ለእኛ የኦሮሞ ህዝብ ጥላ ከለላችን ነው፣ ህዝቡ ባይከላከል ኖሮ ከባድ ጉዳት ይደርስብን ነበር

‹‹ለእኛ የኦሮሞ ህዝብ ጥላ ከለላችን ነው፣ ህዝቡ ባይከላከል ኖሮ ከባድ ጉዳት ይደርስብን ነበር፣ ያዳነን የኦሮሞ ህዝብ ነው ›› የተፈናቀሉ ዜጎች

የኦሮሞ ህዝብ

‹‹ለእኛ የኦሮሞ ህዝብ ጥላ ከለላችን ነው፣ ህዝቡ ባይከላከል ኖሮ ከባድ ጉዳት ይደርስብን ነበር፣ ያዳነን የኦሮሞ ህዝብ ነው ›› የተፈናቀሉ ዜጎች
ባህር ዳር፡ ጥቅምት 15/2010 ዓ/ም (አብመድ)
ዛሬ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሶስት አመራሮች እና የኦሮምያ ክልል ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አዲሱ አረጋ በቦታው ተገኝተዋል፡፡

ሰሞኑን ግጭት ተፈጥሮበት በነበረው በቡኖ በደሌ ዞን ገቺ ወረዳ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ መኖሪያቸው ለመመለስ የሀገር ሽማግሌዎች፣አባ ገዳዎች እና የሀይማኖት አባቶች በሚያደርጉት ውይይት ላይ ከአማራ ክልል የሄደው ልዑክ በቦታው ተገኝቷል፡፡
ከልዕኩ ጋር የተጓዙት የአማራ ክልል የመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንዳስታወቁት ሀገር ሽማግሌዎች ፣አባ ገዳዎች እና የሀይማኖት አባቶች የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ መኖሪያቸው ለመመለስ እና ለማቋቋም እንደሚሰሩ ገልፀውልናል ።በመቀጠልም ከተፈናቃይ ወገኖች ጋር ተወያይተናል ብለዋል ።

የአካባቢው ህዝብ ለተፈናቃዮች ምግብ፣ አልባሳት እና ዕለት አስፈላጊ ቁሳቁስ በማቅረብ ላይ ነ ።መንግስትም ምግብ፣ብርድ ልብስ ፣ ድንኳን እና የመሳሰሉትን በማቅረብ እንደሚገኝ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተናግረዋል፡፡

‹‹ባደረግነው ውይይት ህዝቡ ወደ ቋሚ መኖሪያው ለመመለስ ስምምነት ላይ የደረሰ ሲሆን መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ እና ለቀጣይ ኑሯቸውም ዋስትና እንዲሚሰጣቸው አረጋግጠን፤ ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት ለመመለስ እንደሚሰራ ማረጋገጥ ችለናል›› ብለዋል።

አቶ ንጉሱ አክለውም በዛሬው ዕለት ከበደሌ ወረዳ ተፈናቅለው በበደሌ ከተማ የተጠለሉ ሙሉ በሙሉ ወደ መኖሪያቸው የተመለሱ ሲሆን ከገቺ ወረዳ ሶስት ቀበሌዎች የተፈናቀሉ ወገኖችም ተመልሰዋል። በድምሩ 640 ሰዎች ተመልሰዋል ። ቀሪዎቹንም ለመመለስ ውይይቱ ቀጥሏል ነው ያሉት።

የአካባቢው ህዝብ ‹‹በእናንተ የመጣ በእኛ የመጣ ነው፣የእናንተ ችግር የኛ ችግር ነው፣ አብረናችሁ የመጣውን እንመክታለን፣ የፈረሰውን እንጠግናለን ፣የተዘረፈውን እናስመልሳለን ፣ አብረን እንዘልቃለን ›› ብሏል፡፡
የተፈናቀሉት ወገኖች በበኩላቸው ‹‹ለእኛ የኦሮሞ ህዝብ ጥላ ከለላችን ነው፣ ህዝቡ ባይከላከል ኖሮ ከባድ ጉዳት ይደርስብን ነበር፣ ያዳነን የኦሮሞ ህዝብ ነው ›› በማለት የማይነጠሉና አንድ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የአማራ ክልል የመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ከቦታው እንደገለጹልን የፀጥታ መዋቅሩ እስከ አሁን ድረስ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 240 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መጀመሩን ገልጸዋል።Two days ago I was referring to Amhara elders who went to Mekele and exposed TPLF’s lies about ‘ethnic cleansing in Amhara region’. I found the video. The so called the TPLF government is a Malignant neoplasm in that country. The Ethiopia people must eradicate it as such.

Via: Jawar Mohammed