ለማ መገርሳ አስመራ ገባ?በሃምሌ ወር ወደ አሜሪካ ከመምጣቴ በፊት ፈረሰኛው የቃጅማ ጊዮርጊስ ምነው እግሬን በሰበረው ኖሮ? ስንት ነገር አመለጠኝ?

ለማ መገርሳ አስመራ ገባ?

በሃምሌ ወር ወደ አሜሪካ ከመምጣቴ በፊት ፈረሰኛው የቃጅማ ጊዮርጊስ ምነው እግሬን በሰበረው ኖሮ? ስንት ነገር አመለጠኝ? ለማንኛውም የአባኦ(OLF) እና የዳዴኡኦ (OPDO) ውይይት የተሳካ እንዲሆን እመኛለሁ። ለማ መገርሳ ማለት የኦሮሞን ህዝብ ትግል አንድ እርምጃ ወደፊተ ያራመደ ማለት ነው። የማይግባቡበት አንዳችም ምክንያት አይኖርም።

ቶሎ ወደ አስመራ መመለስ አለብኝ።

ኦቦ ዳውድ ወደ አገሩ የሚገባ ከሆነ ከታሪክ ሰሪው ጋር አንድ ታሪክ ጸሃፊ አብሮ መጉዋዝ አለበት። “ዳውድ ኢብሳ” የሚል ወፍራም መጽሃፍ ታይቶአችሁ ከሆነ አልተሳሳታችሁም። በአመት ሁለት መጽሃፍ መጻፍ አለብኝ። የ49 አመት ሰው ነኝ። ከጊዜ ጋር መሽቀዳደም አለብኝ። ትናንት በር ከፍቼ ከቤት ስወጣ እርጅና እንደ ታማኝ ውሻ ደጃፌ ላይ ተኝቶ አየሁት። እና የሞቀ ሰላምታ ሰጥቼው አለፍኩ።

Ambo! Galatomaa!!

ይህን ፖስተር ስመለከት መደነቄን አልደብቅም። አምቦ ሆይ!!በአክብሮት ስላሰባችሁኝ፡ ለጠላቶቼ መልስ ስለሰጣችሁ galatomaa Ambo!! በርግጥ አንድ እውነት አለ። ህዝብን ማታለል አይቻልም። የራሱ ሚዛን አለው። እውነት አልባ ፐሮፓጋንዳም እንደ ጤዛ ነው

Tesfaye Gebreab