#ለመላው ወላይታ ህዝብ የቀረበ ጥሪ.

 
እንደሚታወቀው ፣ወላይታ ራሷን የቻለች፣ሀገር የነበረችና፣በራሷ ገንዘብ የምትገበያይ፣ጠንካራ በንጉሳዊ አስተዳደር የነበራት እንዲሁም ፣ከጎረቤቶቿ ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲ በመፍጠር፣የኖረች ሀገር መሆኗ የሚታወቅ ነው። ነገር ግን ወደ ኢትዮጵያ ከተቀላቀለች ጊዜ አንስቶ ገጥሟት የማያውቅ ትልቅ፣ክህደት አሁን ተፈጽሞባታል።
#ልጆቿ ከወጡበት እንኳን በአከባቢያቸው ሳይቀር መመለስ አልቻሉም።
#ንጉስ ጦና፣ለአጸ-ሚኒልክ አልገብርም በማለት የታወጀበትን ፣ለወረራ የመጣውን የሚኒልክን ጦር ለስድስት ጊዜ ያህል በአስተማማኝ ሁኔታ በመመከት፣የሚኒልክን ጦር በማንበርከክ በተለያዩ አቅጣጫ የመጣውን የጠላት ወራሪ ሀይል በመመከት ለጊዜውም ብሆን የወላይታ ህዝብ ደረታቸውን ነፍተው፣በሀገራቸው እንድኖሩ፣መስዋዕትነት ከፍሏል።
 
#ከአጸ ሚኒልክ ዘመን አንስቶ የሚፈራረቅበትን አሀዳዊና ዘውዳዊም አገዛዝ አልቀበልም በማለት ከፌደራሊስት ሀይሎች ጋር በመሆን፣በኢትዮጵያ ለውጥ እንድመጣ፣ባለፉት 30 አመታት የራሱን አስተዋጽኦ ያደረገ ህዝብ ነው።
#አሁን ዳግም እያቆጠቆጠ ያለው አሃዳዊ አገዛዝ ወላይታን ለማንበርከክ፣ልጆች፣ዬላጋዎች፣አባቶች፣አይዳሚያዎች፣ጎልተው እንዳይወጡ፣ድባቅ በመምታት፣በሴራ የተሞላ፣ለወላይታ ህዝብ ምንም የማይጠቅም ፣መንግስታዊ አሰራር በመዘርጋት፣ወላይታ በኢትዮጵያዊነት እንዳይኮራ፣በማድረግ የማግለል ፖለቲካ እያራመደ ፣የሚገኘው፣ብልጽግና ፓርቲ ከህዝብ ጫንቃ እንድወርድ፣ህዝቡ ልነሳ ይገባል።
#ስለሆነም መላው የወላይታ ህዝብ አንድላይ በመሆን፣ከፌደራሊስት ሀይሎች ጋር በመሆን፣ሀገራችንን ከአሃዳዊ ስርዓት ማዳን ይኖርብናል ።
ለዚህም የወላይታ ፖለቲካ ሁኔታ እና አፈና የተሞላበት አሰራር ምን መሆን እንዳለበት እንድንወያይ እንጠይቃለን።
#ምንም እንኳን በአሁን ሰዓት ለመወያየት እንኳን አዳራሽ የማይፈቀድ በመሆኑ፣ሀገር ወዳድ የወላይታ ልጆች፣ሀሳባችሁን እንድታጋሩ እንጠይቃለን።


እንግዲህ ተመልከቱ ይሄን ጉድ አሳፋሪ ተግባርን ነገሩ እንዲህ ነው ዛሬ በወላይታ ሶዶ ማረሚ የታሰሩትን ለመጠየቅ ሀገር አቋርጦ ልጆቻቸውን ጥለው “የታሰረውን ጠይቅ” የሚለውን እግዚአብሔርን ሰምተው ልጆቻችን እንጠይቅ ብለው መጥተው ያለምንም ምክኒያት ወደ ማረፊያ ገብተዋል። የወላይታ ህዝብ እውነት ጨዋና እግዚአብሔር የሚፈራ ህዝብ ነው ወንጌልን በተግባር የሚፈጽም ትሁት እና ታዛዥ ህዝብ ነው።
 በእስራ ላይ ያሉትን እኛም ለመጠየቅ ተጉዘን ውሃና መጠነኛ እራት አቅርበን ሰጥተን እነርሱ ጋር ቆይተናል። እኛም የታሰሩትን ለመጠየቅ በሄድንበት ወቅት ያየነው ነገር ፍጹም ተገቢ አይደለም ሰውን ማመናጨቅ የአስተሳሰብ ዝቅጠት ነው። ቢታረምና ቢስተካከል የተሳለ ነው ይሄ ከሰው የማይጠበቅ ተግባር ነውና።
በነገራችን ላይ ከእኛ ጋር እነዚህን አባቶች ለመጠየቅ ከተጓዙት መሐል ዬላጋ ጎበዜ “ግባ”ተብሎ ወደ ማረፊያ ተቀላቅሏል። እኔም ከእስር ተርፌ አበበ ዘለቀ ላይ ሆኜ ይችን መረጃ ጻፍኩላችሁ። ነገ ጠዋት ለቁርስ ጥየቃ ስሄድ ከታሰርኩ ደስ ይለኛል ለህዝብ መታሰር መፈታት ነውና።
ፍትህ ለህዝባችን ፍትህ ለአባቶቻችን
ወላይታ ዳልጋ ማንቲያ 
WRS WDM ወብክመ 
አንዱሻ ነኝ የ27ት በቀን 15/2/2013 ዓ/ም