በእስር ቤት ውስጥ ሰቆቃና ግፍ ለተፈጸመባቸው ካሳ ሊጠየቅ ነው

በእስር ቤት ውስጥ ሰቆቃና ግፍ ለተፈጸመባቸው ካሳ ሊጠየቅ ነው

HUMAN RIGHTS WATCH

(bbc)—ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ውስጥ ለስቃይ እና ለእንግልት የተዳረጉ የቀድሞ እስረኞች መንግሥትን ካሳ እንጠይቃለን አሉ።

የ32 ዓመቱ ሰይፈ ግርማ በሽብር ወንጀል ተከሶ ለሦስት ዓመታትን በእስር አሳልፏል።

በቆይታውም ከፍተኛ የማሰቃየትና የማስፈራራት ተግባራት ይፈፀምበት እንደነበረ የሚናገረው ሰይፈ እግሩ ላይ የሚገኘውን ትልቅ ጠባሳና በግራ ትከሻው ላይ ያለው ጉዳት ማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ በነበረበት ወቅት የደረሰበት እንደሆነ ያስረዳል።

“ከሞቱት አንለይም” የሶማሌ ክልል እስረኞች

• ”አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ንግግራቸውን በተግባር ሊያሳዩ ይገባል” የተመድ ኮሚሽነር

• “. . . ጥፍር መንቀል ሕጋዊ አይደለም ስንለው ብሔሩ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል” ጠ/ሚ ዐብይ

”ጨለማ ቤት ውስጥ ታስሬያለሁ። ምርመራዎች የሚካሄዱት በጉልበት ሲሆን፤ ደድብደባ፣ ውስጥ እግር ገልብጦ መግረፍ እና አጸያፊ የሆኑ ስድቦችን እንሰደብ ነበር። ምርመራዎች የሚካሄዱት ሌሊት ላይ ሲሆን መርማሪዎች መጠጥ ጠጥተው የሚመጡበት ጊዜ አለ” ይላል ሰይፈ።

ይህ የሰይፈ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በቁጥጥር ስር ውለው ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደተፈጸመባቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ይናገራሉ።

አብዛኛዎቹ ደግሞ መንግሥትን በመቃወምና ዴሞክራሲያዊ የሆኑ ለውጦች ይምጣ በማለት ሰልፍ የወጡ ናቸው።

ከእነዚህም መካከል ሌላኛው ዮናስ ጋሻው ይገኝበታል።

የሽብር ክስ ተመስርቶበት የነበረው ዮናስ፤ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት ሱሪውን በማውለቅ የደረሰበትን ድበደባ ለማሳየት በመሞከሩ ብዙዎች ያስታውሱታል።

• ልዩ ፖሊስን ማን መሰረተው?

• ሜጀር ጄኔራል ክንፈ: ‘‘ቤት የለኝም፣ መኪና የለኝም፣ ንብረት የለኝም፤ ያለኝ ሰውነቴ ብቻ ነው’’

በእስር ላይ በነበረበት ወቅት የደረሰበትን ጉዳት ሲያስረዳ ”በደረሰብኝ ድብደባ ምክንያት ዛሬ በክራንች ነው የምሄደው፣ በጀርባዬ መተኛት አልችልም። ሽንት ቤት እንኳ በሰው ድጋፍ ነው የምሄደው” የሚለው ዮናስ ”በቁሜ የሞትኩ ያህል ቢሰማኝም ይህንን ለውጥ በማየቴ ደስተኛ ነኝ” ይላል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በወርሃ ሰኔ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፊት ቀርበው በእስረኞች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይፈጽም እንደነበረ አምነው ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል።

ወደ ስልጣን ከመጡ ሰባት ወራትን ያስቆጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ፤ እየወሰዷቸው ያሉት የለውጥ እርምጃዎች በበርካቶች ዘንድ ተስፋን ያጫሩ ከመሆኑ በተጨማሪ ከሰብአዊ መብት ጥሰትና ሙስና ጋር በተያያዘ ወደ 70 የሚጠጉ ከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊዎችን በጥጥር ስር እንዲውሉ አድርገዋል።

የሰብአዊ መብት ተከራካሪ እና የህግ ባለሙያ የሆኑት አቶ አምሃ መኮንን በመቶዎች ለሚቆጠሩ በሽብር ወንጀል ተከሰው እስር ቤት ለነበሩ ዜጎች ጠበቃ በመሆን አገልግለዋል።

አቶ አምሃ በጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት እየተከናወኑ ያሉ ጥፋተኛ ናቸው የተባሉ አመራሮችን ለህግ የማቅረቡ ሥራ ገና የመጀመሪያ እርምጃ ነው ይላሉ።

”በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ቂም ተፈጥሯል። መንግሥት በአፋጣኝ መልስ ሊሰጥባቸው የሚገቡ ቅሬታዎች አሉ። ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የመጀመሪያው እርምጃ መሆን ያለበት ደግሞ ግልጽ ውይይት መጀመር ነው። ሃገራዊ እርቅ ያስፈልገናል” የይላሉ የሕግ ባለሙያው።

”በተጨማሪም ተጎጂዎች ካሳ የሚያገኙበትን መንገድን ለማመቻቸት እየሰራን ነው። ጉዳያችን በሃገር ውስጥ ፍርድ ቤቶች መልስ የማያገኝ ከሆነ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች ድረስ ለመሄድም ተዘጋጅተናል። እስከመጨረሻው እንታገላለን። መታገላችንን አናቆምም” በማለት አቶ አምሃ አቋማቸወን ገልፀዋል


Ethiopia: በሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ የሚያተኩር ዶክመንተሪ
በሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ የሚያተኩር ዶክመንተሪ

1 Comment

 1. Yes! Compensating and rehabilitating torture victims in Ethiopia must be among top priorities for PM Dr Abiy Ahmed and his government. The TPLF criminal Mafia group had inflicted cruel and inhumane sufferings for 27 years, including torturing and diapearing individual Ethiopians and carrying out ethnic cleansing in Oromia, Amhara, Somali region, Gambella, Sidama, Konso, etc. The minimum gesture the Ethiopian peoples in genrral and victims in particular need from the government is to address the matter genuinely, in order for the wound of injustice to heal.

  TPLF warlords who had run Ethiopia like their personal fiefdom for nearly three decades do not seem to understand the gravity of the human and material destruction they had caused, even today. Instead of acknowledging their past gross human rights violations as well as their theft of the country’s resources; rather than reflecting on their past and taking responsibilities for their messes and being held accountable, they are trying to gather in Makale and laugh into the faces of the Ethiopian people whom they had victimised. If there were any sane person in the rank and file of TPLF, their recent rally in Tigray would be to apologize to the Ethiopians whom they tortured, disappeared, gunned down in numerous parts of the country, families who lost their loved ones to Agazi shooters, kids who became orphans by security forces vented on causing maximum suffering and those they pushed into exile. Instead, they shamelessly boasted about their achievements in ‘building a country that has disrespected them’. What a joke!

  It is absolutely right and appropriate for victims of TPLF regime to demand compensation and for the Ethiopian government to address it urgently. Simple and straightforward; the government must hold individuals and TPLF group, who had used government powers and structures to violate human rights and to enrich themselves unduly, to account. The wealth they have accumulated through looting and unfair means must be confiscated and returned to the country’s account, and part of it be used to compensate and settle victims.

  On part of the victims, a channel through which those who were hurt in the hands of the regime come forwards and give evidence must be created. Justice loving legal professionals and Ethiopians who believe that the Ethiopian peoples in general and victims in particular disserve justice should offer help to organize and coordinate legal processes. Let us be determined to correct the Ethiopian error which has become synonymous with those who had come to power and made away with citizens’ rights in that country. All of us must unite to get justice for victims of the TPLF atrocities, and make this the last injustice to be committed in Ethiopian history.

  Justice for the victims of TPLF!

  OA

Comments are closed.