ለዚህ ጥፋት አንዳንድ የሀይማኖት መሪወች ከተጠያቂነት የሚያመልጡ አይመስለኝም…

ለዚህ ጥፋት አንዳንድ የሀይማኖት መሪወች ከተጠያቂነት የሚያመልጡ አይመስለኝም…

“ከመካላከያ ጎን እንቆማለን” “ዘራፍ” “በለው” “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው” ምናምን ብላችሁ እነዚህን ወጣቶች ለእሳት; የትግራይን ህዝብ ደግሞ ለስቃይ እና ለመከራ የዳረጋችሁ; የሃይማኖት መሪዎች በተለይ ደግሞ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች እና አገልጋዮች; ለዚህ በደላችሁ እግዚአብሔር ይጠይቃችዋል:: እናንተ በሞቀ ቤት ውስጥ እየኖራችሁ; በየካፌውና ሬስቶራንቱ እየዞራች; የደሃው ልጅ ግን ተማርኮ በየመንገዱ አንገት ደፍቶና አቀርቅሮ ይሰቃያል:: ሀገርን ለውድቀት ህዝብን ለጥፋት በማድረግ ውስጥ ተባባሪ ስለሆናችው ከተጠያቂነት አታመልጡም:: በዚህ አጋጣሚ ግን, የትግራይ ህዝብ ስለ አሳያችሁት ቸርነት እግዚአብሔር ይባርካችሁ ልል እፈልጋለው:: በዚህ ሰራዊት ጥቃት ለማድረስ ከበቂ በላይ ምክንያት ብኖራችሁም እናንተ ግን የአምላክን መንገድ መርጣችኃልና እናመስግናለን::
 
የኢትዮጵያ መንግሥት እነዚህን ወታደሮች ሁለቴ መግደል የለበትም:: በመጀመሪያ ላላስፈላጊ ጦርነት ዳርጎ ለሞትና ለውርደት አበቃቸዉ:: አሁን ደግሞ የእኔ ሰራዊት አይደሉም ድራማ ነው እያለ በስቃያቸው እየተሳለቀ ይገኛል:: ይልቅ እነዚህን የጦር ምርኮኞች በአለም አቀፍ የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ እንዲደገፉ ማድረግ አለበት:: These Prisoners of War (POWs) must be taken care by International Red Cross Society (ICRC), the Ethiopian Red Cross Society (ERCS) & other international and local humanitarian agencies. POWs are protected under the Geneva convention.
እግዚአብሔር ለህዝቡ ይድረስ
ቄስ ተመስገን

Temesgen Mengesha Dabsu


ሰበር ዜና ዛሬ Ethiopia |Tigray News | Ethiopian today July 4, 2021