወንጀል፣ የፖለቲካ አሻጥርና አገር የሚያጠፋ ወንጀል እንሸፋፍን ማለት ነው። አልስማማም። ወዳጅነቱ ይቅርብኝ እንጂ በዚህ ሻጥር ተባባሪ አይደለሁም። በትግራይ ክልል መገኘት ራሱ ከህወሓት ጋር ትብብር ነው የሚሉ ነሆላሎች ጊዜ ስላልፈቀደልኝ ነው እንጂ ገና ብዙ ለመጎብኘት የምፈልገው የትግራይ ክልል ከተሞች አሉ።

ማንም ሰው እስካሁን በዚያ መድረክ የተናገርከው የኦሮሞን ህዝብ ትግል ይጎዳል ወይም እውነት አይደለም ያለኝ የለም። ዋናው ክስ ህወሓት ላይ ቂም ይዘህ መቆየት አለብህ ነው። እሱ ፖለቲካ አይደለም። እኔ የኦሮሞን ህዝብ እውነት ለኔ በገባኝ መጠን ከመናገር አልቦዝንም፣ በመቐለ ይሁን በሶማሌ። ይህን በማድረጌ ህወሓት 2 ሚልዮን ብር የሚሰጠኝ ከሆነ ወሮታቸውን ከፍዬ አልጨርስም። ለማንኛዉም እስካሁንም ድረስ ተከፍሎኝ የሰራሁት ለቀጠረኝ ዩኒቨርሲቲ ብቻ ነው።ልሳኔን ለፖለቲካ አከራይቼ አላውቅም። የኦዴፓ የክፍያ መዝገብ ላይ ያሉ ምንደኛ ታጋዮችን እዚያው የነሱ መንደር ዉስጥ ፈልጉአቸው።

OMN: ምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ቆይታ ከህግ ባላሙያቹ አበዱልጀባር ሁሴንና ኢብሳ ገመዳ ጋር ዛሬ ጠብቁን