“ለኢትዮጵያ አንድነት ሲባል የኦሮሞን ማንነት አጥፋ…”- የአፄው ትርክት

“ለኢትዮጵያ አንድነት ሲባል የኦሮሞን ማንነት አጥፋ…”- የአፄው ትርክት

ይህን ከላይ ያለውን ሀሳብ ለአጼ ሀይለስላሴ ያቀረበው በ1933 ከቤልጅግ አገር በማህበራዊ ሳይንስ በሁለተኛ ድግሪ ተመርቆ የመጣው አቶ ተድላ ኃይሌ ከውጪ ሀገር ትምህርቱ መልስ የትምህርቱ ዋና ጭብጥ አድርጎ ለኃይለስላሴ መንግስት ያቀረበው ምክረ ሀሳብ ነው።
.
አቶ ተድላ ኃይሌ በዘመኑ የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር የነበሩ በአቶ ሳህሌ ፀዳሉ እንዲሁም በጠቅላይ ሚንስትሩ አክሊሉ ሀብተወልድ በኩል ዓላማውን በስራ ላይ ለማዋል ተጠቅመዋል።
.
ምን ነበር ዓላማው?
.
ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ “Pioneer of change in Ethiopia.” በሚለው መፅሀፋቸው እንዳስቀመጡት እንደወረደ ትርጉሙ እነሆ:-

“የኢትዮጵያ ነገስታት ኦሮሞዎችን በተመለከተ ሶስት ዓማራጮች አሏቸው:-

1ኛ, ሁሉንም ኦሮሞ ሀብት አልባ ባሮች ማድረግ
2ኛ , ኦሮሞን ወደ አማራነት በመቀየር (Assimilation) ማንነቱን ማጥፋት
3ኛ እኛ በምንመድበውና ለእኛ ዓላማ የሚሰሩ ኦሮሞዎችን መርጠን በመሾም በእጅ አዙር እናስተዳድራቸው የሚል ሲሆን አንደኛውንና ሶስተኛውን አማራጮች መጠቀም ለአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ጠቃሚ ቢሆንም በእኛ ሁኔታ ጠቃሚ አይደለም። ስለሆነም የእኛ ዋና ዓላማ ሁለተኛው ምርጫ የኦሮሞን ማንነት ወደ አማራነት
መቀየር (Assimilate) ማድረግ ይሁን ”
.
እንዴት ሆኖ ስራ ላይ ይውላል ለተባለው ጥያቄ የአቶ ተድላ መልስ:

1ኛ, በስርዓተ ትምህርት በኩል የአማርኛ ቋንቋና የአማራ ባህል ኣንዲስፋፋ ማድረግ።

2ኛ, አማርኛ የሚናገሩ ወታደሮችን በኦሮሞዎች ውስጥ ማስፈርና ከኦሮሞዎች ውስጥ የሚመለመሉ ወታደሮችም አማርኛ ብቻ እንዲናገሩ ማድረግ።

3ኛ, በኦሮሞ ምድር የሰፈሩ ወታደሮች የኦሮሞ ሴቶችን እንዲያገቡና አማርኛ መናገር እንዲያስተምሩ ማድረግ (ተዋልደና የምትል እንዴት እንደተዋለድክ ተመልከት) ሲሆን ከዚህም ጋር ማናቸውም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ማለትም የአስተዳደር ፣ የዳኝነት፣ የምጣኔ ሀብት ድርጅቶች ሁሉ የኦሮሞን ማንነትን በማጥፋት ላይ እንዲያተኩሩ ማድረግ፣ ጠቅላይ ግዛቶች ወይም የአስተዳደር ክፍሎችም ለዚህ ማንነት የማጥፋት ዘመቻ በሚያመች መንገድ እንደገና እንዲሸነሸኑ ይደረግ ከዚህም በተጨማሪ የኦሮሞዎችን ብዛት ለመበረዝ አማራዎችን በተለያዩ የኦሮሞ ክፍሎች
ውስጥ ማስፈር፣ እንዲሁም ትግሬዎች የኩሽ ቋንቋዎችን ቶሎ ስለማይለምዱ እነሱንም ማስፈር ያስፈልጋል።
.
” ኦሮሞነትን ማጥፋት ዘመቻ በምንም ምክንያት የማይታለፍ (imperative) የመጀመሪያው አጀንዳችን ካልሆነና ማንነታቸውን ይዘው እንዲቆዩ ከተፈቀደ አማራና ኦሮሞ ወደፊት ሁለት የተለያዩና የሚቀናቀኑ መንግስቶች ሊመሰርቱ ይችላሉ”ካሉ ቦሀላ አቶ ተድላ በመቀጠል “ኦሮሞዎችን ዘመናዊ ትምህርትና የውጪ ቋንቋ ማስተማር የኦሮሞን ብሄረኝነት ስለሚያሳድግ ኦሮሞዎች እንግሊዘኛ ፣
ጣሊያንኛ ወይም ፈረንሳይኛ እንዳይማሩ ጥንቃቄ ያስፈልጋል”
.
የአቶ ተድላ ኃይሌ ምክር በምን መልኩ ወደ ተግባር ተቀየረ አቶ ተድላ ኃይሌ እንዲህ ይላል “ይህንን የኦሮሞ ማንነት (Assimilate) መለወጥ ደግሞ ንጉሳችን ዳግማዊ ምንሊክ ለእነ ራስ ጎበና፣ ለእነ ፊታውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስና ….ለእነ ደጃዝማች ገ/እግዜብሔር ሞሮዳ ስልጣን በመስጠትና ኦሮሞነታቸውን በመለወጥ አሳይተውናል”
.
ከፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ጋር እንቀጥላለን “Entrusting the education of the Oromo to the English, the Italian or the French could therefore only end up in nurturing Oromo nationalism.”
2005 :page 132-140
.
በአቶ ተድላ ምሁራዊ ምክር :- የተጠናከሩት በዘመኑ የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር የነበሩት የአቶ ሳህሌ ፀዳሉ ደግሞ በ1933 የሚኒስተርነት ስልጣናቸውን ተጠቅመው
የሚከተለውን ፀረ- ሰው ልጅ መብት ገፋፊ አዋጅ አወጁ
” ያገር ጉልበት አንድነት ነው አንድነትንም የሚወልደው ቋንቋ ልማድና ሃይማኖት ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያ ቀዳማዊ መሆኗን ለማስመስከር አንድነቷንም ለማፅናት እስከ አሁን በቆየው ልማዳችን ተማሪ ቤቶቻችንን አስፍተን ቋንቋችንንና ሃይማኖታችንን በመላው በኢትዮጵያ ግዛት በአዋጅ እንዘርጋው ይህ ካልሆነ እስከመቼውም ድረስ አንድነት አይገኝም ። በመላው በኢትዮጵያ ግዛት ለስጋዊና ለመንፈሳዊ ስራ ያማርኛና የግዕዝ ቋንቋ ብቻ በህግ ፀንተው እንዲኖሩ ሌላው ማናቸውም የአረማውያን ቋንቋ ( የኦሮምኛን ጨምሮ 84 ብሄሬሰቦችን ቋንቋ መሆኑ ነው) እንዲደመሰስ ማድረግ ያስፈልጋል”በማለት አቶ ሳህሌ ፀዳሉ በመቀጠል ” ሚሲዎኖች ትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታሎችንም ቢሆን እንዳይከፍቱ መከልከል ያስፈልጋል ከከፈቱም #የውጭ_ቋንቋ_መማርም ቢሆን እድሉ #ለኢትዮጵያዊያን መሰጠት አለበት”ይላሉ። (ልብ በል ኢትዮጵያ ውስጥ የሚከፈት ትምህርት ቤት ተለይቶ ለኢትዮጵያዊያን መሰጠት አለበት ይላሉ እነዚህ ኢትዮጵያዊያን እነማን ናቸው?)
.
እዚህ ላይ መስተዋል ያለበት ሌላው ነገር አቶ ተድላ ኦሮሞዎች በአማራዎች ይዋጡ ሲሉ አቶ ሳህሌ ፀዳሉ ደግሞ የኦሮሞዎች ማንነት ካልተደመሰሰ የሀገር አንድነት አይገኝም የሚሉት ስልጣን ይቀርሙናል የሚል ስጋት ካልሆነ በስተቀር ኦሮሞዎች አንድነት አንፈልግም ያሉበትን ጊዜ አልጠቀሱም።
.
የአሁኖቹስ የመንፈሳዊና የደም ወራሾች ከዚህ የተለየ ምን አላቸው?በ1947 አቶ አማኑኤል አብረሀም ምክትል የትምህርት ሚኒስተር በነበሩ ጊዜ ” አማኑኤል የኦሮሞ ልጆችን ብቻ ያስተምራል”በማለት የኃይለስላሴ ባለስልጣኖች አቤቱታ አቅርበው ነበር። ተጨባጩ እውነታ ግን በዚያን ጊዜ ፊንፊኔ (አዲስ አበባ ውስጥ በመማር ላይ ከነበሩት 4795 ተማሪዎች መካከል 583 ብቻ ኦሮሞዎች ነበሩ ይህ ቁጥር የተማሪው 12% ብቻ ነበር ።ደቡቦች በጭራሽ አልነበሩም ኦሮሞ በአገሪቱ ወደ 40% የተጠጋ ነው።
.
ቀጥሎም በኛው ትውልድ የተመለከትነው…
-በ1985 በአምቦና በደንቢ ዶሎ የነበሩ የሀበሻ ቄሶች “ቁቤ የሚባለው የኦሮሞዎች ፊደል ካልጠፋ ለጥምቀት የወጣው ታቦት ተመልሶ አይገባም ” በማለት ያስቸግሩ ነበር።
.
በ1996/2004 የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ የኦሮምኛ ፕሮግራም ከ15 ደቂቃ ወደ 30 ደቂቃ ከፍ ማድረጉን በመቃወም በአሜሪካ የሚገኙ በርካታ ሀበሾች “ጭማሪው ይሰረዝ” በማለት ሁለት ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።
.
በ2006/2014 በዋሽንግተን የሚገኘው የኦሮሞ ማህበረሰብ ማህበር (Oromo society Center) ከዋሽንግተን አስተዳደር ሽልማት በማግኘቱ “ይሄ ለኦሮሞ ህዝብ እውቅና እንደመስጠት ነው ” በማለት በአሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ድምፅ ሬድዮ ተቃውሞ አሰምቶዋል።
.
እቺ ናት ኢትዮጵያዊነት

(እነሆ ዛሬስ……. የኦሮሞ ትግል የት ደረሰ?)

#Gumaa Saqeta


ምኒልክ በጨለንቆ

አፈንዲ ሙተቂ
—-
እምዬ ምኒልክ ለናንተ መሲሕ ሊሆን ይችላል፡፡ እኛ የምናውቀው ምኒልክ ግን ሌላ ነው፡፡ በዚህ ላይ ብዙ መናገር አያስፈልግም፡፡ ምኒልክ በጨለንቆ ጦርነት ያሻውን ከሰራ በኋላ የጻፈውን ደብዳቤ እንድታነቡት ጋብዘናችኋል፡፡
—-
• ደብዳቤው የተጻፈው ለእውቁ ሀገር አሳሽና ነጋዴ ለካፒቴን ጁልስ ቦሬሊ ነው፡፡ እኔም ከቦሬሊ መጽሐፍ ኮፒ አድርጌ ነው እዚህ የገለበጥኩት (ገጽ 199)፡፡ ደብዳቤው በሌሎች መጻሕፍት ውስጥም ይገኛል፡፡

• ደብዳቤው “ሰውን ሁሉ ፈጀሁት” ነው የሚለው፡፡ የምሥራቅ ኢትዮጵያ ህዝቦችም (ኦሮሞ፣ ሀረሪ፣ ሶማሊ፣ አርጎባ ወዘተ..) በጦርነቱ የተሳተፈ ሰው በደህና እንዳልተመለሰ ነው የሚገልጹት፡፡

• “በጨለንቆ ጦርነት አልተካሄደም” የሚሉ ሰዎች አሉ (ከነዚህ ሰዎች አንዱ ኤዱዋርዶ ባይኖሮ መሆኑ ያስገርማል)፡፡ እነዚህ ሰዎች ሐቁን ለማወቅ የሚሹ ከሆነ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሤ የጻፉትን “ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ” ማንበብ ይኖርባቸዋል፡፡ መጽሐፉን ካላገኛችሁት እውቁ ደራሲ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ የጻፉትን “አፄ ዮሐንስ እና የኢትዮጵያ አንድነት” የተሰኘ መጽሐፍ ከገጽ 291 እስከ 294 አንብቡት፡፡ ከባድ ጦርነት ተካሂዶ እንደነበረ በግልጽ ጽፈዋል፡፡

• ምኒልክ ከጦርነቱ በኋላ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ የፈጸሙትን ደግሞ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ካውክ እና ፕሮፌሰር ሙሐመድ ሐሰን በሰፊው ጽፈውታል፡፡ በወቅቱ በሀረር ከተማ ይኖር የነበረው አርተር ራምቦም ለታሪክ ባስቀረው ዝነኛ ደብዳቤው ያየውንና የሰማውን ጽፏል( ደብዳቤው በኢንተርኔት ላይ አለ፤ ብትፈልጉት በቀላሉ ይገኛል)፡፡
—–
አሁን ሁሉም አልፏል፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ታሪክ የተፈጸመው እኛ ከመወለዳችን በፊት ነው፡፡ እኛ የዚህ ዘመን ልጆች እንደመሆናችን ከሌሎች ጋር በፍቅርና በሰላም ኖረናል፡፡ በዚህ ዘመን ከኢትዮጵያ ተገንጥለን ነፃ መንግሥት እንመሰርታለን ብለን አናስብም፡፡ የሚሻለው ነገር ሁሉም ተባብሮ የተሻለች ኢትዮጵያን መፍጠር ነው፡፡ የሁሉም ህዝቦች ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ኢኮኖሚ ወዘተ ተከብሮ ሁሉም በእኩልነት የሚኖርባትን ኢትዮጵያን ለማየት እንፈልጋለን፡፡ ከሌሎች ጋር የምንኖረውም በዚህ እምነትና ተስፋ ነው፡፡

ነገር ግን ይህ አብሮ የመኖር መርህ “እምዬ ምኒልክ የኢትዮጵያ አዳኝ ናቸው፡፡ አፄ ዮሐንስ የኢትዮጵያ መጥምቁ ዮሐንስ ናቸው” ከሚሉት ሰሞነኛ ሊሒቃን እምነቶች ጋር አንድ አይደለም፡፡ እኛ ሁለቱንም አፄዎች የምናውቀው በጨፍጫፊነታቸውና በወራሪነታቸው ነው፡፡ አሁን ያለውን ውጥንቅጥ ሁኔታ የፈጠሩትም እነርሱ ናቸው፡፡ ብሄራዊ እርቅ ይደረግ የምንለውም እነርሱ የፈጸሟቸውን ጥፋቶች ማስተካከሉ አስፈላጊ ስለሆነ ነው፡፡
ስለዚህ ኢትዮጵያዊነትን ከአፄዎቹ ጋር እየቀላቀላችሁ አትስበኩት፡፡ እንደዚህ የሚያደርግ ሰው በኛ እምነት ኢትዮጵያዊነትን እያጠፋ ነው እንጂ ኢትዮጵያዊነትን እየሰበከ አይደለም፡፡ እስቲ ማ ይሙት! “ምኒልክን የማይወድ ሰው ሁሉ ፀረ-ኢትዮጵያ ነው ተብሎ ይፃፋል? …. “ምኒልክን የማይወድ ሰው የኢትዮጵያዊነትን ጣዕም አያውቀውም” ማለትስ ማን ማለት ነው?…. በዚህ ዓይነት ከግማሽ በላይ የሚሆነው ህዝባችን ጸረ-ኢትዮጵያ ነው ማለት እኮ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት እንዲህ ከሆነ እኛ የለንበትም፡፡ ኢትዮጵያዊነት የሚያምረው የሁሉንም ህዝቦች ክብርና እኩልነት የማይደፈጥጥ ሲሆን ነው፡፡

ስለዚህ ራሳችሁን አስተካክሉ!!
—–
(ይህ ፖስት የተጻፈው የራሴ አራት ዓመት ነው። ፖስቱን የለጠፍኩት “በጨለንቆ ጦርነት አልተካሄደም” ለሚሉ ሰዎች እንደ ማስረጃ ለማሳየት ነበር። ታዲያ ደብዳቤውን ስለጥፈው የአጼ ምኒልክ ደጋፊዎች የክርክሩን አቅጣጫ በመቀየር “ምኒልክ ወደ ጦርነት የገቡት አሚር አብዱላሂ እርቅ እምቢ በማለቱ ነው” የሚል አስገራሚ አስተያየት አምጥተዋል። ወዴት ወዴት? ክርክሩ “ጦርነት ተደረገ ወይንስ አልተደረገም?” ነው። ጦርነት በትክክል ተደርጓል። አሚር አብዱላሂና የኦሮሞ አባዱላዎች እርቅ እምቢ ማለታቸው ለደረሰው ጥፋት ማስተባበያ መሆን አይችልም። ምክንያቱም የሰው ሀገር የወረረው ምኒልክ ነውና።

ለማንኛውም ዋናው ቁም ነገር ደብዳቤው አይደለም። ዋናው ነገር ባለፈው ላይ ክስተት ተማምኖ ያንን አስቀያሚ ምዕራፍ በመዝጋት አዲሲቷን ኢትዮጵያ መገንባት ነው)።