ልደቱ አያሌው ዛሬም የዋስትና መብት ተከልክሎ በእስር ቤት እንዲቆይ ተወስኗል።

ልደቱ አያሌው ዛሬም የዋስትና መብት ተከልክሎ በእስር ቤት እንዲቆይ ተወስኗል።

ልደቱን የቢሾፍቱ ቄሮዎችን ለአመፅ በማነሳሳት መክሰስና በእስር ማንገላታት የፍትህ ስርአቱ ዝቅጠት ትልቅ ማሳያ ነው። የማይመስል ነገር። ልደቱ የአብይ አህመድ ጥርስ ውስጥ የገባው በነዚህ ምክንያቶች ነው።

⚡️የብልጥግና አባል እንዲሆን አስጠይቆት ፈቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ

⚡️ ብልጥግና ጉባኤ ሳያካሂድ ማእከላዊ ኮሚቴ ፤ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ፤ ፕሬዚደንትና ምክትል ሳይመርጥ በምርጫ ቦርድ መመዝገቡን በመቃወሙና ለፓርቲው ህጋዊነት እውቅና ባለመስጠቱ

⚡️ አብይ የህገ መንግስት ትርጉም በሚል አካሄድ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ የመንግስትን ስልጣን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ተቀባይነት እንደሌለው በመናገሩና ከመስከረም ሰላሳ በኋላ የማስተዳደር ስልጣን ያለው መንግስት እንደማይኖር በመናገሩ

⚡️ ከጃዋር ጋር OMN ላይ መቅረቡ። ይህ በተለየ ሁኔታ ብልጥግናን ያስደነገጠበት ምክንያት በአማራና በኦሮሞ ፓርቲዎች እና ህዝቦች መሃል የማገናኛ ክር እነሱ ብቻ እነደሆኑ ለማሳየት የሚያደርጉትን ጥረት የሚያከሽፍ መሆኑ ነው። ይህ ቃለ መጠይቅ በተደረገ በነጋታው ንጉሱ ጥላሁን ሊዋሃዱ የማይችሉ አስተሳሰቦች ተቀናጅተው ጥፋት ደግሰዋል ማለቱን እናስታውሳለን።

⚡️ትልቁ የብልጥግና ካዳሚ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከልደቱ ጋር የቆየ ልዩነት (ፀብ) ስላለው ልደቱን ማሰር ለብርሃኑ ተጨማሪ እጅ መንሻ ስለሚሆንና አብይ ከብርሃኑ ተጨማሪ loyalty ስለሚያስገኝለት።

በፖለቲካ ከልደቱ ጋር የማንስማማባቸው በርካታ ነገሮች ይኖራሉ። ነገር ግን ይህንን ነውረኛ የፖለቲካ ሸፍጥ እያዩ ዝም ማለት ለህሊና ይከብዳል። ልደቱን ፍቱት።

THE FINFINNE INTERCEPT