የአዲስ አበባ ከተማ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ተጨማሪ-ከስምንት ሺሕ በላይ የ40/60 ቤቶችን ለመገንባት 38 ሔክታር መሬት ተሰጠ

የአዲስ አበባ ከተማ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ተጨማሪ-ከስምንት ሺሕ በላይ የ40/60 ቤቶችን ለመገንባት 38 ሔክታር መሬት ተሰጠ

In Bole and Qaalitti sub-cities, a roughly estimated 5000 hectare of land is still farmed by Oromo farmers. All kind of expansions are now going on there. We want to know a clear policy how to deal these farmers. Land grabbing is still alive in Oromia!!!

ከስምንት ሺሕ በላይ የ40/60 ቤቶችን ለመገንባት 38 ሔክታር መሬት ተሰጠ

(ethiopianreporter)—-የአዲስ አበባ ከተማ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ተጨማሪ 8,428 የ40/60 ቤቶችን ለመገንባት፣ 38 ሔክታር መሬት ከአስተዳደሩ መረከቡን አስታወቀ፡፡

ባለ 15 እና 13 ፎቅ 54 ሕንፃዎችን ለመገንባት የዲዛይን ማጣጣም ሥራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን፣ በኢንተርፕራይዙ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት ደጋፊ የሥራ ሒደት መሪ በአቶ ዮሐንስ አባይነህ ተፈርሞ ወጪ የተደረገው ደብዳቤ ያስረዳል፡፡

ኢንተርፕራይዙ ተጨማሪ 8,428 ቤቶችን ለመገንባት ከአስተዳደሩ መሬት የተረከበው በተለምዶ ቦሌ አራብሳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን፣ ባለ 15 ፎቅ 40 ሕንፃዎችና ባለ 13 ፎቅ 14 ሕንፃዎች እንደሚገነቡ ተጠቁሟል፡፡ ኢንተርፕራይዙ ወደ ግንባታ ለመግባት አማካሪ ድርጅቶችን ለመምረጥ የጨረታ ሰነድ ተከፍቶ፣ የቴክኒክ ግምገማ እያደረገ መሆኑም ተገልጿል፡፡

እንደ ኢንተርፕራይዙ ገለጻ፣ የሕንፃ ተቋራጮችን ለመምረጥ የሚያስችል የማኑዋል ዝግጅት መጠናቀቁንና ማኔጅመንቱ በቅርቡ አፅድቆት ሥራው ይጀመራል፡፡ ቀደም ብሎ በተገነቡ ሕንፃዎች ላይ አጋጥመው የነበሩና እስካሁንም ያልተፈቱ ችግሮች እንዳያጋጥሙ፣ እንዲሁም ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ከብረትና ከሊፍት በስተቀር የሌሎች ግብዓቶችን አቅርቦት በአግባቡ የሚያከናውንበት አዲስ የኮንትራት አስተዳደር ሥርዓት ተግባራዊ እንደሚያደርግም ገልጿል፡፡ ሥራውን የሚያስፈጽምም አምስተኛ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መክፈቱንም አክሏል፡፡

የግብዓት አቅርቦት በሥራ ተቋራጮች እንደሚፈጸምና ኢንተርፕራይዙ ፕሮጀክቶቹን በመምራት፣ የጥራት ቁጥጥር ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ ወጪ የተደረገው ደብዳቤ ያስረዳል፡፡ አዲስ ለሚጀመሩት ቤቶች የብረት ግብዓት አስቀድሞ ለማሟላት ኢንተርፕራይዙ ከ50 ሺሕ ቶን በላይ የአርማታ ብረት በዓይነትና በመጠን ለይቶ በግዥ ሒደት ላይ መሆኑንም አክሏል፡፡

የአገር ውስጥ ወይም ዓለም አቀፍ ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ ስለመቻላቸው፣ ጨረታው መቼ እንደሚወጣ፣ ግንባታው መቼ እንደሚጀመርና በስንት ዓመታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ፣ ለግንባታው የተመደበው የገንዘብ መጠንና ከየት እንደተገኘ ማብራሪያ እንዲሰጡ የኮሙዩኒኬሽን የሥራ ሒደት መሪውን አቶ ዮሐንስን ለማግኘት በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ላይ ተደውሎ ስልካቸውን ያነሱት ቢሆንም፣ ጥያቄዎቹን አዳምጠው በመዝጋታቸው ማብራሪያ ማግኘት አልተቻለም፡፡ ኢንተርፕራይዙ በአሁኑ ወቅት 38,000 የ40/60 ቤቶችን እየገነባ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡