“ህገወጥ እስር ቤት እንደቀር፣ ጥፍር መንቀል፣ ጨለማ ቤት ማሰር… እንድቀር የማራሚያ ቤት አስተዳደር ሪፎርም ሰርተናል።” አብይ አህመድ

“ህገወጥ እስር ቤት እንደቀር፣ ጥፍር መንቀል፣ ጨለማ ቤት ማሰር… እንድቀር የማራሚያ ቤት አስተዳደር ሪፎርም ሰርተናል።” አብይ አህመድ
ለአንድ ወር ከዚያ በላይ በህገወጥ እስር ቤት (6 ኪሎ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ጣቢያ፣ ጭለማ ቤት) የታሰሩ ከአስር በላይ የሚሆኑ ጓዶቼ አሉ።
1, ሚካኤል ቦረን
2, ኬነሳ አያና
3, ለሚ ቤኛ
4, ዶ/ር ድሪባ ዋቅጅራ
5, ግንባር ነገራ
6, ዶ/ር ሁሴን ከድር
7, ኦብሳ አብዲሳ
8,ዳዊት አብደታ
9,አብዱልጋፈር ኡመር
10, ኮ/ል ገመቹ አያና
እና የመሳሳሉት በጭለማ ቤት ተቆልፎባቸው፣ ከህግ አግባብ ውጭ( አብዛኞቻቸው በፍርድ ቤት የለቀቃቸው ( አሁን ፍርድ ቤት የማይቀርቡ፣ አቃቤ ህግ መመዝገባቸውን የዘጋ) ታጉሮ እያሉ፣ እያየሁ ውላለሁ። አብይ ይህን እያተናገረ ከማረሚያ ቤት ፖሊስ ደወለልኝ፣ “ሰው ይፈልገሃል አናግራው!” ተብዬ ስልክ አቀበለው እና አወራኝ። አላወቁትም ” Urjii dha na hin barree?” ይለኛል። “ኡርጂ ነኝ አለወቅከኝም?” እንደማለት! እንዳላወኩት ሲራደ፣ የአባቱን ስም አላስከተለም። “Urjii mucaa kolaafame sana! ኡርጂ ያ የተኮለሸው ልጅ” አለኝ። የግል ችግሩን ሊነግረኝ ነው ለነገ እንዳገኘው የቀጠረኝ። እኔ ግን በጣም አዝኛለሁ፣ ልቤ በጣም ተውኳል። ኡርጂ ሲያዝ 17 አመት ለጋ ወጣት ነበር፣ ዛሬ 18 ዐመት ሆኖታል። 6 ኪሎ ባለው የአብይ አህመድ ዘመን “ጎንታነሞ” ውስጥ ጥፍሩ ተነቅሏል፣ ተኮላሽቷል። ይህን ቀድሜም አውቃለሁ፣ ከሌሎች በርካታ የኦሮሞ ወጣቶች ጋር የደረሰባቸውን ለፍርድ ቤት ስያቀርቡ ሰምቻለሁ። አሁን የረበሸኝ ግን የስሙ ቅጥያ(መታወቂያው) አድርጎ “የተኮላሸው ልጅ” ስለኝ እንባዬ መጠ። ወንድ ልጅ በዚህ ጉዳት ራሱን ሲጠራ ያማል!
አብይ ከወያኔ የተሻለው በግብዝነቱ ብቻ ነው! ወያኔዎች እኮ ያራጉት አድርገው ዝም ይላሉ፣ ያደረጉትን (የሚያደርጉትን) በአደባባይ ሲረጉሙት አለያቸውም! ከሚያደረገው አኩል፣ “እንደነርሱ…!” እያለ ራሱን የሚያመፃድቀው ነገር የግብዝነቱ ጥግ ማሳያ ነች።
ፈጣሪ ይፍረድ!