ለTaye Dendea Aredo: የጥላቻ ንግግር(hate speech)የብልጽግና ፓርቲን አይመለከትም ???

ለ Taye Dendea Aredo: የጥላቻ ንግግር(hate speech)የብልጽግና ፓርቲን አይመለከትም ???

ለ Taye Dendea Aredo፦
Via Getu Saqeta

“ሸኔ” በሚል ባዶ ጩኼት የራስን ጥፋት በሌላ ላይ የማላከክ ‘የዕብደት ፖሌትካ’ አያዋጣም!

በመጀመርያ ደረጃ ለአንቴ ባዶ ጩኼት ዋጋ ሰጥቼ ጊዜዬን በማጥፋቴ ፈጣሪ ዋቃ ይቅር ይበለኝ። ቀጥሎ የአንቴ የዕውቀት ቁንፅልነት ምን ያህል አሳዛኝ እንደሆነ መደበቅ አልፈልግም። ይሄን ዕብደት ብለው ይቀለኛል።

ወደ ቁምነገሩ ስመለስ፡ የተዘጋው ኢንተርኔት ብቻ ሳይሆን ስልክ፣ ውሃ እና ኤለክትርክ ጭምር ነው። እንቴርነት የተዘጋው ከመላው ምዕራብ ኦሮሚያ ነው እንጅ ከ “ወለጋ” ብቻም አይደለም። በወለጋ ውስጥ የሚኖር በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ አይደለም አንድ ሰውም ቢሆን መረጃ የማግኘት፣ የመያዝ እና የማስተላለፍ መብት አለው። በተለይ በአሁን ጊዜ አለማቀፍ ወረርሽን በታወጀበት ሁኔታ ይህን መብት መገደብ ከዘር ማጥፋት ወንጀል ያልተናነሰ አደጋ ሊያስከትል ይቸላል። አገልግሎቱ የተቋረጠበትን ቦታ ደግሞ “ወለጋ” በሚል ብቻ መገደብህ ትልቅ ቅጥፈት ነው።

ያም ሆነ ይህ፡ አለማቀፍ ሚዲያዎች እና የሰብዓዊ ተሟጋች ተቋማትም (OHCHR እና Special Rapporteur for Freedom of Expression ጨምሮ) ይሄን እውነታ እያጋለጡ ባሉበት ሁነታ አንተ ዐይንህን በጨው ታጥቤህ አገልግሎቱ የተቋረጠው ‘“ወለጋ” ላይ ብቻ ስለሆነ ችግር የለውም’ ለማለት ይቃታሃል። ይሄንን ሐቅ አንቴም በደምብ ስለሚታውቅ እዚህ ላይ አልዘረዝርልህም።

ሌላው “ሸኔ” እያልክ የሚትጠራው ሃይል ዘግናኝ ወንጀሎችን እየፈፀመ መሆኑን ባገኜሄው አጋጣሚ ሁሉ ስትፅፍ እና ስትለፍፍ ይሄው ከአንድ ዓመት በላይ እየታዘብኩህ ነው። ነገር ግን በጣም የሚገርመው ክስህንም ሆነ ስሞታህን አንድም ቀን በተጨባጭ ማስረጃ አስደግፈህ ማቅረብ አልቻልክም። ስለሆነም፡ እስት እውነነት ማስረጃ በእጅህ ካለህ አውጣው ወይም ገለልተኛ የሆነ ኮሚሽን ተቋቁሞ በአከባብው ላይ የተፈፀመውን ግፍ መርምሮ ሐቁን እንድያጋልጥ ለመንግስትህ ምክር ስጥ።

አንድ የማይካድ እውነታ አለ። ይሄውም፡ አንቴ እና ተከታዮችህ ከሚትሉት በተቃራኒ ምዕራብ ኦሮሚያ እና ሌሎች አከባቢዎች ላይ የመንግሥትህ ወታደሮች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈፀሙ እንደሆነ በተጨባጭ ማስረጃ የተደገፉ በርካታ ዘገባዎች ይፋ ሆኗል። አንዳንዶቹን ዘግናኝ ወንጀሎችን በአይናችን አይተናል።

ስለሆነም፡ “ወለጋም” በል “ጋርባጉራቻ” የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዳይከፈት ሽንጥህን ገትረህ የሚትሟገተው ምናልባት በአንቴ መንግሥት የፀጥታ ሃይሎች ንጹሃን ላይ የተፈፀሙት ወንጀሎች ይጋለጣሉ ከሚል ሥጋት ከመርበድበህ የተነሳ ካልሆነ በስተቀር የአገልግሎቶቹን መዘጋት “ሼነ” ከሚለው አዕምሮህ ውስጥ ከተፈጠረው Unicorn ዓይነት ምናባዊ ፍጡር ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም። የአንቴ ክስ “ፍየል ወዲያ፡ ቅዝምዝም ወዲህ” የሚሉት ዓይነት ተረት ተረት ነው።
ለማንኛውም እየፈፀምክ ላለሄው ቅጥፈት እና ደባ ሁሉ ከሰው ፍርድ ታመልጥ ይሆናል፤ ነገር ግን የፈጣሪን ፍርድ አታመልጥም።
End
ዋቃ ይፋረድህ!