ሕወሓት በፍርሃት ያቋቋመው “የፌስ ቡክ ሰራዊት” ከቻይናው ” የ50ሳንቲም ሰራዊት”

ሕወሓት በፍርሃት ያቋቋመው “የፌስ ቡክ ሰራዊት” ከቻይናው ” የ50ሳንቲም ሰራዊት”

ሕወሓት በፍርሃት ያቋቋመው “የፌስ ቡክ ሰራዊት” ከቻይናው ” የ50ሳንቲም ሰራዊት” ጋር አንድና አንድ ነው. የቻይናው የ50ሳንቲም ሰራዊት ብዙ ሚሊዮን አባላት ያሉት የኮምኒስቶች ስብስብ ሲሆን አንድ ተቃዋሚን /አክቲቪስትን የሚያጥላላ ፖስት ለለጠፈ፣ኮሜንት የሰጠ የቻይና 50 ሳንቲም ማበረታቻ ይታሰብለታል. በዚህ አይነት በወር ጠቀም ያለ ጉርሻ በለጠፉት ፖስት መጠን ይገኛል.
በ200 የፌስ ቡክ መሪዎችና በ3000 ጀሌዎች በአቶ ሬድዋን ሁሴን የኮምዩኒኬሽን ሚኒስትርነት ዘመን ተመርቆ ስራ የጀመረው የሕወሓት የፌስ ቡክ ሰራዊት ዋና ዋና ሃላፊነቶች ተሰጥተውት በቻይና ሞዴል መስራት እየጀመረ ነው.የተቀበላቸውን የስራ ዝርዝሮች እንደሚከተለው እናቀርባለን

1. የሐሰት አካውንት መፍጠር – የፌስ ቡክ ሰራዊት ኮምፑዩተርና ኔትወርክ በየመስሪያ ቤቶች ቢሮዎች ተሰጥቷቸው በኦሮሞ፣በአማራ፣በትግራይ፣በሙስሊም፣በክርስቲያን ስም የሀሰት አካውንት በመፍጠር በየ ፔጁና በየ ተቃዋሚዎች ዌብ ሳይቶች እየገቡ ፖስት ይለጥፋሉ ኮሜንት ይጽፋሉ

2. የተሳሳተ መረጃ ማስተላለፍ -የፌስ ቡክ ሰራዊት የግንቦት ሰባት-የኦ.ፌ.ኮ ና የሌሎችም ፓርቲዎች አባል በመምሰል የተሳሳተ መረጃ ይሰጣሉ-ተቃራኒ ሃሳብ ያነሳሉ-ከፋፋይ ሃሳብ ያንሸራሽራሉ. አማራ በመምሰል ኦሮሞን ይሰድባሉ-ኦሮሞ በመምሰል አማራን ያዋርዳሉ -ሙስሊም በመምሰል ክርስቲያንን ክርስቲያን በመምሰል ሙስሊምን ያሰድባሉ.

3. የአክቲቪስቶች ስም ፌክ አካውንት መጠቀም – የታወቁ የፌስ ቡክ አክቲቪስቶችን ስምና ፕሮፋይል ፎቶ በመጠቀም ያደናግራሉ. በአክቲቪስቶች ስም ተቃራኒ ሃሳብ በመለጠፍ እምነት እንዲያጡ ያደርጋሉ.

4. የተቃዋሚ አመራሮችን ስም ያጠፋሉ -የተቃዋሚ አመራሮችን ስም እየጠቀሱ ሃሰተኛ ታሪክ እየፈጠሩና በፎቶ እያስደገፉ ተአማኒ እንዳይሆን ጥላሸት ይቀባሉ

5. ትግልን ማቃለል -የፌስ ቡክ ሰራዊት የህዝብን ትግል ያቃልላል. የጎንደር ገበሬን፣የግንቦት ሰባትን፣የኦሮሞ ህዝብን ትግል ያሳንሳል.የጥቂት ግለሰቦች የስልጣን ትግል እንደሆነ በማቃለል ይለጥፋል.የወጣቱ ጥያቄ የዲሞክራሲና የሃብት ፍትሃዊነት መሆኑን በማስተባበል የጥቂት ወጣቶች ስራ የማጣት እንደሆነ ያስተጋባሉ.

በህዝብ ትግል ላይ ወደሁዋላ የሚመልስ ሃሳብ ከተመለከታችሁ እሱ የህወሃት ቅጥረኛ የፌስ ቡክ ሰራዊት ነው. መከፋፈል፣ግጭት፣ልዩነት ለማንሳት የሚሞክር ሃሳብ ከፌስቡክ ሰራዊት ነው. ሁላችንም እነዚህን ከፋፋዮች አፍ ማዘጋት ይጠበቅብናል. ከፌስ ቡክ መረጃ መውሰድና መስጠት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት.

ናትናኤል መኮንን

 Via Natnael Mokonnen